2 ነገሥት 13 – NASV & NUB

New Amharic Standard Version

2 ነገሥት 13:1-25

የእስራኤል ንጉሥ ኢዮአካዝ

1የይሁዳ ንጉሥ የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ በነገሠ በሃያ ሦስተኛው ዓመት፣ የኢዩ ልጅ ኢዮአካዝ በሰማርያ ከተማ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ዐሥራ ሰባት ዓመትም ገዛ። 2እርሱም የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤልን ያሳተበትን ኀጢአት በመከተል በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠራ፤ ከዚህ ድርጊቱም አልተመለሰም። 3የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ ስለዚህ የሶርያ ንጉሥ አዛሄልና ልጁ ቤን ሃዳድ በነበሩበት ዘመን ሁሉ አሳልፎ በእጃቸው ሰጣቸው።

4ከዚያም ኢዮአካዝ እግዚአብሔርን ለመነ፤ እግዚአብሔርም የሶርያ ንጉሥ እስራኤልን እንዴት አድርጎ እንዳስጨነቀ አይቷልና ልመናውን ሰማው። 5ስለዚህ እግዚአብሔር ለእስራኤል የሚታደጋቸውን ሰው ሰጠ፤ እነርሱም ከሶርያውያን ጭቈና ተላቀቁ፤ እንደ ቀድሞውም በየድንኳናቸው መኖር ጀመሩ፤ 6ይሁን እንጂ እስራኤልን ከአሳተው ከኢዮርብዓም ቤት ኀጢአት አልተመለሱም፤ በዚያው ገፉበት እንጂ። የአሼራም ምስል ዐምድ13፥6 በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ሁሉ ይህ የአሼራን ሴት ጣዖት የሚያመለክት ነው። በሰማርያ መመለኩ ቀጠለ።

7ከኢዮአካዝ ሰራዊት የተረፈው አምሳ ፈረሰኞች፣ ዐሥር ሠረገሎችና ዐሥር ሺሕ እግረኛ ወታደር ብቻ ነው፤ ይህ የሆነበትም ምክንያት የሶርያ ንጉሥ የቀረውን ስለ አጠፋውና እንደ ዐውድማ ብናኝ ስለ አደረገው ነበር።

8ኢዮአካዝ በዘመነ መንግሥቱ ያከናወነው ሌላው ሥራ፣ ያደረገውና የፈጸመውም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? 9ኢዮአካዝ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ተቀበረ። ልጁ ዮአስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ

10በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአስ ዘመን፣ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፣ የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ በሰማርያ ከተማ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ዐሥራ ስድስት ዓመትም ገዛ። 11እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠራ፤ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤልን ከአሳተበት ኀጢአት ሁሉ አልራቀም፤ በዚያው ገፋበት።

12ዮአስ በዘመነ መንግሥቱ ያከናወነው ሌላ ሥራ፣ ያደረገውና የፈጸመው ሁሉ እንዲሁም በይሁዳ ንጉሥ በአሜስያስ ላይ ያካሄደው ጦርነት ጭምር በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? 13ዮአስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ኢዮርብዓም በእግሩ ተተክቶ በዙፋኑ ተቀመጠ። ዮአስም በሰማርያ ከእስራኤል ነገሥታት ጋር ተቀበረ።

14በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ ለሞት ባደረሰው ሕመም ታሞ ነበር። የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ሊጠይቀው ወርዶ አለቀሰለት፤ “ወየው አባቴን! ወየው አባቴን! ወየው የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች!” እያለም ጮኸ።

15ኤልሳዕም፣ “አንድ ቀስትና ፍላጾች አምጣ” አለው፤ እርሱም አመጣ፤ 16የእስራኤልንም ንጉሥ፣ “ቀስቱን በእጅህ ያዘው” አለው፤ ቀስቱን በያዘውም ጊዜ ኤልሳዕ እጆቹን በንጉሡ እጆች ላይ አኖረ።

17ቀጥሎም፣ “የምሥራቁን መስኮት ክፈት” አለው፤ ከፈተውም፤ ኤልሳዕም፣ “በል አስፈንጥረው” አለው፤ አስፈነጠረውም፤ ከዚያም፣ “የእግዚአብሔር የድል ቀስት! ሶርያ ድል የምትሆንበት ቀስት!” አለ። ኤልሳዕም እንደ ገና “ሶርያውያንንም አፌቅ ላይ ፈጽመህ ድል ታደርጋቸዋለህ” አለው።

18ቀጥሎም፣ “በል ቀስቶቹን ውሰድ” አለው፤ ንጉሡም ወሰደ። ኤልሳዕም፣ “መሬቱን ውጋ” አለው፤ እርሱም ሦስት ጊዜ ወግቶ አቆመ።

19የእግዚአብሔርም ሰው ተቈጣውና፣ “መሬቱን አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መውጋት ነበረብህ፤ እንዲህ ብታደርግ ኖሮ ሶርያን ታሸንፍና ፈጽመህ ትደመስሳት ነበር፤ አሁን ግን የምታሸንፈው ሦስት ጊዜ ብቻ ነው” አለው።

20ኤልሳዕ ሞተ፤ ቀበሩትም። በዚህም ጊዜ ሞዓባውያን አደጋ ጣዮች በየዓመቱ በጸደይ ወራት ወደ እስራኤል ምድር እየሰረጉ ይገቡ ነበር።

