2 ነገሥት 23 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

2 ነገሥት 23:1-37

ኢዮስያስ ኪዳኑን ዐደሰ

23፥1-3 ተጓ ምብ – 2ዜና 34፥29-32

23፥4-20 ተጓ ምብ – 2ዜና 34፥3-733

23፥21-23 ተጓ ምብ – 2ዜና 35፥118-19

23፥28-30 ተጓ ምብ – 2ዜና 35፥20–36፥1

1ከዚያም ንጉሡ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠራ። 2የይሁዳን ሰዎች ሁሉ፣ የኢየሩሳሌምን ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ፣ ካህናቱንና ነቢያቱን ሁሉ ከልጅ እስከ ዐዋቂ አንድም ሰው ሳይቀር ይዟቸው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መጣ። በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የተገኘውንም የኪዳኑን መጽሐፍ ቃል በጆሯቸው እንዲሰሙት በሙሉ አነበበላቸው። 3ንጉሡም በዐምደ ወርቁ አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ እግዚአብሔርን እንደሚከተል ትእዛዞቹን፣ ደንቦቹን፣ ሥርዐቶቹን በፍጹም ልቡ፣ በፍጹምም ነፍሱ እንደሚጠብቅ፣ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈውን ኪዳን እንደሚያጸና በእግዚአብሔር ፊት ኪዳኑን አደሰ፤ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ለኪዳኑ ያላቸውን ታማኝነት አረጋገጡ።

4ንጉሡም ለበኣል፣ ለአሼራና ለሰማይ ከዋክብት ሰራዊት ሁሉ የተሠሩትን የመገልገያ ዕቃዎች በሙሉ፣ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንዲያወጡ ሊቀ ካህናቱን ኬልቅያስን በሁለተኛ ማዕረግ ያሉትን ካህናትና የቤተ መቅደሱን በር ጠባቂዎች አዘዘ። ዕቃዎቹንም ከኢየሩሳሌም ውጭ በቄድሮን ሸለቆ ሜዳ ላይ አቃጠላቸው፤ ዐመዱንም ወደ ቤቴል ወሰደው። 5በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ዙሪያ በሚገኙ ኰረብቶች ላይ ዕጣን እንዲያጥኑ የይሁዳ ነገሥታት የሾሟቸውን የጣዖት ካህናት አባረረ እንዲሁም ለበኣል፣ ለፀሓይና ለጨረቃ፣ ለስብስብ ከዋክብትና ለመላው የሰማይ ከዋክብት ሰራዊት የሚያጥኑትን አስወገደ። 6የአሼራንም ምስል ዐምድ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አውጥቶ ከኢየሩሳሌም ውጭ ወዳለው ወደ ቄድሮን ሸለቆ ወስዶ አቃጠለው፤ አድቅቆ ፈጭቶም በሕዝቡ መቃብር ላይ በተነው። 7እንዲሁም ስለ አምልኮ ባዕድ ሥርዐት በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የቤተ ጣዖት ወንደቃዎችን ክፍሎችና ሴቶች ለአሼራ መጋረጃ የሚፈትሉባቸውን ክፍሎች አፈረሰ።

8ኢዮስያስ የቤተ ጣዖት ካህናትን ሁሉ ከይሁዳ ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም አወጣቸው፤ ከጌባ ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ፣ ካህናቱ ዕጣን ያጥኑባቸው የነበሩትን የኰረብታ ማምለኪያ ስፍራዎችን አረከሰ። ከከተማዪቱ በር በስተ ግራ በኩል፣ በከተማዪቱ ገዥ በኢያሱ በር መግቢያ አጠገብ የነበሩትን የበሮቹን ማምለኪያ ስፍራዎች23፥8 ወይም፣ ከፍተኛ ቦታዎች አፈረሰ። 9የየኰረብታው ማምለኪያ ካህናት ኢየሩሳሌም ባለው በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ባያገለግሉም እንኳ ከካህናት ወንድሞቻቸው ጋር እርሾ ያልነካው ቂጣ ይበሉ ነበር።

10በሄኖም ሸለቆ የነበረውን ቶፌት የተባለውን ማምለኪያ አረከሰ፤ ይኸውም ማንም ሰው ወንድ ወይም ሴት ልጁን ለሞሎክ በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ እንዳያቀርብበት23፥10 ወይም ወንድ ወይም ሴት ልጁን የገደለ ነው። 11የይሁዳ ነገሥታት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መግቢያ ላይ ለፀሓይ አምልኮ የሰጧቸውን ፈረሶች ከዚያ አስወገደ። እነዚህም ናታን ሜሌክ በተባለ በአንድ ሹም ቤት አጠገብ በአደባባዩ ላይ ነበሩ። ኢዮስያስም ለፀሓይ አምልኮ የተሰጡትን ሠረገሎች አቃጠለ።

