إرميا 6 – NAV & NASV

Ketab El Hayat

إرميا 6:1-30

حصار أورشليم

1«لُوذُوا بِالْنَّجَاةِ يَا ذُرِّيَّةَ بِنْيَامِينَ، وَاهْرُبُوا مِنْ وَسَطِ أُورُشَلِيمَ. انْفُخُوا بِالْبُوقِ فِي تَقُوعَ، وَأَشْعِلُوا عَلَمَ نَارٍ عَلَى بَيْتِ هَكَّارِيمَ، لأَنَّ الشَّرَّ قَدْ أَقْبَلَ مِنَ الشِّمَالِ لِيَعِيثَ فِي الأَرْضِ خَرَاباً. 2هَا أَنَا أُهْلِكُ أُورُشَلِيمَ الْجَمِيلَةَ الْمُتْرَفَةَ ابْنَةَ صِهْيَوْنَ، 3فَيَحُلُّ بِها الرُّعَاةُ مَعَ قُطْعَانِهِمْ، وَيَضْرِبُونَ حَوْلَهَا خِيَامَهُمْ، وَيَرْعَى كُلٌّ مِنْهُمْ حَيْثُ نَزَلَ. 4أَعِدُّوا عَلَيْهَا حَرْباً. قُومُوا نُهَاجِمُهَا عِنْدَ الظَّهِيرَةِ. وَيْلٌ لَنَا فَقَدْ مَالَ النَّهَارُ وَانْتَشَرَتْ ظِلالُ الْمَسَاءِ. 5هُبُّوا لِنَهْجُمَ فِي اللَّيْلِ وَنَهْدِمَ قُصُورَهَا».

6لأَنَّ هَذَا مَا يُعْلِنُهُ الرَّبُّ الْقَدِيرُ: «اقْطَعُوا الشَّجَرَ، وَأَقِيمُوا مِتْرَسَةً حَوْلَ أُورُشَلِيمَ، إِذْ يَجِبُ أَنْ تُعَاقَبَ هَذِهِ الْمَدِينَةُ، لأَنَّ دَاخِلَهَا مُفْعَمٌ بِالظُّلْمِ. 7وَكَمَا تُنْبِعُ الْعَيْنُ مِيَاهَهَا كَذَلِكَ هِيَ تُنْبِعُ شَرَّهَا. يَتَرَدَّدُ فِي أَرْجَائِهَا الظُّلْمُ وَيَعُمُّهَا السَّلْبُ، وَأَمَامِي دَائِماً مَرَضٌ وَبَلايَا. 8فَاحْذَرِي يَا أُورُشَلِيمُ لِئَلَّا أَجْفُوَكِ وَأَجْعَلَكِ مُوْحِشَةً وَأَرْضاً مَهْجُورَةً».

9وَهَذَا مَا يُعْلِنُهُ الرَّبُّ الْقَدِيرُ: «لِيَجْمَعُوا بِدِقَّةٍ لِقَاطَ بَقِيَّةِ إِسْرَائِيلَ كَمَا يَجْمَعُونَ لِقَاطَ كَرْمَةٍ. رُدَّ يَدَكَ إِلَى الأَغْصَانِ ثَانِيَةً كَلاقِطِ الْعِنَبِ». 10لِمَنْ أَتَحَدَّثُ وَأُنْذِرُ حَتَّى يَسْمَعُوا؟ انْظُرْ! إِنَّ آذَانَهُمْ صَمَّاءُ فَلا يَسْمَعُونَ، وَكَلِمَةَ الرَّبِّ مَثَارُ خِزْيٍ لَهُمْ فَلا يُسَرُّونَ بِها. 11لِذَلِكَ امْتَلَأْتُ مِنْ سَخَطِ الرَّبِّ وَأَعْيَانِي كَبْتُهُ. «أَسْكُبُهُ عَلَى الأَوْلادِ فِي الطَّرِيقِ وَعَلَى الشُّبَّانِ الْمُجْتَمِعِينَ فِي مَجَالِسِهِمْ، فَيُصِيبُ الرَّجُلَ وَزَوْجَتَهُ وَالشَّيْخَ وَالطَّاعِنَ فِي السِّنِّ. 12وَتَتَحَوَّلُ بُيُوتُهُمْ وَحقُولُهُمْ لآخَرِينَ، وَكَذَلِكَ نِسَاؤُهُمْ، لأَنِّي أَبْسُطُ يَدِي ضِدَّ سُكَّانِ الأَرْضِ» يَقُولُ الرَّبُّ 13«لأَنَّهُمْ جَمِيعاً، صِغَارَهُمْ وَكِبَارَهُمْ، مُوْلَعُونَ بالرِّبْحِ الْحَرَامِ. حَتَّى النَّبِيُّ وَالْكَاهِنُ يَرْتَكِبَانِ الزُّورَ فِي أَعْمَالِهِمَا. 14يُعَالِجُونَ جِرَاحَ شَعْبِي بِاسْتِخْفَافٍ قَائِلِينَ: ’سَلامٌ، سَلامٌ.‘ فِي حِينِ لَا يُوْجَدُ سَلامٌ. 15هَلْ خَجِلُوا لأَنَّهُمُ اقْتَرَفُوا الرِّجْسَ؟ كَلا! لَمْ يَخْزَوْا قَطُّ وَلَمْ يَعْرِفُوا الْخَجَلَ، لِذَلِكَ سَيَسْقُطُونَ بَيْنَ السَّاقِطِينَ، وَحِينَ أُعَاقِبُهُمْ يُطَوَّحُ بِهِمْ».

