2 ነገሥት 21 – NASV & KJV

New Amharic Standard Version

2 ነገሥት 21:1-26

የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ

21፥1-10 ተጓ ምብ – 2ዜና 33፥1-10

21፥17-18 ተጓ ምብ – 2ዜና 33፥18-20

1ምናሴ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም አምሳ አምስት ዓመት ገዛ፤ እናቱም ሐፍሴባ ትባል ነበር። 2ምናሴ እግዚአብሔር ከእስራኤላውያን ፊት አሳድዶ ያወጣቸውን የአሕዛብን አስጸያፊ ልማድ በመከተል በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸመ። 3አባቱ ሕዝቅያስ ያፈረሰውን የየኰረብታውን ማምለኪያ ስፍራ መልሶ ሠራ፤ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ እንዳደረገው ሁሉ፣ እርሱም ለበኣል መሠዊያዎችን አቆመ፤ የአሼራንም ምስል ዐምድ ሠራ። እንዲሁም ለሰማይ ከዋክብት ሰራዊት ሁሉ ሰገደ፤ አመለካቸውም። 4እግዚአብሔር፣ “ስሜን በኢየሩሳሌም አኖራለሁ” ባለበት በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠዊያዎችን ሠራ። 5በሁለቱም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባዮች ለሰማይ ከዋክብት ሰራዊት ሁሉ መሠዊያ ሠራ። 6የገዛ ልጁን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ21፥6 ወይም፣ የራሱን ልጅ በዚህ ውስጥ እንዲያልፍ አደረገ።፤ መተተኛና ጠንቋይ ሆነ፤ ሙታን አነጋጋሪዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን ምክር ጠየቀ፤ እግዚአብሔርን ለቍጣ የሚያነሣሣውን ክፉ ድርጊት በፊቱ ፈጸመ።

7የሠራውን የአሼራን የተቀረጸ ምስል ዐምድ ወስዶ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አስቀመጠ፤ ይህም እግዚአብሔር ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን፣ “በዚህ ቤተ መቅደስና ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ በመረጥኋት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘላለም አኖራለሁ” ያለው ስፍራ ነው። 8እንዲሁም፣ “ብቻ ያዘዝኋቸውን ሁሉ ተጠንቅቀው በመፈጸምና ባሪያዬ ሙሴ የሰጣቸውንም ሕግ በሙሉ በመጠበቅ ይጽኑ እንጂ ከእንግዲህ የእስራኤላውያን እግር፣ ለአባቶቻቸው ከሰጠኋቸው ምድር ወጥቶ እንዲንከራተት አላደርግም” ያለው ስለዚሁ ስፍራ ነው። 9ሕዝቡ ግን አልሰሙም፤ እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ፊት ካጠፋቸው አሕዛብ ይልቅ ክፉ ድርጊት እንዲፈጽሙ ምናሴ አሳታቸው።

10እግዚአብሔር በባሪያዎቹ በነቢያት አማካይነት እንዲህ ሲል ተናገረ፤ 11“የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ይህን ሁሉ አስጸያፊ ኀጢአት ሠርቷል፤ ከእርሱ በፊት ከነበሩት አሞራውያን ይልቅ ክፉ ድርጊት ፈጽሟል፤ ይሁዳንም በጣዖታቱ አስቷል። 12ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‘ለሚሰማ ሁሉ ጆሮዎቹ ጭው እንዲሉ የሚያደርግ ክፉ መከራ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ አመጣለሁ። 13በሰማርያ ላይ ያዘጋጀሁትን መለኪያ ገመድ፣ የአክዓብንም ቤት የለካሁበትን ቱንቢ በኢየሩሳሌም ላይ እዘረጋለሁ፤ አንድ ሰው ሳሕን እንደሚወለውል ከወለወለም በኋላ እንደሚገለብጠው እኔም ኢየሩሳሌምን ወልውዬ እገለብጣታለሁ። 14የርስቴንም ቅሬታ እተዋቸዋለሁ፤ ለጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ ለጠላቶቻቸውም ሁሉ ብዝበዛና ምርኮ ይሆናሉ። 15ይህን የማደርገውም የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ በፊቴ ክፉ ድርጊት ስለ ፈጸሙና ለቍጣ ስላነሣሡኝ ነው።’ ” 16ይልቁንም ምናሴ፣ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት እንዲፈጽም ይሁዳን ካሳተበት ኀጢአት ሌላ፣ ኢየሩሳሌምን ከዳር እስከ ዳር እስኪሞላት ድረስ ብዙ ንጹሕ ደም አፈሰሰ።

17በምናሴ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራ፣ የሠራውን ኀጢአት ጨምሮ የፈጸመው ድርጊት ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? 18ምናሴም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ “የዖዛ አትክልት” በሚባለው በቤተ መንግሥቱ አትክልት ውስጥ ተቀበረ። ልጁ አሞንም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

