1 ዮሐንስ 4 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

1 ዮሐንስ 4:1-21

መናፍስትን መርምሩ

1ወዳጆች ሆይ፤ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ፤ ምክንያቱም ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና። 2የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚቀበል መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ 3ኢየሱስን የማይቀበል መንፈስ ግን ከእግዚአብሔር አይደለም፤ እንደሚመጣ የሰማችሁት የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ይህ ነው፤ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።

4ልጆች ሆይ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ፤ እነርሱንም አሸንፋችኋቸዋል፤ ምክንያቱም በእናንተ ውስጥ ያለው በዓለም ካለው ይበልጣል። 5እነርሱ ከዓለም ናቸው፤ ስለዚህ የሚናገሩት እንደ ዓለም ነው፤ ዓለምም ይሰማቸዋል። 6እኛ ከእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል፤ ከእግዚአብሔር ያልሆነ ግን አይሰማንም፤ በዚህም የእውነትን መንፈስና የሐሰትን መንፈስ እናውቃለን።

የእግዚአብሔር ፍቅርና የሰው ፍቅር

7ወዳጆች ሆይ፤ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለሆነ እርስ በርሳችን እንዋደድ፤ የሚወድድ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ ነው፤ እግዚአብሔርንም ያውቃል። 8የማይወድድ ግን እግዚአብሔርን አያውቅም፤ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። 9እግዚአብሔር ፍቅሩን በመካከላችን የገለጠው እንዲህ ነው፤ እኛ በእርሱ አማካይነት በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ላከ። 10ፍቅር ይህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን እርሱ እንደ ወደደንና ስለ ኀጢአታችን ማስተስረያ4፥10 ወይም ኀጢአታችንን አስወግዶ፣ ቍጣውን ያርቅልን ዘንድ ይሆን ዘንድ ልጁን መላኩ ነው። 11ወዳጆች ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ ከወደደን፣ እኛም እርስ በእርሳችን መዋደድ ይገባናል። 12እግዚአብሔርን ያየ ከቶ ማንም የለም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ ግን እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል፤ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል።

13መንፈሱን ስለ ሰጠን፣ እኛ በእርሱ እንደምንኖር እርሱም በእኛ እንደሚኖር እናውቃለን። 14አብ ልጁን የዓለም አዳኝ ይሆን ዘንድ እንደ ላከው አይተናል፤ እንመሰክራለንም። 15ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምኖ በሚመሰክር ሁሉ፣ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል፤ እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል። 16ስለዚህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር እናውቃለን፤ በፍቅሩም እናምናለን።

እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል። 17በዚህም ዓለም እርሱን እንመስላለንና፤ በፍርድ ቀን ድፍረት ይኖረን ዘንድ፣ ፍቅር በዚህ ዐይነት በመካከላችን ፍጹም ሆኗል፤ 18በፍቅር ፍርሀት የለም፤ ፍጹም ፍቅር ግን ፍርሀትን አውጥቶ ይጥላል፤ ፍርሀት ከቅጣት ጋር የተያያዘ ነውና። የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።

19እርሱ አስቀድሞ ወድዶናልና እኛ እንወድደዋለን። 20ማንም፣ “እግዚአብሔርን እወድደዋለሁ” እያለ ወንድሙን ቢጠላ፣ እርሱ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድድ ያላየውን እግዚአብሔርን መውደድ አይችልምና። 21እርሱም “እግዚአብሔርን የሚወድድ ሁሉ ወንድሙን መውደድ ይገባዋል” የሚለውን ይህን ትእዛዝ ሰጥቶናል።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

約翰一書 4:1-21

靈的分辨

1親愛的弟兄姊妹,不要什麼靈都信,總要試驗那些靈是否出於上帝,因為世上已經出現了許多假先知! 2任何靈若承認耶穌基督曾降世為人,就是從上帝來的,你們可以憑這一點認出上帝的靈。 3任何靈若不承認耶穌,就不是從上帝來的,而是敵基督者的靈。以前你們聽說敵基督者要來,現在他已經在世上了。

4孩子們,你們屬於上帝,你們已經勝過了那些假先知,因為在你們裡面的聖靈比在世上運行的邪靈更有能力。 5他們屬於世界,所以他們談論的都是世俗的事,世人也聽從他們。 6我們屬於上帝,認識上帝的人聽從我們,不屬於上帝的人不聽從我們。這樣,我們就可以分辨真理的靈和錯謬的靈。

上帝是愛

7親愛的弟兄姊妹,我們應當彼此相愛,因為愛是從上帝來的。凡有愛心的人都是從上帝生的,並且認識上帝。 8沒有愛心的人不認識上帝,因為上帝就是愛。 9上帝差遣祂獨一的兒子到世上來,是為了叫我們靠著祂得到生命。這就顯明了上帝對我們的愛。 10不是我們愛上帝,而是上帝愛我們,並且差遣祂兒子為我們的罪作了贖罪祭,這就是愛。

11親愛的弟兄姊妹,上帝既然這樣愛我們,我們也應該彼此相愛。 12從來沒有人見過上帝,如果我們彼此相愛,上帝就住在我們裡面,祂的愛就在我們裡面得到成全。

13上帝將祂的靈賜給了我們,所以我們知道自己住在祂裡面,祂也住在我們裡面。 14我們看見過,現在做見證:父差遣了祂的兒子成為世人的救主。 15無論是誰,他若承認耶穌是上帝的兒子,上帝必住在他裡面,他也住在上帝裡面。 16我們已經認識並且相信了上帝對我們的愛。

上帝就是愛,住在愛中的,就是住在上帝裡面,上帝也住在他裡面。 17這樣,愛在我們裡面得到成全,使我們在審判的日子可以坦然無懼,因為我們在這世上以基督為榜樣。 18愛裡沒有恐懼,純全的愛能驅除恐懼,因為恐懼意味著怕受懲罰。人若心裡恐懼,就表示他尚未明白那純全的愛。

19我們愛,因為上帝先愛了我們。 20若有人說「我愛上帝」,卻恨自己的弟兄姊妹,這人就是說謊話,因為人若不愛看得見的弟兄姊妹,又怎能愛看不見的上帝呢? 21愛上帝的人也應該愛弟兄姊妹,這是上帝給我們的命令。