Deuteronomy 22 – NIVUK & NASV

New International Version – UK

Deuteronomy 22:1-30

1If you see your fellow Israelite’s ox or sheep straying, do not ignore it but be sure to take it back to its owner. 2If they do not live near you or if you do not know who owns it, take it home with you and keep it until they come looking for it. Then give it back. 3Do the same if you find their donkey or cloak or anything else they have lost. Do not ignore it.

4If you see your fellow Israelite’s donkey or ox fallen on the road, do not ignore it. Help the owner to get it to its feet.

5A woman must not wear men’s clothing, nor a man wear women’s clothing, for the Lord your God detests anyone who does this.

6If you come across a bird’s nest beside the road, either in a tree or on the ground, and the mother is sitting on the young or on the eggs, do not take the mother with the young. 7You may take the young, but be sure to let the mother go, so that it may go well with you and you may have a long life.

8When you build a new house, make a parapet around your roof so that you may not bring the guilt of bloodshed on your house if someone falls from the roof.

9Do not plant two kinds of seed in your vineyard; if you do, not only the crops you plant but also the fruit of the vineyard will be defiled.22:9 Or be forfeited to the sanctuary

10Do not plough with an ox and a donkey yoked together.

11Do not wear clothes of wool and linen woven together.

12Make tassels on the four corners of the cloak you wear.

Marriage violations

13If a man takes a wife and, after sleeping with her, dislikes her 14and slanders her and gives her a bad name, saying, ‘I married this woman, but when I approached her, I did not find proof of her virginity,’ 15then the young woman’s father and mother shall bring to the town elders at the gate proof that she was a virgin. 16Her father will say to the elders, ‘I gave my daughter in marriage to this man, but he dislikes her. 17Now he has slandered her and said, “I did not find your daughter to be a virgin.” But here is the proof of my daughter’s virginity.’ Then her parents shall display the cloth before the elders of the town, 18and the elders shall take the man and punish him. 19They shall fine him a hundred shekels22:19 That is, about 1.2 kilograms of silver and give them to the young woman’s father, because this man has given an Israelite virgin a bad name. She shall continue to be his wife; he must not divorce her as long as he lives.

20If, however, the charge is true and no proof of the young woman’s virginity can be found, 21she shall be brought to the door of her father’s house and there the men of her town shall stone her to death. She has done an outrageous thing in Israel by being promiscuous while still in her father’s house. You must purge the evil from among you.

22If a man is found sleeping with another man’s wife, both the man who slept with her and the woman must die. You must purge the evil from Israel.

23If a man happens to meet in a town a virgin pledged to be married and he sleeps with her, 24you shall take both of them to the gate of that town and stone them to death – the young woman because she was in a town and did not scream for help, and the man because he violated another man’s wife. You must purge the evil from among you.

25But if out in the country a man happens to meet a young woman pledged to be married and rapes her, only the man who has done this shall die. 26Do nothing to the woman; she has committed no sin deserving death. This case is like that of someone who attacks and murders a neighbour, 27for the man found the young woman out in the country, and though the betrothed woman screamed, there was no-one to rescue her.

28If a man happens to meet a virgin who is not pledged to be married and rapes her and they are discovered, 29he shall pay her father fifty shekels22:29 That is, about 575 grams of silver. He must marry the young woman, for he has violated her. He can never divorce her as long as he lives.

30A man is not to marry his father’s wife; he must not dishonour his father’s bed.22:30 In Hebrew texts this verse (22:30) is numbered 23:1.

New Amharic Standard Version

ዘዳግም 22:1-30

1የወንድምህ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ብታየው፣ ወደ እርሱ መልሰህ አምጣለት እንጂ ዝም ብለህ አትለፈው፤ 2ወንድምህ በአቅራቢያህ ባይኖር፣ ወይም የማን መሆኑን የማታውቅ ከሆነ፣ ባለቤቱ ፈልጎት እስኪመጣ ድረስ፣ ወደ ቤትህ ወስደህ ከአንተ ዘንድ አቈየው፤ ከዚያም መልሰህ ስጠው። 3የወንድምህን አህያ ወይም ልብስ ወይም የጠፋበትን ማናቸውንም ነገር ስታገኝ እንደዚሁ አድርግ፤ በቸልታ አትለፈው።

4የወንድምህ አህያ ወይም በሬ መንገድ ላይ ወድቆ ብታየው፣ በእግሩ እንዲቆምለት ርዳው እንጂ ዐልፈኸው አትሂድ።

5ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፤ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ፤ እንዲህ የሚያደርገውን ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ይጸየፈዋልና።

6በመንገድ ስታልፍ፣ አንዲት ወፍ ጫጩቶቿን ወይም ዕንቁላሎቿን የታቀፈችበትን ጐጆ በዛፍ ወይም በመሬት ላይ ብታገኝ፣ እናቲቱን ከነጫጩቶቿ አትውሰድ፤ 7ጫጩቶቿን መውሰድ ትችላለህ፤ እናቲቱን ግን መልካም እንዲሆንልህና ዕድሜህም እንዲረዝም ልቀቃት፤