የይሁዳ ንጉሥ አሞን

21፥19-24 ተጓ ምብ – 2ዜና 33፥21-25

19አሞን ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሁለት ዓመት ገዛ፤ እናቱ ሜሶላም ትባላለች፤ እርሷም የዮጥባ አገር ሰው የሐሩስ ልጅ ነበረች። 20አባቱ ምናሴ እንዳደረገው ሁሉ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸመ። 21አባቱ በሄደበት መንገድ ሁሉ ሄደ፤ አባቱ ያመለካቸውን አማልክት አመለከ፤ ሰገደላቸውም። 22የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ተወ፤ በእግዚአብሔርም መንገድ አልሄደም።

23የአሞንም ሹማምት ዐመፁ፤ ንጉሡንም በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ገደሉት። 24ከዚያም የአገሩ ሕዝብ በንጉሥ አሞን ላይ ያመፁትን ሁሉ ገደሉ፤ ልጁን ኢዮስያስንም በእግሩ ተክተው አነገሡት።

25በአሞን ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራ፣ የፈጸመውም ድርጊት ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? 26እርሱም በዖዛ አትክልት ውስጥ ባለው መቃብሩ ተቀበረ፤ ልጁ ኢዮስያስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

King James Version

2 Kings 21:1-26

1Manasseh was twelve years old when he began to reign, and reigned fifty and five years in Jerusalem. And his mother’s name was Hephzi-bah. 2And he did that which was evil in the sight of the LORD, after the abominations of the heathen, whom the LORD cast out before the children of Israel. 3For he built up again the high places which Hezekiah his father had destroyed; and he reared up altars for Baal, and made a grove, as did Ahab king of Israel; and worshipped all the host of heaven, and served them. 4And he built altars in the house of the LORD, of which the LORD said, In Jerusalem will I put my name. 5And he built altars for all the host of heaven in the two courts of the house of the LORD. 6And he made his son pass through the fire, and observed times, and used enchantments, and dealt with familiar spirits and wizards: he wrought much wickedness in the sight of the LORD, to provoke him to anger. 7And he set a graven image of the grove that he had made in the house, of which the LORD said to David, and to Solomon his son, In this house, and in Jerusalem, which I have chosen out of all tribes of Israel, will I put my name for ever: 8Neither will I make the feet of Israel move any more out of the land which I gave their fathers; only if they will observe to do according to all that I have commanded them, and according to all the law that my servant Moses commanded them. 9But they hearkened not: and Manasseh seduced them to do more evil than did the nations whom the LORD destroyed before the children of Israel.

10¶ And the LORD spake by his servants the prophets, saying, 11Because Manasseh king of Judah hath done these abominations, and hath done wickedly above all that the Amorites did, which were before him, and hath made Judah also to sin with his idols: 12Therefore thus saith the LORD God of Israel, Behold, I am bringing such evil upon Jerusalem and Judah, that whosoever heareth of it, both his ears shall tingle. 13And I will stretch over Jerusalem the line of Samaria, and the plummet of the house of Ahab: and I will wipe Jerusalem as a man wipeth a dish, wiping it, and turning it upside down.21.13 wiping…: Heb. he wipeth and turneth it upon the face thereof 14And I will forsake the remnant of mine inheritance, and deliver them into the hand of their enemies; and they shall become a prey and a spoil to all their enemies; 15Because they have done that which was evil in my sight, and have provoked me to anger, since the day their fathers came forth out of Egypt, even unto this day. 16Moreover Manasseh shed innocent blood very much, till he had filled Jerusalem from one end to another; beside his sin wherewith he made Judah to sin, in doing that which was evil in the sight of the LORD.21.16 from…: Heb. from mouth to mouth

17¶ Now the rest of the acts of Manasseh, and all that he did, and his sin that he sinned, are they not written in the book of the chronicles of the kings of Judah? 18And Manasseh slept with his fathers, and was buried in the garden of his own house, in the garden of Uzza: and Amon his son reigned in his stead.

19¶ Amon was twenty and two years old when he began to reign, and he reigned two years in Jerusalem. And his mother’s name was Meshullemeth, the daughter of Haruz of Jotbah. 20And he did that which was evil in the sight of the LORD, as his father Manasseh did. 21And he walked in all the way that his father walked in, and served the idols that his father served, and worshipped them: 22And he forsook the LORD God of his fathers, and walked not in the way of the LORD.

23¶ And the servants of Amon conspired against him, and slew the king in his own house. 24And the people of the land slew all them that had conspired against king Amon; and the people of the land made Josiah his son king in his stead. 25Now the rest of the acts of Amon which he did, are they not written in the book of the chronicles of the kings of Judah? 26And he was buried in his sepulchre in the garden of Uzza: and Josiah his son reigned in his stead.21.26 Josiah: Gr. Josias