1 ነገሥት 6 – NASV & BPH

New Amharic Standard Version

1 ነገሥት 6:1-38

ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን መሥራት ጀመረ

6፥1-29 ተጓ ምብ – 2ዜና 3፥1-14

1እስራኤላውያን ከግብፅ በወጡ በአራት መቶ ሰማንያ6፥1 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም አራት መቶ አርባ ይላሉ። ዓመት፣ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ዚፍ በተባለው በሁለተኛው ወር ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ።

2ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር የሠራው ቤተ መቅደስ ርዝመቱ ስድሳ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ክንድ፣ ቁመቱ ሠላሳ ክንድ6፥2 ርዝመቱ 27 ሜትር፣ ወርዱ 9 ሜትር እንዲሁም ቁመቱ 13.5 ሜትር ያህል ነው። ነበር። 3በቤተ መቅደሱ ዋነኛ አዳራሽ ፊት ለፊት ያለው በረንዳ ወርዱ እንደ ቤተ መቅደሱ ወርድ ሁሉ ሃያ ክንድ6፥3 9 ሜትር ያህል ነው። ሲሆን፣ ርዝመቱ ዐሥር ክንድ6፥3 4.5 ሜትር ያህል ነው። ወደ ውጭ የወጣ ነበር። 4ለቤተ መቅደሱም ባለ ዐይነ ርግብ መስኮቶች አበጀ። 5በዋናው ቤተ መቅደስና በቅድስተ ቅዱሳኑ ግድግዳ ዙሪያ ልዩ ክፍሎች ያሉት ተቀጥላ ግንብ ሠራ። 6የምድር ቤቱ ወርድ አምስት ክንድ፣6፥6 በዚህ እንዲሁም በ10 እና 24 ላይ 2.3 ሜትር ያህል ነው። የመካከለኛው ፎቅ ስድስት ክንድ፣6፥6 2.7 ሜትር ያህል ነው። የሦስተኛው ፎቅ ሰባት ክንድ6፥6 3.1 ሜትር ያህል ነው። ነበር፤ የቤተ መቅደሱን ግድግዳ ዘልቆ እንዳይገባም፣ ከቤተ መቅደሱ ግንብ ውጭ ዙሪያውን እርከኖች አደረገ።

7ቤተ መቅደሱ የተሠራው እዚያው ድንጋዩ ተቈፍሮ ከወጣበት ቦታ በተዘጋጀ ድንጋይ በመሆኑ የመራጃ፣ የመሮ ወይም የሌላ ብረት ነክ መሣሪያ ድምፅ በቤተ መቅደሱ አካባቢ አልተሰማም ነበር።

8የምድር ቤቱ6፥8 የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ዕብራይስጡ ግን የመካከለኛው ደርብ ይላሉ። መግቢያ በስተ ደቡብ በኩል ባለው የቤተ መቅደሱ ጐን ሲሆን፣ ወደ መካከለኛውና ከዚያም ወደ መጨረሻው ፎቅ የሚያስወጣ ደረጃ ነበረው። 9ቤተ መቅደሱንም በዚሁ ሁኔታ ሠርቶ ጨረሰ፤ ለጣራው ተሸካሚ አደረገለት፤ በዝግባ ሳንቃም ከደነው። 10በቤተ መቅደሱም ዙሪያ በሙሉ፣ ቁመታቸው አምስት አምስት ክንድ የሆነ ክፍሎች ሠራ፤ እነዚህንም ከቤተ መቅደሱ ጋር በዝግባ አግዳሚ ዕንጨቶች አያያዛቸው።

11የእግዚአብሔርም ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሰሎሞን መጣ፤ 12“ስለምትሠራው ስለዚህ ቤተ መቅደስ ሥርዐቴን ብትከተል፣ ፍርዴን በተግባር ብትገልጸው፣ ትእዛዞቼን ብትጠብቅና ብትመላለስባቸው ለአባትህ ለዳዊት የሰጠሁትን ተስፋ በአንተ እፈጽመዋለሁ፤ 13በእስራኤላውያን መካከል እኖራለሁ፤ ሕዝቤን እስራኤልንም አልተወውም።”

14ስለዚህ ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ሠርቶ ፈጸመ፤ 15የውስጡን ግድግዳ ከቤተ መቅደሱ ወለል እስከ ጣራው ድረስ በዝግባ ሳንቃ ለበጠ፤ የቤተ መቅደሱንም ወለል የጥድ ሳንቃ አለበሰው። 16በቤተ መቅደሱም ውስጥ በስተ ኋላ በኩል፣ ሃያውን ክንድ ቅድስተ ቅዱሳን እንዲሆን፣ ከወለሉ አንሥቶ እስከ ጣራው ድረስ በዝግባ ሳንቃዎች ጋረደው፤ 17በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት ያለው ዋና አዳራሽ ርዝመቱ አርባ ክንድ6፥17 18 ሜትር ያህል ነው። ነበር። 18የቤተ መቅደሱም፣ ውስጡ በሙሉ በዝግባ የተለበጠ ሲሆን፣ ይህም በእንቡጥ አበቦችና በፈኩ አበቦች ቅርጽ የተጌጠ ነበር፤ በሙሉ ዝግባ እንጂ የሚታይ ድንጋይ አልነበረም።