8አዲስ ቤት በምትሠራበት ጊዜ፣ ከጣራው ላይ ሰው ወድቆ በቤትህ ላይ የደም በደል እንዳታመጣ፣ በጣራው ዙሪያ መከታ አብጅለት።

9በወይን ተክል ቦታህ ውስጥ ሁለት ዐይነት ዘር አትዝራ፤ ይህን ካደረግህ፣ የዘራኸው ሰብል ብቻ ሳይሆን፣ የወይን ፍሬህም ይጠፋል።

10በሬና አህያ በአንድ ላይ ጠምደህ አትረስ።

11ሱፍና በፍታ አንድ ላይ ተፈትሎ የተሠራ ልብስ አትልበስ።

12በምትለብሰው ልብስ ላይ በአራቱ ማእዘኖች ዘርፍ አድርግ።

ጋብቻን በንጽሕና ስለ መጠበቅ

13አንድ ወንድ ሚስት አግብቶ አብሯት ከተኛ በኋላ ቢጠላት፣ 14ስሟንም በማጥፋት፣ “ይህችን ሴት አገባኋት፤ ዳሩ ግን በደረስሁባት ጊዜ ድንግልናዋን አላገኘሁም” ቢል፣ 15የልጂቱ አባትና እናት ድንግልናዋን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘው በከተማዪቱ በር ወዳሉት አለቆች ይምጡ። 16የልጂቱም አባት ለአለቆቹ እንዲህ ይበል፤ “ልጄን ለዚህ ሰው ዳርሁለት፤ እርሱ ግን ጠላት፤ 17ስሟንም በማጥፋት፣ ‘ልጅህን ከነድንግልናዋ አላገኘኋትም’ ብሎኛል፤ ነገር ግን የልጄ ድንግልና ማረጋገጫ ይኸውላችሁ፤” ከዚያም ወላጆቿ የደሙን ሸማ በከተማዪቱ አለቆች ፊት ይዘርጉት። 18ከዚያም በኋላ አለቆቹ ሰውየውን ይዘው ይቅጡት፤ 19ይህ ሰው የአንዲት እስራኤላዊት ድንግል ስም አጥፍቷልና አንድ መቶ ሰቅል22፥19 ወደ አንድ ኪሎ ግራም ነው። ብር ያስከፍሉት፤ ገንዘቡንም ለልጂቱ አባት ይስጡት፤ ሴቲቱም ሚስቱ ሆና ትኖራለች፤ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም።

20ሆኖም ክሱ እውነት ሆኖ ሴቲቱ ድንግል ለመሆኗ ምንም ማረጋገጫ ማቅረብ ካልተቻለ፣ 21ገና በአባቷ ቤት ሳለች በማመንዘር በእስራኤል ውስጥ ወራዳ ተግባር ፈጽማለችና ወደ አባቷ ቤት ደጃፍ ያምጧት፤ እዚያም የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሯት። ክፉውን ከመካከልህ ማስወገድ አለብህ።

22አንድ ሰው፣ ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ፣ አብሯት የተኛው ሰውና ሴቲቱ ሁለቱም ይገደሉ፤ ክፉውን ከእስራኤል ማስወገድ አለብህ።

23አንድ ሰው የታጨች ድንግል በከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእርሷ ጋር ቢተኛ፣ 24ልጃገረዲቱ በከተማ ውስጥ እያለች አስጥሉኝ ብላ ስላልጮኸች፣ ሰውየውም የሌላን ሰው ሚስት አስገድዶ ስለ ደፈረ፣ ሁለቱንም ወደ ከተማ ደጃፍ ወስዳችሁ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሯቸው። ክፉውን ከመካከልህ ማስወገድ አለብህ።

25ነገር ግን አንድ ሰው የታጨችውን ልጃገረድ ከከተማ ውጭ አግኝቶ በማስገደድ ቢደፍራት፣ ይህን ድርጊት የፈጸመው ሰው ብቻ ይገደል። 26በልጃገረዲቱ ላይ ግን ምንም አታድርጉባት፤ ለሞት የሚያበቃ ኀጢአት ምንም አልሠራችም፤ ይህ ዐይነቱ ጕዳይ፣ አደጋ ጥሎ ባልንጀራውን ከሚገድል ሰው አድራጎት ጋር የሚመሳሰል ነው። 27ምክንያቱም ሰውየው የታጨችውን ልጃገረድ ከከተማ ውጭ ስላገኛትና ብትጮኽም እንኳ ለርዳታ የደረሰላት ማንም ሰው ስላልነበር ነው።

28አንድ ሰው ያልታጨች ልጃገረድ አግኝቶ በማስገደድ ቢደርስባትና ቢጋለጡ፣ 29ሰውየው ለልጅቷ አባት አምሳ ሰቅል22፥29 ወደ 0.6 ኪሎ ግራም ነው። ብር ይክፈል፤ ልጃገረዲቱን አስገድዶ ደፍሯታልና፣ እርሷን ማግባት አለበት፤ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም።

30አንድ ሰው የአባቱን ሚስት ማግባት የለበትም፤ የአባቱንም መኝታ አያርክስ።