16وَهَذَا مَا يُعْلِنُهُ الرَّبُّ: «قِفُوا فِي الطُّرُقَاتِ وَانْظُرُوا، وَاسْأَلُوا عَنِ الْمَسَالِكِ الصَّالِحَةِ الْقَدِيمَةِ وَاطْرُقُوهَا، فَتَجِدُوا رَاحَةً لِنُفُوسِكُمْ. وَلَكِنَّكُمْ قُلْتُمْ: ’لَنْ نَسِيرَ فِيهَا.‘ 17فَأَقَمْتُ عَلَيْكُمْ رُقَبَاءَ قَائِلاً: اسْمَعُوا دَوِيَّ الْبُوقِ. وَلَكِنَّكُمْ قُلْتُمْ: ’لَنْ نَسْمَعَ!‘ 18لِذَلِكَ اسْمَعُوا أَيُّهَا الأُمَمُ، وَاعْلَمِي أَيَّتُهَا الْجَمَاعَةُ مَاذَا يَحُلُّ بِهِمْ. 19اسْمَعِي أَيَّتُهَا الأَرْضُ وَانْظُرِي، لأَنِّي جَالِبٌ شَرّاً عَلَى هَذَا الشَّعْبِ عِقَاباً لَهُمْ عَلَى أَفْكَارِهِمِ الأَثِيمَةِ، لأَنَّهُمْ لَمْ يُطِيعُوا كَلِمَاتِي وَتَنَكَّرُوا لِشَرِيعَتِي. 20لأَيِّ غَرَضٍ يَصْعَدُ إِلَيَّ الْبَخُورُ مِنْ شَبَا، وَقَصَبُ الطِّيبِ مِنْ أَرْضٍ نَائِيَةٍ؟ مُحْرَقَاتُكُمْ مَرْفُوضَةٌ، وَتَقْدِمَاتُكُمْ لَا تَسُرُّنِي». 21لِذَلِكَ يُعْلِنُ الرَّبُّ: «هَا أَنَا أُقِيمُ لِهَذَا الشَّعْبِ مَعَاثِرَ يَتَعَثَّرُ بِها الآبَاءُ وَالأَبْنَاءُ مَعاً، وَيَهْلِكُ بِها الْجَارُ وَصَدِيقُهُ».

22«انْظُرُوا، هَا شَعْبٌ زَاحِفٌ مِنَ الشِّمَالِ، وَأُمَّةٌ عَظِيمَةٌ تَهُبُّ مِنْ أَقَاصِي الأَرْضِ، 23تَسَلَّحَتْ بِالْقَوْسِ وَالرُّمْحِ، وَهِيَ قَاسِيَةٌ لَا تَرْحَمُ. جَلَبَتُهَا كَهَدِيرِ الْبَحْرِ وَهِيَ مُقْبِلَةٌ عَلَى صَهَوَاتِ الْخَيْلِ. قَدِ اصْطَفَّتْ كَإِنْسَانٍ وَاحِدٍ لِمُحَارَبَتِكِ يَا أُورُشَلِيمُ». 24سَمِعْنَا أَخْبَارَهُمُ الْمُرْعِبَةَ فَدَبَّ الضَّعْفُ فِي أَيْدِينَا، وَتَوَلّانَا كَرْبٌ وَأَلَمٌ كَأَلَمِ امْرَأَةٍ تُعَانِي مِنَ الْمَخَاضِ. 25لَا تَخْرُجُوا إِلَى الْحَقْلِ وَلا تَمْشُوا فِي الطَّرِيقِ، فَلِلْعَدُوِّ سَيْفٌ، وَالْهَوْلُ مُحْدِقٌ مِنْ كُلِّ جِهَةٍ.

