1 ነገሥት 12 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

1 ነገሥት 12:1-33

እስራኤል በሮብዓም ላይ ዐመፀ

12፥1-24 ተጓ ምብ – 2ዜና 10፥1–11፥4

1እስራኤላውያን ሁሉ ሊያነግሡት ወደ ሴኬም ስለ ሄዱ፣ ሮብዓም ወደዚያው ሄደ።12፥1 ወይም በግብፅ ቀረ ተብሎ መተርጐም ይችላል። 2የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ይህን በሰማ ጊዜ፣ ከንጉሥ ሰሎሞን ሸሽቶ ከሚኖርበት ከግብፅ ተመልሶ መጣ። 3ስለዚህም ወደ ኢዮርብዓም ላኩበት፤ እርሱና መላው የእስራኤል ጉባኤም ወደ ሮብዓም መጥተው፣ 4“አባትህ ከባድ ቀንበር ጫነብን፤ አንተ ግን አሁን የአባትህን የጭካኔ አገዛዝ የጫነብንንም ከባድ ቀንበር ብታቀልልን እንገዛልሃለን” አሉት።

5ሮብዓምም፣ “እንግዲያውስ ሂዱ፤ ከሦስት ቀን በኋላ ተመልሳችሁ ወደ እኔ ኑ” አላቸው። ስለዚህ ሕዝቡ ሄዱ።

6ከዚያም ሮብዓም አባቱ ሰሎሞን በሕይወቱ ሳለ ካገለገሉት ሽማግሌዎች ጋር ተማከረ፤ “ለዚህ ሕዝብ ምን መልስ እንድሰጥ ትመክሩኛላችሁ?” አላቸው።

7እነርሱም፣ “ዛሬ አንተ ለዚህ ሕዝብ አገልጋይ ብትሆን፣ ብትገዛለትና ደስ የሚያሰኝ መልስ ብትሰጠው፣ ምንጊዜም የአንተ አገልጋይ ይሆናል” ብለው መለሱለት።

8ሮብዓም ግን ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ንቆ፣ አብሮ አደግ የሆኑትንና እርሱን የሚያገለግሉትን ወጣቶች፣ 9“ሐሳብ ለማግኘት፣ የእናንተስ ምክር ምንድን ነው? ‘አባትህ የጫነብንን ቀንበር አቅልልልን’ ለሚሉኝ ለእነዚህ ሰዎች ምን መልስ እንስጥ?” ሲል ጠየቃቸው።

10ወጣት አብሮ አደጎቹም፣ እንዲህ አሉት፣ “ ‘አባትህ ከባድ ቀንበር ጫነብን፣ አንተ ግን ቀንበራችንን አቅልልልን’ ላሉህ ለእነዚህ ሰዎች፣ ‘ትንሿ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ይልቅ ትወፍራለች፤ 11አባቴ ከባድ ቀንበር ጫነባችሁ፤ እኔ ግን ከዚያ ይብስ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ’ በላቸው!” አሉ።

12ንጉሡ፣ “በሦስተኛው ቀን ተመልሳችሁ ኑ” ብሏቸው ስለ ነበር፣ ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ በሦስተኛው ቀን ወደ ሮብዓም ተመልሰው መጡ። 13ንጉሡም በሽማግሌዎቹ የተሰጠውን ምክር ትቶ፣ ሕዝቡን የሚያስከፋ መልስ ሰጣቸው፤ 14ወጣቶቹ የሰጡትን ምክርም ተቀብሎ፣ “አባቴ ቀንበራችሁን አከበደባችሁ፤ እኔ ደግሞ ከዚያ ይብስ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በዐለንጋ ገረፋችሁ፣ እኔ ደግሞ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ” አላቸው። 15እግዚአብሔር በሴሎናዊው በአኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም የተናገረው ቀድሞውኑ እግዚአብሔር የወሰነው ስለሆነ፣ መፈጸም ነበረበትና ንጉሡ ሕዝቡን አልሰማም።

16እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ ሊሰማቸው አለመፈለጉን በተረዱ ጊዜ፣ ለንጉሡ እንዲህ በማለት መለሱ፤

“ከዳዊት ምን ድርሻ አለን?

ከእሴይስ ልጅ ምን የምናገኘው አለ?

እስራኤል ሆይ፤ ወደየድንኳንህ ተመለስ፤

ዳዊት ሆይ፤ እንግዲህ የገዛ ቤትህን ጠብቅ!”

