2 ዜና መዋዕል 16 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 16:1-14

የአሳ የመጨረሻ ዓመታት

16፥1-6 ተጓ ምብ – 1ነገ 15፥17-22

16፥11–17፥1 ተጓ ምብ – 1ነገ 15፥23-24

1አሳ በነገሠ በሠላሳ ስድስተኛው ዓመት፣ የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በይሁዳ ላይ ዘምቶ፣ ከይሁዳ ንጉሥ ከአሳ ግዛት ማንም እንዳይወጣ፣ ወደዚያም ማንም እንዳይገባ ለመከልከል ራማን መሸገ።

2አሳም ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና ከራሱም ቤተ መንግሥት ግምጃ ቤቶች ብርና ወርቅ ወስዶ በደማስቆ ተቀምጦ ይገዛ ለነበረው ለሶርያ ንጉሥ ለወልደ አዴር ላከ፤ 3ከዚያም “ቀድሞ በአባቴና በአባትህ መካከል እንደ ነበረው ሁሉ፣ ዛሬም በእኔና በአንተ መካከል የስምምነት ውል ይኑረን፤ እነሆ፤ ብርና ወርቅ ልኬልሃለሁ፤ ከእኔ ተመልሶ ይሄድ ዘንድ ከባኦስ ጋር ያደረግኸውን የስምምነት ውል አፍርስ” አለው።

4ወልደአዴር የንጉሥ አሳን ሐሳብ ተቀበለ፤ የጦር አዛዦቹንም በእስራኤል ከተሞች ላይ አዘመተ። እነርሱ ዒዮንን፣ ዳንን፣ አቤልማ ይምንና የንፍታሌምን የዕቃ ግምጃ ቤት ከተሞች ሁሉ ድል አድርገው ያዙ። 5ባኦስ ይህን በሰማ ጊዜ ራማን መገንባቱን አቆመ፤ ሥራውንም አቋረጠ። 6ንጉሥ አሳም የይሁዳን ሰዎች ሁሉ አመጣቸው፤ እነርሱም ባኦስ ይሠራበት የነበረውን ድንጋይና ዕንጨት ወሰዱ፤ አሳም ጌባንና ምጽጳን ሠራባት።

7በዚያን ጊዜም ባለ ራእዩ አናኒ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ መጥቶ እንዲህ አለው፤ “በአምላክህ በእግዚአብሔር ሳይሆን በሶርያ ንጉሥ ስለ ታመንህ፣ የሶርያ ንጉሥ ሰራዊት ከእጅህ አምልጧል። 8ኢትዮጵያውያንና ሊቢያውያን ብዙ ቍጥር ካላቸው ሠረገላዎቻቸውና16፥8 ወይም ሠረገለኞች ፈረሶቻቸው ጋር ኀያል ሰራዊት አልነበሩምን? ይሁን እንጂ በእግዚአብሔር ስለ ታመንህ በእጅህ አሳልፎ ሰጠህ፤ 9በፍጹም ልባቸው የሚታመኑበትን ለማበርታት የእግዚአብሔር ዐይኖች በምድር ሁሉ ላይ ይመለከታሉና። የሞኝነት ሥራ ስለ ሠራህ፣ ከእንግዲህ ወዲያ ጦርነት አይለይህም።”

10ከዚህ የተነሣም አሳ ባለ ራእዩን ተቈጣው፤ በጣም ስለ ተናደደም እስር ቤት አስገባው። በዚያን ጊዜም አሳ አንዳንድ ሰዎችን ክፉኛ አስጨነቃቸው።

11በአሳ ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የተከናወነው ሥራ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መዛግብት ተጽፏል። 12አሳ በነገሠ በሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት እግሮቹን ክፉኛ ታመመ፤ ሕመሙ ቢጸናበትም እንኳ፣ በዚያ ሁሉ ሕመም የባለ መድኀኒቶችን እንጂ የእግዚአብሔርን ርዳታ አልፈለገም። 13አሳም በነገሠ በአርባ አንደኛው ዓመት ሞተ፤ እንደ አባቶቹም ሁሉ አንቀላፋ። 14በዳዊት ከተማ ከዐለት አስፈልፍሎ ለራሱ ባሠራውም መቃብር ቀበሩት። በቅመማ ቅመምና በልዩ ልዩ ጣፋጭ ሽቱዎች በተሞላ ቃሬዛ ላይ አኖሩት፤ ስለ ክብሩም ትልቅ እሳት አነደዱ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

历代志下 16:1-14

犹大与以色列争战

1亚撒执政第三十六年,以色列巴沙上来攻打犹大,修筑拉玛,企图隔断犹大亚撒与外界的联系。 2于是,亚撒收集耶和华殿里和王宫库房里的金银,派人送给住在大马士革亚兰便·哈达,说: 3“我们之间应立盟约,像我们的父亲之间立约一样,现在奉上金银为礼,请你取消与以色列巴沙立的盟约。这样,他就会从我境内退兵。” 4便·哈达接受了亚撒王的提议,派将领攻打以色列的城邑,攻占了以云亚伯·玛音拿弗他利所有的储货城。 5巴沙闻讯,就停止修筑拉玛6亚撒王率领全体犹大人,将巴沙修筑拉玛所用的石头和木材全部搬走,用来修建迦巴米斯巴

哈拿尼先见

7那时,哈拿尼先见晋见犹大亚撒说:“因为你不倚靠你的上帝耶和华,反而倚靠亚兰王,所以亚兰王的军队已经从你手中逃脱。 8古实人与路比人不是一支强大的军队吗?他们的战车骑兵不是极多吗?然而,因为你倚靠耶和华,耶和华就把他们交在你手中。 9耶和华的眼目遍察天下,彰显大能来扶助那些全心归向祂的人。你做了愚蠢的事!从此以后,你必遭遇战祸。” 10亚撒听了就对先见发怒,把他囚禁在监狱里,同时又压迫一些民众。

亚撒逝世

11亚撒其他的事自始至终都记在犹大以色列的列王史上。 12亚撒执政第三十九年患了严重的脚病。然而,他在病中却没有寻求耶和华的帮助,只寻求医生的帮助。 13亚撒在他执政第四十一年去世,与他祖先同眠, 14葬在大卫城他为自己凿的坟墓里。民众把他放在堆满精心调制的各种香料的床上,又点了一堆大火向他致哀。