26فَيَا أُورُشَلِيمُ ارْتَدِي الْمُسُوحَ وَتَمَرَّغِي فِي الرَّمَادِ، وَنُوحِي كَمَنْ يَنُوحُ عَلَى وَحِيدِهِ، وَانْتَحِبِي نَحِيباً مُرّاً، لأَنَّ الْمُدَمِّرَ يَنْقَضُّ عَلَيْنَا فَجْأَةً. 27«إِنِّي أَقَمْتُكَ مُمْتَحِناً لِلْمَعْدِنِ، وَجَعَلْتُ شَعْبِي مَادَّةَ خَامٍ لِكَيْ تَعْرِفَ طُرُقَهُمْ وَتَفْحَصَهَا. 28فَكُلُّهُمْ عُصَاةٌ مُتَمَرِّدُونَ سَاعُونَ فِي النَّمِيمَةِ. هُمْ نُحَاسٌ وَحَدِيدٌ وَكُلُّهُمْ فَاسِدُونَ. 29لَشَدَّ مَا تُضْرِمُ رِيحُ المِنْفَاخِ الشَّدِيدَةُ النَّارَ فَتَلْتَهِمُ الرَّصَاصَ وَلَكِنْ كَمَا يَتَعَذَّرُ تَنْقِيَتُهُ مِنَ الزَّغَلِ كَذَلِكَ يَتَعَذَّرُ فَصْلُ الأَشْرَارِ. 30وَهُمْ يُدْعَوْنَ حُثَالَةَ الْفِضَّةِ الْمَرْذُولَةِ، لأَنَّ الرَّبَّ قَدْ رَفَضَهُمْ».

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 6:1-30

የኢየሩሳሌም መከበብ

1“እናንት የብንያም ልጆች፤ ክፉ ነገር፣

ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ድንገት ይመጣልና፣

ከኢየሩሳሌም ሸሽታችሁ አምልጡ፤

በቴቁሔ መለከትን ንፉ፤

በቤትሐካሪም ላይ ምልክት ከፍ

አድርጋችሁ አሳዩ።

2ውብና ሽሙንሙን የሆነችዋን፣

የጽዮንን ሴት ልጅ አጠፋታለሁ።

3እረኞች መንጎቻቸውን ይዘው ይመጡባታል፤

ድንኳናቸውን በዙሪያዋ ይተክላሉ፤

እያንዳንዳቸውም በየአቅጣጫቸው መንጋቸውን ያሰማራሉ።

4“በእርሷ ላይ ጦርነት ዐውጁ፤

ተነሡ በቀትር አደጋ እንጣልባት፤

ወይ ጉድ! ቀኑ እኮ መሸብን!

ጥላው ረዘመ።

5እንግዲህ ተነሡ በሌሊት እናጥቃት፤

ምሽጎቿንም እንደምስስ!”

6የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ዛፎቹን ቍረጡ፤

በኢየሩሳሌም ዙሪያ የዐፈር ድልድል ሥሩ።

ይህች ከተማ ቅጣት ይገባታል፤

ግፍን ተሞልታለችና።

7የውሃ ጕድጓድ ውሃ እንደሚያመነጭ፣

እርሷም እንዲሁ ክፋቷን ታፈልቃለች።

ዐመፅና ጥፋት በውስጧ ይስተጋባል፤

ሕመሟና ቍስሏ ዘወትር ይታየኛል።

8ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተጠንቀቂ፤

አለዚያ ከአንቺ ዘወር እላለሁ፤

ማንም ሊኖርባት እስከማይችል ድረስ፣

ምድርሽን ባዶ አደርጋለሁ።”

9የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“የወይን ፍሬ ተሟጦ እንደሚቃረም፣

ከእስራኤል የተረፉትን እንዲሁ ይቃርሟቸው።

ወይን ለቃሚ እንደሚለቅም፣

እጅህን ወደ ቅርንጫፎቹ ደጋግመህ ዘርጋ።”

10ለማን ልናገር? ማንን ላስጠንቅቅ?

ማንስ ይሰማኛል?

እነሆ፣ ጆሮዎቻቸው አልተገረዙምና፣6፥10 ወይም ጆሮዎቻቸው ተደፍነዋል

መስማት አይችሉም።

በእግዚአብሔር ቃል ይሣለቃሉ፤

ደስም አይሰኙበትም።

11በእነርሱ ላይ በእግዚአብሔር ቍጣ ተሞልቻለሁ፤

በውስጤም ልይዘው አልቻልሁም።

“መንገድ ላይ በሚገኙ ሕፃናት፣

በተሰበሰቡ ወጣቶችም ላይ አፍስሰው፤

ባልም ሚስትም፣

ያረጁና የጃጁም አያመልጡም።

12በምድሪቱ በሚኖሩት ላይ

እጄን በምዘረጋበት ጊዜ፣

ዕርሻቸውና ሚስቶቻቸው ሳይቀሩ፣

ቤቶቻቸው ለሌሎች ይሆናሉ፤”

ይላል እግዚአብሔር

13“ከትንሹ እስከ ትልቁ ሰው፣

ሁሉም ለጥቅም የሚስገበገቡ ናቸው፤

ነቢያቱም ካህናቱም ሳይቀሩ፣

ሁሉም ያጭበረብራሉ።

14የሕዝቤን ቍስል እንደ ቀላል ቈጠሩ፣

እንዲፈወስም ተገቢውን እንክብካቤ አላደረጉለትም፤

ሰላምም ሳይኖር፣

‘ሰላም፣ ሰላም’ ይላሉ።

15ስለ ጸያፉ ተግባራቸው ዐፍረዋል እንዴ?

