กันดารวิถี 20 – TNCV & NASV

Thai New Contemporary Bible

กันดารวิถี 20:1-29

น้ำจากหิน

1ชุมชนอิสราเอลทั้งปวงมาถึงถิ่นกันดารศินในเดือนที่หนึ่ง และตั้งค่ายพักแรมที่คาเดช มิเรียมสิ้นชีวิตลงและถูกฝังไว้ที่นั่น

2ที่แห่งนั้นไม่มีน้ำให้ประชากรดื่ม พวกเขาจึงรวมตัวกันต่อต้านโมเสสกับอาโรนอีก 3พวกเขาโต้เถียงกับโมเสสและกล่าวว่า “เราน่าจะตายพร้อมกับพี่น้องของเราซึ่งล้มตายต่อหน้าองค์พระผู้เป็นเจ้า! 4เหตุใดท่านจึงนำชุมชนขององค์พระผู้เป็นเจ้ามาตายในถิ่นกันดารนี้ รวมทั้งฝูงสัตว์เลี้ยงของเราด้วย? 5ทำไมถึงให้เราออกจากอียิปต์มาอยู่ในที่เลวร้ายเช่นนี้? ไม่มีเมล็ดข้าวหรือมะเดื่อ องุ่น หรือทับทิม มิหนำซ้ำยังไม่มีน้ำให้ดื่ม!”

6โมเสสกับอาโรนออกจากชุมนุมประชากร ไปยังทางเข้าเต็นท์นัดพบและหมอบกราบซบหน้าลง และพระเกียรติสิริขององค์พระผู้เป็นเจ้ามาปรากฏต่อพวกเขา 7องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับโมเสสว่า 8“จงเอาไม้เท้ามา แล้วเจ้ากับอาโรนพี่ชายของเจ้าจงเรียกประชากรมารวมกัน จงพูดกับศิลานั้นต่อหน้าพวกเขาและศิลานั้นจะหลั่งน้ำออกมา เจ้าจะให้น้ำแก่ชุมชนจากศิลานั้น เพื่อทั้งคนและสัตว์จะได้ดื่มกิน”

9ดังนั้นโมเสสจึงนำไม้เท้าจากเบื้องหน้าองค์พระผู้เป็นเจ้ามาตามที่ตรัสสั่ง 10เขากับอาโรนเรียกประชากรมารวมกันที่หน้าศิลา และโมเสสพูดกับพวกเขาว่า “ฟังนะ เจ้าพวกกบฏ เราจะต้องเอาน้ำออกจากศิลานี้ให้พวกเจ้าหรือ?” 11แล้วโมเสสก็เงื้อไม้เท้าขึ้นฟาดก้อนหินสองครั้ง น้ำจึงพุ่งออกมา ทั้งคนและสัตว์ได้ดื่มกิน

12แต่องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับโมเสสและอาโรนว่า “เพราะเจ้าไม่ได้เชื่อเรามากพอ ไม่ได้ให้เกียรติเราในฐานะองค์บริสุทธิ์ต่อหน้าชนอิสราเอล เจ้าจะไม่ได้พาชุมชนนี้เข้าสู่ดินแดนที่เรายกให้เขา”

13สถานที่นั้นได้ชื่อว่าเมรีบาห์20:13 แปลว่าโต้แย้งหรือวิวาทเพราะเป็นที่ซึ่งประชากรอิสราเอลโต้แย้งกับองค์พระผู้เป็นเจ้าและที่นั่นพระองค์ทรงสำแดงพระองค์เองว่าบริสุทธิ์ศักดิ์สิทธิ์ท่ามกลางพวกเขา

เอโดมไม่อนุญาตให้อิสราเอลผ่าน

14โมเสสส่งผู้สื่อสารจากคาเดชไปยังกษัตริย์เอโดมว่า

“ชาวอิสราเอลพี่น้องของท่านกล่าวเช่นนี้ว่า ท่านคงทราบเรื่องราวความทุกข์ยากลำบากของเราทั้งหมดแล้ว 15บรรพบุรุษของเราไปยังอียิปต์ และพวกเราก็อาศัยอยู่ที่นั่นหลายปี ชาวอียิปต์ข่มเหงรังแกเรากับบรรพบุรุษ 16แต่เมื่อเราร้องทูลองค์พระผู้เป็นเจ้าพระองค์ทรงได้ยินและทรงส่งทูตองค์หนึ่งนำเราออกมาจากอียิปต์

“บัดนี้เราตั้งค่ายพักอยู่ที่คาเดช ซึ่งเป็นเมืองชายแดนของท่าน 17โปรดอนุญาตให้เราผ่านแดน เราจะไม่ล่วงล้ำไร่นาหรือสวนองุ่นของท่าน เราจะไม่ดื่มน้ำจากบ่อของท่าน แต่จะไปตามทางหลวง และจะไม่หันไปทางซ้ายหรือทางขวาจนกว่าจะผ่านพ้นเขตแดนของท่าน”

