Esther 6 – NIV & NASV

New International Version

Esther 6:1-14

Mordecai Honored

1That night the king could not sleep; so he ordered the book of the chronicles, the record of his reign, to be brought in and read to him. 2It was found recorded there that Mordecai had exposed Bigthana and Teresh, two of the king’s officers who guarded the doorway, who had conspired to assassinate King Xerxes.

3“What honor and recognition has Mordecai received for this?” the king asked.

“Nothing has been done for him,” his attendants answered.

4The king said, “Who is in the court?” Now Haman had just entered the outer court of the palace to speak to the king about impaling Mordecai on the pole he had set up for him.

5His attendants answered, “Haman is standing in the court.”

“Bring him in,” the king ordered.

6When Haman entered, the king asked him, “What should be done for the man the king delights to honor?”

Now Haman thought to himself, “Who is there that the king would rather honor than me?” 7So he answered the king, “For the man the king delights to honor, 8have them bring a royal robe the king has worn and a horse the king has ridden, one with a royal crest placed on its head. 9Then let the robe and horse be entrusted to one of the king’s most noble princes. Let them robe the man the king delights to honor, and lead him on the horse through the city streets, proclaiming before him, ‘This is what is done for the man the king delights to honor!’ ”

10“Go at once,” the king commanded Haman. “Get the robe and the horse and do just as you have suggested for Mordecai the Jew, who sits at the king’s gate. Do not neglect anything you have recommended.”

11So Haman got the robe and the horse. He robed Mordecai, and led him on horseback through the city streets, proclaiming before him, “This is what is done for the man the king delights to honor!”

12Afterward Mordecai returned to the king’s gate. But Haman rushed home, with his head covered in grief, 13and told Zeresh his wife and all his friends everything that had happened to him.

His advisers and his wife Zeresh said to him, “Since Mordecai, before whom your downfall has started, is of Jewish origin, you cannot stand against him—you will surely come to ruin!” 14While they were still talking with him, the king’s eunuchs arrived and hurried Haman away to the banquet Esther had prepared.

New Amharic Standard Version

አስቴር 6:1-14

መርዶክዮስ ከፍ ከፍ አለ

1በዚያች ሌሊት ንጉሡ እንቅልፍ መተኛት አልቻለም። ስለዚህ በዘመነ መንግሥቱ የተመዘገበው የታሪክ መጽሐፍ ቀርቦ እንዲነበብለት አዘዘ። 2በዚያም በሩን ከሚጠብቁት ከንጉሡ የጦር አዛዦች ሁለቱ፣ ገበታና ታራ ንጉሥ ጠረክሲስን ለመግደል አሢረው እንደ ነበርና ይህንም መርዶክዮስ እንደ ተናገረ ተጽፎ ተገኘ።

3ንጉሡም፣ “ታዲያ ይህን በማድረጉ መርዶክዮስ ያገኘው ክብርና ማዕረግ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ።

የቅርብ አገልጋዮቹም፣ “ምንም አልተደረገለትም” ብለው መለሱ።

4ንጉሡም፣ “በአደባባዩ ማን አለ?” ሲል ጠየቀ። በዚህ ጊዜ ሐማ በተከለው ዕንጨት ላይ መርዶክዮስ ይሰቀል ዘንድ ለንጉሡ ለመናገር በውጭ በኩል ወደሚገኘው የቤተ መንግሥቱ አደባባይ ገና መድረሱ ነበር።

5የቅርብ አገልጋዮቹም፣ “እነሆ፤ ሐማ በአደባባዩ ቆሟል” አሉት።

ንጉሡም፣ “ግባ በሉት” ብሎ አዘዘ።

6ሐማ በገባ ጊዜ ንጉሡ፣ “ንጉሥ ሊያከብረው ለወደደው ሰው ምን ሊደረግለት ይገባል?” ሲል ጠየቀው።

በዚህ ጊዜ ሐማ፣ “ንጉሡ ከእኔ ይልቅ የሚያከብረው ማን አለ?” ሲል በልቡ ዐሰበ። 7ስለዚህ ለንጉሡ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ንጉሡ ሊያከብረው ለወደደው ሰው፣ 8ንጉሡ የሚጐናጸፈው ልብሰ መንግሥት፣ ንጉሡም የሚቀመጥበትና የንጉሡን ዘውድ በራሱ ላይ ያደረገ ፈረስ ይምጣለት። 9ከዚያም ልብሱና ፈረሱ እጅግ ከከበሩት ከንጉሡ ልዑላን መሳፍንት በአንዱ እጅ ይሰጥለት። ንጉሡ ሊያከብረው የወደደውን ሰው ያልብሱት፤ በፈረሱም ላይ አስቀመጠውም በከተማዪቱ ዋና ዋና መንገዶች ላይ እየመሩ፣ ‘ንጉሡ ሊያከብረው ለሚወድደው ሰው ይህ ተደርጎለታል’ ይበሉ።”

10ንጉሡም ሐማን፣ “በል ፈጥነህ ሂድ፤ ልብሱንና ፈረሱን ውሰድ፤ በንጉሡ በር ላይ ለሚቀመጠው ለአይሁዳዊው ለመርዶክዮስም ልክ እንዳልኸው አድርግለት፤ ከተናገርኸውም አንዳች ነገር እንዳይጐድል” ሲል አዘዘው።

11ስለዚህ ሐማ ልብሱንና ፈረሱን ወስዶ መርዶክዮስን አለበሰው፤ በዋና ዋና መንገዶች ላይ እየመራም፣ “ንጉሥ ሊያከብረው ለሚወድደው ሰው ይህ ተደርጎለታል” እያለ በፊቱ ያውጅ ነበር።

12ከዚያም በኋላ መርዶክዮስ ወደ ንጉሡ በር ተመለሰ፤ ሐማ ግን ዐዝኖና ራሱን ተከናንቦ በጥድፊያ ወደ ቤቱ ሄደ። 13የደረሰበትንም ሁሉ ለሚስቱ ለዞሳራና ለወዳጆቹ ሁሉ ነገራቸው።

አማካሪዎቹና ሚስቱ ዞሳራም፣ “በፊቱ መውደቅ የጀመርህለት መርዶክዮስ ዘሩ ከአይሁድ ወገን ከሆነ፣ ልትቋቋመው አትችልም፤ ያለ ጥርጥር ትጠፋለህ” አሉት። 14ከእርሱ ጋር በመነጋገር ላይ ሳሉ፣ የንጉሡ ጃንደረቦች ደርሰው ሐማን አስቴር ወዳዘጋጀችው ግብዣ አጣደፉት።