ኧረ ጨርሶ ዕፍረት የላቸውም!

ዕፍረት ምን እንደ ሆነ እንኳ አያውቁም፤

ስለዚህ ከሚወድቁት ጋር ይወድቃሉ፤

በምቀጣቸውም ጊዜ ይዋረዳሉ፤”

ይላል እግዚአብሔር

16እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“መንታ መንገድ ላይ ቁሙ፣ ተመልከቱም፤

መልካሟን፣ የጥንቷን መንገድ ጠይቁ፤

በእርሷም ላይ ሂዱ።

ለነፍሳችሁ ዕረፍት ታገኛላችሁ፤

እናንተ ግን፣ ‘በእርሷ አንሄድም’ አላችሁ።

17ጠባቂዎችን አቆምሁላችሁ፤

‘የመለከትንም ድምፅ ስሙ’ አልኋችሁ፤

እናንተ ግን፣ ‘አንሰማም’ አላችሁ።

18እንግዲህ ሕዝቦች ሆይ ስሙ፤

እናንተም ምስክሮች ምን

እንደሚገጥማቸው አስተውሉ።

19ምድር ሆይ፤ ስሚ፤

ቃሌን ስላላደመጡ፣

ሕጌንም ስለ ናቁ፣

በዚህ ሕዝብ ላይ የሐሳባቸውን ውጤት፣

ጥፋትን አመጣባቸዋለሁ።

20ዕጣን ከሳባ ምድር፣

ጣፋጩ ቅመም ከሩቅ አገር ቢመጣ ምን ይጠቅመኛል?

የሚቃጠል መሥዋዕታችሁን አልቀበልም፤

ሌላውም መሥዋዕታችሁ ደስ አያሰኙኝም።”

21ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“በዚህ ሕዝብ ፊት መሰናክልን አስቀምጣለሁ፤

አባቶችና ወንዶች ልጆች በአንድነት ይደናቀፉበታል፤

ጎረቤቶችና ባልንጀሮችም ይጠፋሉ።”

22እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“እነሆ፤ ሰራዊት፣

ከሰሜን ምድር እየመጣ ነው፤

ከምድር ዳርቻም፣

ታላቅ ሕዝብ እየተነሣሣ ነው።

23ቀስትና ጦር ይዘዋል፤

ጨካኞችና ምሕረት የለሽ ናቸው፤

ፈረሶቻቸውን ሲጋልቡ፣

ድምፃቸው እንደ ተናወጠ ባሕር ነው፤

የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ለሰልፍ የታጠቁ ሆነው፣

ሊወጉሽ ይመጣሉ።”

24ስለ እነርሱ ወሬ ደርሶናል፤

ክንዶቻችንም ዝለዋል፤

ጭንቀት ይዞናል፤ እንደምታምጥም

ሴት ሆነናል።

25ጠላት ሰይፍ ታጥቋል፤

በየቦታውም ሽብር ሞልቷል፤

ስለዚህ ወደ ውጭ አትውጡ፤

በየመንገዱ አትዘዋወሩ።

26የሕዝቤ ልጅ ሆይ፤ ማቅ ልበሺ፤

በዐመድም ላይ ተንከባለዪ፤

አንድያ ልጁን እንዳጣ ሰው፣

ምርር ብለሽ አልቅሺ፤

አጥፊው በድንገት፣

በላያችን ይመጣልና።

27“ብረት እንደሚፈተን፣

የሕዝቤን መንገድ፣

አካሄዳቸውንም እንድትፈትን፣

አንተን ፈታኝ አድርጌሃለሁ።

28ሁሉም ለማማት የሚዞሩ፣

ድድር ዐመፀኞች፣

ናስና ብረት የሆኑ፣

ምግባረ ብልሹዎች ናቸው።

29ርሳሱን ለማቅለጥ፣

ወናፉ በብርቱ አናፋ፤

ግን ምን ይሆናል፣ ከንቱ ልፋት ነው፤

ክፉዎች ጠርገው አልወጡምና።

30እግዚአብሔር ንቋቸዋልና፣

የተናቀ ብር ተብለው ይጠራሉ።”