18แต่เอโดมตอบว่า

“จงถอยไป ขืนฝ่าเข้ามาในพรมแดนของเรา เราจะยกพลออกไปโจมตีพวกเจ้าด้วยดาบ”

19ชนอิสราเอลตอบว่า

“พวกเราจะไปตามทางหลวง หากเราหรือสัตว์ของเราดื่มน้ำของท่าน เราจะจ่ายค่าตอบแทน เราเพียงแต่ต้องการเดินผ่านไปเท่านั้น ไม่มีอย่างอื่นเคลือบแฝง”

20แต่พวกเขาตอบว่า

“ห้ามผ่านเขตแดน”

จากนั้นเอโดมยกทัพใหญ่และมีอานุภาพมากออกมาต่อสู้กับพวกเขา 21ในเมื่อเอโดมไม่ยอมให้ผ่านเขตแดน อิสราเอลจึงเปลี่ยนเส้นทาง

อาโรนสิ้นชีวิต

22ชุมชนอิสราเอลทั้งหมดเดินทางจากคาเดชมายังภูเขาโฮร์ 23องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับโมเสสและอาโรนที่ภูเขาโฮร์ ใกล้ชายแดนเอโดมว่า 24“อาโรนจะตายไปอยู่กับบรรพบุรุษของเขา เขาจะไม่ได้เข้าไปในดินแดนที่เรายกให้ประชากรอิสราเอล เพราะเจ้าทั้งสองกบฏต่อคำสั่งของเราเรื่องน้ำที่เมรีบาห์ 25บัดนี้จงนำอาโรนและเอเลอาซาร์บุตรของเขาขึ้นไปบนภูเขาโฮร์ 26จงถอดเครื่องแต่งกายปุโรหิตของอาโรนและสวมให้เอเลอาซาร์ เพราะที่นั่นอาโรนจะตายไปอยู่กับบรรพบุรุษของเขา”

27โมเสสก็ปฏิบัติตามพระบัญชาขององค์พระผู้เป็นเจ้าคนทั้งสามขึ้นไปบนภูเขาโฮร์ด้วยกันต่อหน้าชุมนุมประชากรทั้งหมด 28โมเสสก็ถอดเครื่องแต่งกายปุโรหิตของอาโรนสวมให้เอเลอาซาร์ อาโรนสิ้นชีวิตบนยอดเขานั้น แล้วโมเสสกับเอเลอาซาร์จึงกลับลงมา 29ครั้นชุมนุมประชากรทั้งปวงทราบว่าอาโรนสิ้นชีวิตแล้ว วงศ์วานของอิสราเอลทั้งหมดก็ไว้อาลัยให้อาโรนอยู่สามสิบวัน

New Amharic Standard Version

ዘኍል 20:1-29

ከዐለት የፈለቀ ውሃ

1በመጀመሪያው ወር መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ወደ ጺን ምድረ በዳ መጥተው በቃዴስ ተቀመጡ፤ እዚያ ማርያም ሞተች፤ ተቀበረችም።

2በዚህ ጊዜ ለማኅበረ ሰቡ የሚሆን ውሃ አልነበረም፤ ሕዝቡም ሙሴንና አሮንን በመቃወም ተሰበሰቡ። 3ሙሴን ተጣሉት፤ እንዲህም አሉት፤ “ወንድሞቻችን በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት በሞቱ ጊዜ ምነው እኛም ያኔ ሞተን ባረፍነው ኖሮ! 4የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ማኅበረ ሰብ ወደዚህ ምድረ በዳ ያመጣችሁት ለምንድን ነው! ከነከብቶቻችን እዚሁ እንድናልቅ ነውን? 5ከግብፅ አውጥታችሁ እህል ወይም በለስ፣ ወይን ወይም ሮማን ወደሌለበት ወደዚህ ክፉ ቦታ ያመጣችሁንስ ለምንድን ነው? የሚጠጣ ውሃ እንኳ ይታጣ!”

6ሙሴና አሮን ከማኅበረ ሰቡ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሄደው በግንባራቸው ተደፉ፤ የእግዚአብሔርም (ያህዌ) ክብር ተገለጠላቸው። 7እግዚአብሔርም (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 8“በትሪቱን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን በአንድነት ሰብሰቡ፤ እነርሱም እያዩ ዐለቱን ተናገሩት፤ ዐለቱም ውሃ ያወጣል። አንተም ለማኅበረ ሰቡ ከዐለቱ ውሃ ታወጣላቸዋለህ፤ እነርሱና ከብቶቻቸውም ይጠጣሉ።”

