2 ዜና መዋዕል 10 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

2 ዜና መዋዕል 10:1-19

እስራኤል በሮብዓም ላይ ዐመፀ

10፥1–11፥4 ተጓ ምብ – 1ነገ 12፥1-24

1እስራኤላውያን ሁሉ ሊያነግሡት ወደዚያ ሄደው ስለ ነበር፣ ሮብዓም ወደ ሴኬም ሄደ። 2ከንጉሥ ሰሎሞን ሸሽቶ በግብፅ ይኖር የነበረው የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ይህን ሲሰማ፣ ከግብፅ ተመልሶ መጣ። 3እርሱንም ልከው አስጠሩት፤ ከዚያም እርሱና እስራኤል ሁሉ ወደ ሮብዓም ሄደው እንዲህ አሉት፤ 4“አባትህ በላያችን ከባድ ቀንበር ጫነብን፤ አንተ ግን አስጨናቂውን ሥራና በላያችን የጫነብንን ከባድ ቀንበር አቅልልልን፤ እኛም እንገዛልሃለን።”

5ሮብዓምም፣ “ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ወደ እኔ ኑ” አላቸው፤ ስለዚህ ሰዎቹ ወጥተው ሄዱ።

6ከዚያም ንጉሥ ሮብዓም፣ “ለዚህ ሕዝብ ምን እንድመልስለት ትመክሩኛላችሁ?” በማለት አባቱ ሰሎሞን በሕይወት ሳለ ያገለገሉትን የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠየቃቸው።

7እነርሱም፣ “ለዚህ ሕዝብ ደግ ከሆንህለት፣ ደስ ካሰኘኸውና የሚስማማው መልስ ከሰጠኸው ምንጊዜም ይገዛልሃል” አሉት።

8ሮብዓም ግን ሽማግሌዎች የሰጡትን ምክር ትቶ፣ አብሮ አደጎቹና አገልጋዮቹ ከሆኑት ወጣቶች ምክር ጠየቀ፤ 9እንዲህም አላቸው፤ “ ‘አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልልን’ ለሚሉኝ ለእነዚህ ሰዎች የምትሰጡኝ ምክር ምንድን ነው? ምንስ ብለን እንመልስላቸው?”

10አብሮ አደጎቹም ወጣቶች እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ለጠየቍህ ሕዝብ፤ ‘አባትህ በላያችን ከባድ ቀንበር ጫነብን፤ አንተ ግን ቀንበራችንን አቅልልልን’ ለሚሉህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ትንሿ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ይልቅ ትወፍራለች፤ 11አባቴ ከባድ ቀንበር ጫነባችሁ፤ እኔ ግን የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ።’ ”

12ንጉሡ፣ “ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ኑ” ባላቸው መሠረት ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ ከሦስት ቀን በኋላ ወደ ሮብዓም ተመለሱ። 13ንጉሡም የሽማግሌዎችን ምክር በመናቅ፣ አመናጭቆ መለሰላቸው፤ 14እርሱም የወጣቶቹን ምክር በመቀበል፣ “አባቴ ቀንበራችሁን አከበደ፤ እኔ ደግሞ የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ደግሞ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ” አላቸው። 15እግዚአብሔር በሴሎናዊው በአሒያ አማካይነት ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ ወስኖ ስለ ነበር፣ ንጉሡ ሕዝቡን አላዳመጠም።

16መላው እስራኤልም ንጉሡ ሊሰማቸው አለመፈለጉን በተረዱ ጊዜ፣ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤

“ከዳዊት ምን ድርሻ አለን?

ከእሴይስ ልጅ ምን ክፍል አለን?

እስራኤል፣ ሆይ፤ ወደ ድንኳንህ ተመለስ፤

ዳዊት ሆይ፤ አንተም የገዛ ቤትህን ጠብቅ።”

ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ ወደየቤታቸው ተመለሱ። 17ይሁን እንጂ በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩትን እስራኤላውያን አሁንም የሚገዛቸው ሮብዓም ነበር።

18ንጉሥ ሮብዓም የገባሮች ኀላፊ የነበረውን አዶራምን ላከው፤ እስራኤላውያን ግን በድንጋይ ወግረው ገደሉት። ንጉሥ ሮብዓም ግን እንደ ምንም ብሎ ሰረገላው ላይ በመውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሸሽቶ አመለጠ። 19ስለዚህ እስራኤል እስከ ዛሬ ድረስ በዳዊት ቤት ላይ እንደ ዐመፀ ነው።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

历代志下 10:1-19

北方支派背叛罗波安

1罗波安前往示剑,因为以色列人都去了那里要立他为王。 2尼八的儿子耶罗波安曾为了躲避所罗门王而逃往埃及,并一直住在那里。他听到消息便返回以色列3以色列人派人去请他,他就和以色列众人去见罗波安,说: 4“你父亲使我们负担沉重,求你减轻我们的负担吧,我们一定效忠你。” 5罗波安对他们说:“你们三天之后再来见我。”众人就离开了。

6罗波安王去征询曾服侍他父亲所罗门的老臣的意见,说:“你们认为我该怎样回复这些百姓?” 7他们回禀说:“王若善待这些百姓,使他们喜悦,对他们好言相待,他们会永远做王的仆人。”

8罗波安却没有采纳老臣的意见。他又去征询那些和他一起长大的青年臣僚的意见, 9说:“百姓求我减轻我父亲加给他们的重担。你们认为我该怎样回复他们?” 10他们说:“百姓说你父亲使他们负担沉重,请求你减轻他们的负担。你可以这样回复他们,‘我的小指头比我父亲的腰还粗。 11我父亲使你们负重担,我要使你们负更重的担子;我父亲用鞭子打你们,我要用刺鞭打你们。’”

12过了三天,耶罗波安和百姓遵照罗波安王的话来见他。 13-14罗波安王没有采纳老臣的建议,而是照青年臣僚的建议,疾言厉色地对他们说:“我父亲使你们负重担,我要使你们负更重的担子!我父亲用鞭子打你们,我要用刺鞭打你们!” 15王不听百姓的请求。这事出于耶和华上帝,为要应验祂借示罗亚希雅先知对尼八的儿子耶罗波安说的话。

16以色列人见王不听他们的请求,就说:

“我们与大卫有何相干?

我们与耶西的儿子没有关系!

以色列人啊,各自回家吧!

大卫家啊,自己照顾自己吧!”

于是,以色列人都各自回家了。 17但住在犹大城邑的以色列人仍受罗波安统治。 18罗波安王派劳役总管哈多兰以色列人那里,以色列人却用石头打死了他,罗波安王连忙上车逃回耶路撒冷19从此,以色列人反叛大卫家,直到今天。