19በቤተ መቅደሱም ውስጠኛ ክፍል የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት የሚቀመጥበትን ቅድስተ ቅዱሳን ሠራ። 20ቅድስተ ቅዱሳኑም ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ክንድ፣ ቁመቱም ሃያ ክንድ6፥20 ርዝመቱ፣ ወርዱና ቁመቱ 9 ሜትር ያህል ነው። ነበር፤ ውስጡን በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ ከዝግባ የተሠራውንም መሠዊያ በወርቅ ለበጠው። 21ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱን በውስጥ በኩል በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በወርቅ በተለበጠው ቅድስተ ቅዱሳን ፊት ለፊትም የወርቅ ሰንሰለቶች ዘረጋ። 22ስለዚህ ውስጡን በሙሉ በወርቅ ለበጠው፤ በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ያለውን መሠዊያም እንደዚሁ በወርቅ ለበጠው። 23በቅድስተ ቅዱሳኑም ውስጥ ቁመታቸው ዐሥር ክንድ6፥23 4.5 ሜትር ያህል ነው። የሆነ ሁለት የኪሩቤል ቅርጽ ከወይራ ዕንጨት ሠራ፤ 24የአንደኛው ኪሩብ አንዱ ክንፍ አምስት ክንድ ሲሆን፣ ሌላውም ክንፉ እንደዚሁ አምስት ክንድ ነበር፤ ይህም ከአንዱ ክንፍ ጫፍ እስከ ሌላው ክንፍ ጫፍ ዐሥር ክንድ ማለት ነው። 25የሁለተኛውም ኪሩብ ክንፍ እንደዚሁ ዐሥር ክንድ ሆነ፤ ሁለቱ ኪሩቤል በመጠንና በቅርጽ አንድ ዐይነት ነበሩና። 26የእያንዳንዱም ኪሩብ ቁመት ዐሥር ክንድ ነበር። 27ክንፎቻቸው እንደ ተዘረጋ፣ ኪሩቤልን ወስዶ በቅድስተ ቅዱሳኑ አኖራቸው፤ የአንዱ ኪሩብ ክንፍ አንዱን ግድግዳ ሲነካ፣ የሌላው ኪሩብ ክንፍ ደግሞ ሌላውን ግድግዳ ይነካ ነበር፤ ሌሎቹ ክንፎቻቸውም በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል እርስ በርሳቸው ይነካኩ ነበር። 28ኪሩቤልንም በወርቅ ለበጣቸው።

29በመቅደሱ ግድግዳ ዙሪያ ላይ ሁሉ በውስጥም በውጭም ኪሩቤልን፣ ከዘንባባ ዛፎችና ከፈነዱ አበቦች ጋር ቀረጸ። 30እንዲሁም የቅድስተ ቅዱሳኑንና የመቅደሱን ወለል በሙሉ በወርቅ ለበጠ።

31ለቅድስተ ቅዱሳኑም መግቢያ የወይራ ዕንጨት ደጃፎች ሠራ፤ መቃኖቻቸውንና መድረኮቻቸውን ባለ አምስት ማእዘን አደረገ። 32በሁለቱ የወይራ ዕንጨት መዝጊያዎችም ላይ ኪሩቤልን፣ የዘንባባ ዛፎችንና የፈነዱ አበቦችን ቀረጸ፤ በወርቅም ለበጣቸው። 33እንዲሁም ለዋናው አዳራሽ መግቢያ ባለ አራት ማእዘን የወይራ ዕንጨት መቃን ሠራ፤ 34እያንዳንዳቸው በማጠፊያ የተያያዙ ሁለት ሁለት ሳንቃዎች ያሏቸው ሁለት መዝጊያዎች አበጀ። 35ኪሩቤልን፣ የዘንባባ ዛፎችንና የፈኩ አበቦችንም ቀረጸባቸው፤ ቅርጹን ሠራ፤ ጥሩ አድርጎም በወርቅ ለበጠው።

36የውስጠኛውን አደባባይ በሦስት ረድፍ ጥርብ ድንጋይና በአንድ ረድፍ የዝግባ ሳንቃ ሠራው።

37የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም በአራተኛው ዓመት ዚፍ በተባለው ወር መሠረቱ ተጣለ፤ 38በዐሥራ አንደኛው ዓመት ቡል በተባለውም በስምንተኛው ወር ቤተ መቅደሱ በዝርዝር ጥናቱ መሠረት እንደ ታቀደው ተፈጸመ፤ ሠርቶ የጨረሰውም በሰባት ዓመት ጊዜ ውስጥ ነበር።

