2 ዜና መዋዕል 27 – NASV & KJV

New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 27:1-9

የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአታም

27፥1-47-9 ተጓ ምብ – 2ነገ 15፥33-38

1ኢዮአታም በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ሲሆን፣ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ። እናቱም ኢየሩሳ የተባለች የሳዶቅ ልጅ ነበረች። 2አባቱ ዖዝያን እንዳደረገው ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ይሁን እንጂ እንደ አባቱ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አልገባም። ሕዝቡም በበደሉ እንደ ገፋበት ነበር። 3ኢዮአታም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የላይኛውን በር እንደ ገና ሠራው፤ በዖፌልም በኩል ባለው ቅጥር ላይ፣ አያሌ የማሻሻል ተግባር አከናወነ። 4በይሁዳ ኰረብታዎች ላይ ከተሞችን፣ ደን በለበሱ ስፍራዎችም ምሽጎችንና ማማዎችን ሠራ።

5ኢዮአታም የአሞናውያንን ንጉሥ ወግቶ ድል አደረጋቸው። በዚያ ዓመትም አሞናውያን አንድ መቶ መክሊት27፥5 3.4 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው። ጥሬ ብር፣ ዐሥር ሺሕ ቆሮስ27፥5 2,200 ኪሎ ሊትር ያህል ነው። ስንዴና ዐሥር ሺሕ ቆሮስ ገብስ ገበሩለት። አሞናውያን በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት ይህንኑ ግብር አመጡለት።

6ኢዮአታም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት በታማኝነት ስለ ተመላለሰ፣ እየበረታ ሄደ።

7በኢዮአታም ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባር፣ ያደረጋቸው ጦርነቶችና የሠራቸው ነገሮች በሙሉ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፏል። 8እርሱም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ። 9ኢዮአታም እንደ አባቶቹ ሁሉ አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ልጁ አካዝም በእርሱ ፈንታ ነገሠ።

King James Version

2 Chronicles 27:1-9

1Jotham was twenty and five years old when he began to reign, and he reigned sixteen years in Jerusalem. His mother’s name also was Jerushah, the daughter of Zadok. 2And he did that which was right in the sight of the LORD, according to all that his father Uzziah did: howbeit he entered not into the temple of the LORD. And the people did yet corruptly. 3He built the high gate of the house of the LORD, and on the wall of Ophel he built much.27.3 Ophel: or, the tower 4Moreover he built cities in the mountains of Judah, and in the forests he built castles and towers.

5¶ He fought also with the king of the Ammonites, and prevailed against them. And the children of Ammon gave him the same year an hundred talents of silver, and ten thousand measures of wheat, and ten thousand of barley. So much did the children of Ammon pay unto him, both the second year, and the third.27.5 So…: Heb. This 6So Jotham became mighty, because he prepared his ways before the LORD his God.27.6 prepared: or, established

7¶ Now the rest of the acts of Jotham, and all his wars, and his ways, lo, they are written in the book of the kings of Israel and Judah. 8He was five and twenty years old when he began to reign, and reigned sixteen years in Jerusalem.

9¶ And Jotham slept with his fathers, and they buried him in the city of David: and Ahaz his son reigned in his stead.