9ስለዚህም ሙሴ ልክ እንደ ታዘዘው በትሩን ከእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ወሰደ። 10እርሱና አሮንም ማኅበሩን በዐለቱ ፊት አንድ ላይ ሰበሰቡ፤ ሙሴም፣ “እናንት ዐመፀኞች አድምጡ፤ ከዚህ ዐለት እኛ ለእናንተ ውሃ ማውጣት አለብን?” አላቸው። 11ከዚያም ሙሴ እጁን ዘርግቶ በበትሩ ዐለቱን ሁለት ጊዜ መታው፤ ውሃውም ተንዶለዶለ፤ ማኅበረ ሰቡና ከብቶቻቸውም ጠጡ።

12ነገር ግን እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴንና አሮንን፣ “በእስራኤላውያን ፊት እኔን ቅዱስ አድርጋችሁ ለማክበር ስላልታመናችሁብኝ ይህን ማኅበረ ሰብ ወደምሰጠው ምድር ይዛችሁ አትገቡም” አላቸው።

13እስራኤላውያን ከእግዚአብሔር (ያህዌ) ጋር የተጣሉበት፣ እርሱም ቅዱስ መሆኑን በመካከላቸው የገለጠበት ይህ የመሪባ20፥13 መሪባ ማለት መጣላት ማለት ነው። ውሃ ነበር።

ኤዶም እስራኤል እንዳያልፍ ከለከለ

14ሙሴ ከቃዴስ ለኤዶም ንጉሥ እንዲህ ሲል መልእክተኞች ላከ፤

“ወንድምህ እስራኤል የሚለው ይህ ነው፤ የደረሰብን መከራ ሁሉ ምን እንደ ሆነ አንተም ታውቃለህ። 15የቀድሞ አባቶቻችን ወደ ግብፅ ወረዱ፤ እኛም እዚያ ብዙ ዘመን ኖርን። ግብፃውያን እኛንም አባቶቻችንንም አሠቃዩን፤ 16ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) በጮኽን ጊዜ ግን ጩኸታችንን ሰማ፤ መልአክ ልኮም ከግብፅ አወጣን።

“አሁንም ያለነው እዚሁ ቃዴስ በግዛትህ ድንበር ላይ ባለችው ከተማ ነው። 17ስለዚህ በአገርህ እንድናልፍ እባክህን ፍቀድልን፤ በየትኛውም ዕርሻ ወይም የወይን ተክል ውስጥ አንገባም፤ ከየትኛውም ጕድጓድ ውሃ አንጠጣም። የንጉሡን አውራ ጐዳና ይዘን ከመጓዝ በስተቀር፣ ግዛትህን ዐልፈን እስክንሄድ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።”

18ኤዶም ግን እንዲህ ሲል መለሰ፤

“በዚህ በኩል አታልፉም፤ እናልፋለን የምትሉ ከሆነ በሰልፍ ወጥተን በሰይፍ እንመታችኋለን።”

19እስራኤላውያንም መልሰው፣

“አውራውን መንገድ ይዘን እንሄዳለን፤ እኛም ሆንን ከብቶቻችን የትኛውንም ውሃችሁን ከጠጣን ዋጋውን እንከፍላለን፤ በእግር ዐልፈን መሄድ ብቻ እንጂ ሌላ ምንም አንፈልግም።” አሏቸው።

20ኤዶምም እንደ ገና፣

“በዚህ ማለፍ አትችሉም” የሚል መልስ ሰጣቸው።

ከዚያም ኤዶም ብዙና ኀይለኛ የሆነ ሰራዊት አሰልፎ ሊወጋቸው ወጣ፤ 21ስለዚህ ኤዶም በግዛቱ ዐልፈው እንዳይሄዱ ስለ ከለከላቸው እስራኤላውያን ተመለሱ።

የአሮን መሞት

22መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ከቃዴስ ተነሥቶ ወደ ሖር ተራራ መጣ። 23እግዚአብሔርም (ያህዌ) በኤዶም ወሰን አጠገብ ባለው በሖር ተራራ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ 24“አሮን ወደ ወገኖቹ ይሰበሰባል፤ ሁለታችሁም በመሪባ ውሃ በትእዛዜ ላይ ዐምፃችኋልና ለእስራኤላውያን ወደምሰጣት ምድር አይገባም። 25አሮንንና ልጁን አልዓዛርን ወደ ሖር ተራራ ይዘሃቸው ውጣ። 26አሮን ወደ ወገኖቹ ስለሚሰበሰብ ልብሱን አውልቀህ ልጁን አልዓዛርን አልብሰው፤ አሮንም እዚያው ይሞታል።”

27ሙሴ እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው አደረገ፤ መላው ማኅበረ ሰብ እያያቸው ወደ ሖር ተራራ ወጡ። 28ሙሴም የአሮንን ልብስ አውልቆ ልጁን አልዓዛርን አለበሰው፤ አሮንም እዚያው ተራራው ጫፍ ላይ ሞተ። ከዚያም ሙሴና አልዓዛር ከተራራው ወረዱ፤ 29መላው ማኅበረ ሰብም አሮን መሞቱን በተረዳ ጊዜ፣ የእስራኤል ቤት በሙሉ ሠላሳ ቀን አለቀሰለት።