12የይሁዳ ነገሥታት በላይኛው የአካዝ እልፍኝ አጠገብ በሰገነቱ ላይ ያቆሟቸውን መሠዊያዎች፣ ምናሴም በሁለቱ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባዮች ላይ ያሠራቸውን መሠዊያዎች አስወገደ፤ ስብርብራቸውን አወጣ፤ ድቃቂውንም አንሥቶ ወደ ቄድሮን ሸለቆ ጣለው። 13እንዲሁም ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ከርኩሰት ኰረብታ በስተ ደቡብ የነበሩትን የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለሲዶናውያን የርኩሰት አምላክ ለአስታሮት፣ ለሞዓብ ሕዝቦች የርኩሰት አምላክ ለካሞሽ፣ ለአሞን ሕዝቦች የርኩሰት አምላክ ለሞሎክ ያሠራቸውን የኰረብታ ላይ ማምለኪያዎች ንጉሡ አረከሰ። 14አሁንም ኢዮስያስ ማምለኪያ የድንጋይ ሐውልቶችን ሰባበረ፤ የአሼራን ምስል ዐምዶች ቈራረጠ፤ ስፍራውንም በሙታን ዐጥንት ሞላው።

15እስራኤልን ባሳተው በናባጥ ልጅ በኢዮርብዓም የተሠራውን መሠዊያ፣ በቤቴል የነበረውን ያን የኰረብታ ማምለኪያ ስፍራ፣ መሠዊያው ያለበትን ያን የኰረብታ ማምለኪያ ስፍራ እንኳ እንደዚሁ አፈረሰ፤ ድንጋዮቹን ሰባበረ፤ እንደ ዱቄትም አደቀቃቸው፤ የአሼራንም ምስል ዐምድ አቃጠለ። 16ኢዮስያስ ዘወር ሲል በኰረብታው ላይ የነበሩትን መቃብሮች አየ፤ ዐፅሞቹንም ከየመቃብሩ አስወጣ፤ ያ የእግዚአብሔር ሰው አስቀድሞ እንደ ተናገረው፣ የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ መሠዊያውን ለማርከስ ሲል ዐፅሞቹን በላዩ ላይ አቃጠለበት።

17ንጉሡም፣ “ያ የማየው የመቃብር ሐውልት የማን ነው?” ሲል ጠየቀ የከተማዪቱም ሰዎች፣ “ከይሁዳ መጥቶ አሁን አንተ ያደረግኸውን ነገር ሁሉ በቤቴል መሠዊያ ላይ እንደሚደርስ የተናገረ የዚያ የእግዚአብሔር ሰው መቃብር ነው” አሉት።

18ኢዮስያስም፣ “በሉ እንዳለ ተዉት፤ ዐፅሙን ማንም ሰው ከቦታው እንዳያንቀሳቅሰው” አለ፤ ስለዚህ የእርሱንና ከሰማርያ የመጣውን ነቢይ ዐፅም ሳይነኩ እንዳለ ተውት። 19ኢዮስያስም በቤቴል እንዳደረገው ሁሉ በሰማርያም ከተሞች ኰረብቶች ላይ የእስራኤል ነገሥታት አሠርተዋቸው የነበሩትንና እግዚአብሔርን ያስቈጡበትን ቤተ ጣዖቶች ሁሉ አስወገደ፤ አረከሳቸውም። 20ኢዮስያስ እነዚያን የየኰረብታውን ማምለኪያ ቦታ ካህናትን ሁሉ፣ በየመሠዊያው ላይ ዐረዳቸው፤ በመሠዊያዎቹ ላይ የሰው ዐፅም አቃጠለ፣ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።

21ንጉሡም መላውን ሕዝብ፣ “በዚህ በኪዳኑ መጽሐፍ በተጻፈው መሠረት የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ፋሲካ አክብሩ” ብሎ አዘዘ። 22እስራኤልን ከመሩ ከመሳፍንት ዘመን ጀምሮ፣ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት ዘመን ሁሉ፣ እንደዚህ ያለ ፋሲካ መቼም ተከብሮ አያውቅም። 23በኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት ግን ይህ ፋሲካ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ተከበረ። 24ከዚህም በቀር ኢዮስያስ ሙታን አነጋጋሪዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን፣ የየቤተ ሰቡ ሰውን አማልክት፣ ጣዖታትን እንዲሁም በይሁዳና በኢየሩሳሌም የተገኙትን ሌሎች አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ አስወገደ፤ ይህን ያደረገውም ካህኑ ኬልቅያስ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ባገኘው መጽሐፍ የተጻፈው የሕጉ ቃል ተፈጻሚነት እንዲኖረው ለማድረግ ነው። 25በሙሴ ሕግ በተጻፈው መሠረት በፍጹም ልቡ፣ በፍጹም ነፍሱ፣ በፍጹም ኀይሉ ወደ እግዚአብሔር የተመለሰ፣ እንደ ኢዮስያስ ያለ ንጉሥ፣ ከእርሱ በፊትም ሆነ ከእርሱ በኋላ ፈጽሞ አልተነሣም። 26ይህም ሆኖ እንኳ ለቍጣ እንዲነሣሣ ምናሴ ካደረጋቸው ነገሮች ሁሉ የተነሣ፣ እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ከነደደው ከአስፈሪው ቍጣው ገና አልበረደም ነበር። 27ስለዚህ እግዚአብሔር፣ “እስራኤልን እንዳስወገድሁ ሁሉ ይሁዳንም ከፊቴ አስወግዳለሁ፤ የመረጥኋትን ከተማ ኢየሩሳሌምንና፣ ‘ስሜ በዚያ ይሆናል’23፥27 1ነገ 8፥29 ይመ ብዬ የተናገርሁለትን ይህን ቤተ መቅደስ እተዋለሁ” አለ።

28በኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራ፣ የፈጸመውም ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?

29ኢዮስያስ ንጉሥ በነበረበት ዘመን የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ኒካዑ የአሦርን ንጉሥ ለመርዳት ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ወጥቶ ነበር፤ ንጉሥ ኢዮስያስም ጦርነት ሊገጥመው ወጣ፤ ሆኖም ፈርዖን ኒካዑ ፊት ለፊት ገጥሞት መጊዶ ላይ ገደለው። 30የኢዮስያስም አገልጋዮች ከመጊዶ ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው በገዛ መቃብሩ ቀበሩት። የአገሩም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአክስን ወሰዱት፤ ቀብተውም በአባቱ እግር አነገሡት።

የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአክስ

23፥31-34 ተጓ ምብ – 2ዜና 36፥2-4

31ኢዮአክስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ ሦስት ዓመት ነበር፤ እርሱም በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ሦስት ወር ገዛ። እናቱ አሚጣል ትባላለች፤ እርሷም የልብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች። 32አባቶቹ እንዳደረጉ ሁሉ፣ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ። 33በኢየሩሳሌም ተቀምጦ እንዳይገዛም ፈርዖን ኒካዑ በሐማት ምድር ሪብላ በምትባል ቦታ በሰንሰለት አሰረው23፥33 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ግን (2ዜና 36፥3 ይመ)፣ ኒካዑ በሐማት ምድር ሪብላ በምትባል ላይ አስወገደው፤ በይሁዳም ላይ መቶ መክሊት23፥33 3.4 ሜትሪክ ቶን ያህል ነው። ብርና አንድ መክሊት23፥33 34 ኪሎ ግራም ያህል ነው። ወርቅ ግብር ጣለበት። 34ፈርዖን ኒካዑ የኢዮስያስን ልጅ ኤልያቄምን በአባቱ በኢዮስያስ እግር አነገሠው፤ ኤልያቄም የተባለ ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠው። ነገር ግን ኢዮአክስን በምርኮ ወደ ግብፅ ወሰደው፤ እርሱም በዚያ ሞተ። 35ኢዮአቄምም ፈርዖን ኒካዑ የጠየቀውን ብርና ወርቅ ከፈለ፤ ይህን ለማድረግም የመሬት ግብር ጣለ፤ የአገሩም ሰዎች እንደ ገቢው መጠን ብሩንና ወርቁን እንዲከፍሉ አደረገ።

ኢዮአቄም የይሁዳ ንጉሥ

23፥36–24፥1፡5-6 ተጓ ምብ – 2ዜና 36፥5-8

36ኢዮአቄም ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ። እናቱ ዘቢዳ ትባላለች፤ እርሷም የሩማ ተወላጅ የፈዳያ ልጅ ነበረች። 37ኢዮአቄም አባቶቹ እንደ አደረጉት ሁሉ፣ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

列王紀下 23:1-37

約西亞的改革

1於是,王召集猶大耶路撒冷的所有長老, 2與祭司、先知、猶大人、耶路撒冷的居民等全體民眾,不論貴賤,一同上到耶和華的殿。王把在殿中發現的約書唸給他們聽。 3王站在柱旁,在耶和華面前立約,要全心全意地跟隨耶和華,遵從祂的一切誡命、法度和律例,履行約書上的規定。民眾都答應守約。