Bibelen på hverdagsdansk

1. Kongebog 6:1-38

Salomon bygger templet

1I Salomons fjerde regeringsår, i måneden ziv, det vil sige årets anden måned,6,1 Måneden ziv svarer til dansk april-maj. (Året menes at være 996 f.Kr.) påbegyndte han tempelbyggeriet—480 år efter, at Israels folk havde forladt Egypten. 2Templet blev 27 m langt, 9 m bredt og 13,5 m højt. 3Foran indgangen til templet blev der bygget en forhal, 9 m på den lange led svarende til templets bredde og 4,5 m på den korte led. 4Hele vejen rundt på tempelbygningen var der smalle vinduesåbninger.

5-6Rundt langs templets ydermur byggede Salomon en række mindre rum i tre etager. Stueetagen var 2,25 m bred, førstesalen var 2,7 m bred, og andensalen var 3,15 m bred. De bjælker der dannede gulv og loft, hvilede på nogle fremspring i tempelmuren, således at man ikke behøvede at bryde hul i muren for at lave denne tilbygning.

7Tempelbygningens sten var blevet færdighugget i stenbruddet, hvilket betød, at bygningen blev rejst i stilhed uden støj fra hamre, mejsler eller andre jernredskaber.

8Der var kun adgang til den udvendige tilbygning gennem en dør, der vendte mod syd, og trapper førte op til første og anden sal.

9Templets tag bestod af tværbjælker og planker af cedertræ. 10Det var også tværbjælker og planker af cedertræ, der forbandt tilbygningen med templet. Hver etage i tilbygningen var 2,25 m høj.

11-12Herren talte til Salomon om det tempel, han var i færd med at bygge. „Hvis du nøje følger mine instrukser og adlyder mine befalinger,” sagde han, „vil jeg opfylde det løfte, jeg gav din far, David. 13Jeg vil tage bolig iblandt mit folk Israel og ikke forlade dem.”

14Da selve tempelbygningen var færdig, fortsatte Salomon med den indvendige indretning. 15Væggene blev beklædt med cedertræspaneler fra gulv til loft, og gulvbrædderne var af cyprestræ. 16-22Der blev lavet et inderrum på 9 m gange 9 m gange 9 m. Det var det allerhelligste rum. Også det rum blev beklædt på alle sider med cedertræsplanker. Det største rum i templet, som kaldtes det hellige, blev således 18 m langt. Cedertræspaneler dækkede alle murene fuldstændigt, og de blev dekoreret med udskårne figurer af blomsterknopper og udsprungne blomster.

I templets inderste rum, det allerhelligste, blev pagtens ark anbragt. Røgelsesalteret, som skulle stå foran indgangen til det allerhelligste rum, blev lavet af cedertræ. Templets indersider blev derefter belagt med rent guld, både i det hellige og det allerhelligste. Også cedertræsalteret blev belagt med guld.

23-28I det allerhelligste rum anbragte Salomon to keruber, udskåret af vildt oliventræ. De var 4,5 m høje. Hver vinge var 2,25 m lang, og hver kerubs vingefang var således 4,5 m. De to keruber var nøjagtig ens, og de var begge belagt med guld. De var anbragt således, at deres udbredte vinger tilsammen nåede fra væg til væg, og det sted, hvor deres vingespidser rørte hinanden, var nøjagtig midt i rummet.

29Figurer, der skulle forestille keruber, palmetræer og blomster, var sirligt udskåret i panelerne i begge tempelrum, 30og selv gulvet i begge rum blev belagt med guld.

31-32Salomon lod fremstille to dørfløje af vildt oliventræ til at lukke af for det allerhelligste rum, og rammen omkring døråbningen blev lavet med en gavl, så den var en femkant.6,31-32 Teksten er vanskelig at forstå i versene 31-34. Dørene blev udsmykket med udskårne keruber, palmetræer og blomster, og det hele blev belagt med guld.

33Ved indgangen til det hellige rum lod han også lave en dørramme af vildt oliventræ, men den var firkantet. 34Der blev lavet to fløjdøre af cyprestræ, hvor hver fløj havde to dørflader, som drejede på hængsler. 35På fløjdørene lod han udskære keruber, palmetræer og blomster, som blev belagt med guld.

36Han lod bygge en mur rundt om den indre forgård med tre lag sten og et lag cedertræsbjælker.

37Tempelbyggeriet startede som sagt i årets anden måned i Salomons fjerde regeringsår, 38og det var færdigt til mindste detalje i bul måned, det vil sige den ottende måned, i Salomons 11. regeringsår. Det tog altså godt syv år at opføre templet.