21አንድ ጊዜ እስራኤላውያን ሰው ሞቶ ሲቀብሩ፣ አንድ የአደጋ ጣይ ቡድን በድንገት አዩ፤ ስለዚህ የሞተውን ሰው ሬሳ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ ጣሉት፤ ሬሳው የኤልሳዕን ዐፅም እንደ ነካም ወዲያውኑ ሰውየው ድኖ በእግሩ ቆመ።

22በኢዮአካዝ ዘመነ መንግሥት ሁሉ፣ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል፣ እስራኤልን ያስጨንቃቸው ነበር። 23እግዚአብሔር ግን ራራላቸው፤ ዐዘነላቸው፤ ፊቱን መለሰላቸው፤ ይህም ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር ስለ ገባው ኪዳን ሲል ነው፤ እስከ ዛሬ ድረስ ሊያጠፋቸው አልፈለገም፤ ከፊቱም አላስወገዳቸውም።

24የሶርያ ንጉሥ አዛሄል ሞተ፤ ልጁ ቤን ሃዳድም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። 25ከዚያም የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ፣ አዛሄል ከአባቱ ከኢዮአካዝ እጅ በጦርነት የወሰዳቸውን ከተሞች ከአዛሄል ልጅ ከቤን ሃዳድ አስመልሶ ያዘ። ዮአስ ሦስት ጊዜ ድል አደረገው፤ የእስራኤልንም ከተሞች በዚህ ሁኔታ መልሶ ያዘ።

Swedish Contemporary Bible

2 Kungaboken 13:1-25

Joachas regerar i Israel

1I Joashs, Achasjas sons, tjugotredje regeringsår över Juda blev Jehus son Joachas kung över Israel i Samaria och regerade sedan i sjutton år. 2Men Joachas gjorde det som var ont i Herrens ögon och begick Jerobeams, Nevats sons, synder, som han hade förlett Israel till att begå och vände sig inte bort från dem. 3Herren greps därför av vrede mot Israel, och han överlämnade dem åt kung Hasael i Aram och dennes son Ben-Hadad. 4Men Joachas vädjade till Herren, och Herren hörde honom när han såg hur kungen i Aram förtryckte Israel. 5Herren sände en räddare, och Israel lyckades ta sig ur araméernas grepp och fick sedan leva i sina hem som förut. 6Men de vände sig inte bort från de synder som Jerobeams ätt hade förlett Israel till att begå utan fortsatte med dem. Också asherapålen fick stå kvar i Samaria.

7Slutligen reducerades Joachas armé till 50 ryttare, 10 vagnar och 10 000 fotsoldater. Kungen i Aram hade lyckats utplåna de övriga styrkorna och gjort dem lika damm på en tröskplats.

8Joachas historia i övrigt, allt han gjorde, finns nedtecknat i Israels kungars krönika.

Joash regerar i Israel

9Joachas dog och gick till vila hos sina förfäder. Han begravdes i Samaria, och hans son Joash blev kung efter honom. 10Under Juda kung Joashs trettiosjunde regeringsår blev Joash, Joachas son, kung i Israel och regerade i Samaria i sexton år. 11Men han gjorde det som var ont i Herrens ögon och vände sig inte bort från Jerobeams, Nevats sons, synder, som han förlett Israel till att begå. Han fortsatte på samma sätt.

12Joashs historia i övrigt, vad han gjorde, och hans krig mot Amasja i Juda, finns nedtecknat i Israels kungars krönika.

13Joash dog och gick till vila hos sina förfäder. Jerobeam efterträdde honom. Han begravdes i Samaria bland Israels kungar.

Elishas sista profetia och en uppståndelse

14När Elisha låg sjuk i den sjukdom som sedan blev hans död, besökte Israels kung Joash honom och grät över honom: ”Min far! Min far! Israels vagnar och ryttare!” sa han.

15”Skaffa fram en båge och några pilar”, bad Elisha då honom. Han gjorde så. 16Elisha sa till Israels kung: ”Ta bågen i din hand!” När han tog den, lade Elisha sina händer på kungens. 17”Öppna nu det östra fönstret!” sa Elisha, och Joash gjorde som han sa. ”Skjut nu!” befallde han och medan han sköt, tillade Elisha: ”Detta är Herrens räddningspil mot Aram. Du ska nämligen slå araméerna vid Afek och utplåna dem.” 18Sedan sa han: ”Ta nu pilarna”, och när han tog dem, sa han till Israels kung: ”Slå dem mot golvet!”

Kungen slog dem mot golvet tre gånger. 19Gudsmannen blev arg på honom och utbrast: ”Du skulle ha slagit fem eller sex gånger, för då skulle du ha slagit Aram fullständigt. Nu kommer du bara att slå dem tre gånger.” 20Efter denna händelse dog Elisha och begravdes.

På den tiden brukade rövarband från Moab tränga in i landet varje vår. 21En gång när några män höll på att begrava en man, fick de syn på ett rövarband. Då slängde de den döda kroppen i Elishas grav och gick därifrån. Så snart kroppen kom i beröring med Elishas ben, fick den döde mannen liv igen och reste sig upp.

Uppfyllelse av Elishas profetia

22Kung Hasael av Aram hade förtryckt Israel under hela kung Joachas regering. 23Men Herren var barmhärtig mot dem och hade medlidande med dem för det förbunds skull som han slutit med Abraham, Isak och Jakob. Han ville inte utplåna dem eller driva bort dem ur sin åsyn.

24Men så dog kung Hasael av Aram, och hans son Ben-Hadad blev kung efter honom. 25Och Joash, Joachas son, återerövrade de städer som hans far Joachas hade förlorat till Ben-Hadad i ett krig. Tre gånger slog Joash Ben-Hadad och tog så tillbaka de israelitiska städerna.