4王吩咐大祭司希勒迦及其副手和殿門守衛清除耶和華殿裡用來祭拜巴力亞舍拉及天上萬象的一切器具,將其搬到耶路撒冷城外汲淪溪旁的田野燒掉,又把灰燼帶到伯特利5從前,猶大各王任命祭司在猶大各城和耶路撒冷周圍的邱壇燒香。現在,約西亞除掉那些祭司,又除掉向巴力、日、月、星辰及天上萬象燒香的祭司。 6他將亞舍拉神像從耶和華的殿裡搬到耶路撒冷城外汲淪溪旁燒掉,磨成灰撒在平民的墳墓上。 7他又拆毀耶和華的殿內男廟妓的房屋,就是婦女為亞舍拉編織帳幔的地方。 8他召集猶大各城中的祭司,污瀆從迦巴別示巴的各邱壇,那些祭司曾在那裡燒香。他拆毀耶路撒冷城門左邊、約書亞總督門前的邱壇。 9但在邱壇燒香的祭司不能在耶路撒冷耶和華的祭壇那裡事奉,只可以和其他祭司一起吃無酵餅。 10他污瀆欣嫩子谷中的陀斐特,使人們不能焚燒自己的兒女獻給摩洛11他從耶和華的殿門口除掉猶大各王獻給太陽神的馬匹,這些馬匹在太監拿單·米勒房子旁邊的院子裡。他燒掉了那些獻給太陽神的戰車。 12他推倒猶大各王在亞哈斯樓頂上建造的祭壇,摧毀瑪拿西在耶和華殿的兩個院子裡所築的祭壇,把它們打碎,把灰丟進汲淪溪。 13他污瀆耶路撒冷東面、敗壞山南面的邱壇。這些邱壇都是以色列所羅門西頓人可憎的神明亞斯她錄摩押人可憎的神明基抹亞捫人可憎的神明米勒公建造的。 14他砸碎神柱,砍倒亞舍拉神像,用死人骨頭填滿那些地方。

15他拆掉伯特利高崗上的祭壇,即尼八的兒子耶羅波安誘使以色列人犯罪時建造的祭壇,把祭壇燒毀,搗碎成灰,又焚燒亞舍拉神像。 16約西亞轉身看見山上的墳墓,就派人取出墓中的屍骨,放在那祭壇上焚燒,污瀆了那祭壇,應驗了耶和華藉祂的僕人所說的預言。 17約西亞問:「我看到的那墓碑是誰的?」那城裡的人告訴他:「是上帝僕人的,他曾從猶大來預言你對伯特利祭壇所做的這些事。」 18他說:「不要動他,不要動他的屍骨。」於是,他們沒有動那位先知和撒瑪利亞來的先知的屍骨。 19他拆毀以色列各王從前建在撒瑪利亞各城高崗上、惹耶和華發怒的邱壇,就像他在伯特利所做的一樣。 20他在祭壇上殺死那些邱壇的祭司,又在壇上焚燒死人骨頭。之後,他返回耶路撒冷

約西亞守逾越節

21約西亞王吩咐民眾:「你們應當依照約書的記載慶祝逾越節,以尊崇你們的上帝耶和華。」 22-23約西亞執政第十八年,他們在耶路撒冷慶祝逾越節,以尊崇耶和華。自士師治理以色列起,至以色列猶大列王統治期間,都沒有這樣慶祝過逾越節。

24為了遵守祭司希勒迦在耶和華殿裡找到的律法書上的話,約西亞徹底清除了耶路撒冷猶大境內的靈媒、巫師、家庭神像及其他一切可憎之物。 25約西亞全心、全意、全力歸向耶和華,遵行摩西的一切律法,在猶大列王中空前絕後。

26然而,瑪拿西所行的一切惹怒耶和華,耶和華對猶大仍盛怒未息。 27耶和華說:「我要像驅逐以色列人一樣將猶大人從我面前趕走。我要撇棄我所揀選的耶路撒冷和我名常在的殿。」

28約西亞其他的事及作為都記在猶大的列王史上。 29約西亞執政期間,埃及尼哥前往幼發拉底河援助亞述王,約西亞出兵迎戰尼哥,在米吉多被殺。 30他的臣僕用車把他的屍體從米吉多運回耶路撒冷,安葬在他的墓穴裡。民眾膏立他兒子約哈斯做王。

約哈斯做猶大王

31約哈斯二十三歲登基,在耶路撒冷執政三個月。他母親叫哈慕她,是立拿耶利米的女兒。 32約哈斯像他祖先一樣做耶和華視為惡的事。 33埃及尼哥約哈斯囚禁在哈馬利比拉,不准他在耶路撒冷做王,又罰猶大國三點四噸銀子和三十四公斤金子。

約雅敬做猶大王

34埃及尼哥約西亞的另一個兒子以利亞敬為王,給他改名為約雅敬約哈斯尼哥帶到埃及,並死在那裡。 35為了繳納法老索要的金銀,約雅敬向全國徵稅,按照民眾家產的多少徵收金銀。 36約雅敬二十五歲登基,在耶路撒冷執政十一年。他母親叫西布妲,是魯瑪毗大雅的女兒。 37他像他祖先一樣做耶和華視為惡的事。