ስለዚህም እስራኤላውያን ወደ ድንኳኖቻቸው ተመለሱ። 17ሮብዓምም በይሁዳ ምድር በሚኖሩት እስራኤላውያን ላይ ገዥ ሆነ።

18ንጉሥ ሮብዓም የጕልበት ሠራተኞች አለቃ የነበረውን አዶኒራምን12፥18 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ቅጆችና የሱርስት ትርጕሞች ከዚህ ጋር ይስማማሉ (1ነገ 4፥6 5፥14 ይመ) ዕብራይስጡ፣ አዶራም ይላል። ላከው፤ ነገር ግን እስራኤል ሁሉ በድንጋይ ወግረው ገደሉት። ንጉሡ ሮብዓም ግን እንደ ምንም ብሎ ሠረገላው ላይ በመውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሸሸ። 19ስለዚህ ሕዝቡ በዳዊት ቤት ላይ እስከ ዛሬ ድረስ እንዳመፀ ነው።

20ኢዮርብዓም መመለሱን እስራኤላውያን ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣ ወደ ጉባኤያቸው በማስጠራት በመላው እስራኤል ላይ አነገሡት። ለዳዊት ቤት በታማኝነት ጸንቶ የተገኘው የይሁዳ ቤት ብቻ ነው።

21ሮብዓም ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ፣ የእስራኤልን ቤት ወግተው መንግሥቱን ለሰሎሞን ልጅ ለሮብዓም እንዲመልሱ መላውን የይሁዳ ቤትና የብንያምን ነገድ ሰበሰበ፤ የሰራዊቱም ቍጥር አንድ መቶ ሰማንያ ሺሕ ነበር።

22ነገር ግን ይህ የአምላክ ቃል፣ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ሆነው ወደ ሳማያ መጣ፤ 23“ለይሁዳ ንጉሥ ለሰሎሞን ልጅ ለሮብዓም፣ ለመላው የይሁዳ ቤትና ለብንያም ነገድ፣ ለቀረውም ሕዝብ ሁሉ እንዲህ በል፤ 24እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ይህ ነገር ከእኔ የሆነ ነውና ወንድሞቻችሁን እስራኤላውያንን ለመውጋት አትውጡ፤ እያንዳንዳችሁ ወደየቤታችሁ ተመለሱ።’ ” ስለዚህ እግዚአብሔር እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ፤ ወደየቤታቸውም ተመለሱ።

በቤቴልና በዳን የቆሙ የወርቅ ጥጆች

25ከዚያም ኢዮርብዓም በኰረብታው አገር በኤፍሬም የምትገኘውን ሴኬምን ምሽግ አድርጎ ሠራ፤ በዚያም ተቀመጠ። ደግሞም ያንን ትቶ በመውጣት የጵኒኤልን ምሽግ ሠራ።12፥25 ዕብራይስጡ ጰኑኤል ይለዋል

26ኢዮርብዓም በልቡ እንዲህ ሲል ዐሰበ፤ “መንግሥቱ ለዳዊት ቤት የሚመለስ ይመስላል፤ 27ይህ ሕዝብ መሥዋዕት ለማቅረብ ኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚወጣ ከሆነ፣ እንደ ገና ልቡን ወደ ጌታው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓም ሊያዞር ነው። ከዚያም እኔን ይገድለኛል፤ ወደ ንጉሡም ወደ ሮብዓም ይመለሳል።”

28ንጉሡ ከመከረበት በኋላ ሁለት የወርቅ ጥጆች አሠርቶ ሕዝቡን፣ “እስራኤል ሆይ፤ ወደ ኢየሩሳሌም እስካሁን የወጣኸው ይበቃል፤ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ እነዚህ ናቸው” አለ። 29አንዱን በቤቴል ሌላውንም በዳን አቆመው። 30ይህም አድራጎት ኀጢአት ሆነ፤ ሕዝቡም በዚያ ላለው ለመስገድ እስከ ዳን ድረስ ርቆ ሄደ። 31ኢዮርብዓም በማምለኪያ ኰረብቶች ላይ አብያተ ጣዖታትን ሠራ፤ ከሕዝቡ የተለያዩ ክፍሎች ሁሉ፣ ሌዋውያን ካልሆኑት ካህናትን ሾመ። 32በይሁዳ እንደሚደረገው ሁሉ እርሱም በስምንተኛው ወር ዐሥራ አምስተኛው ቀን በዓል እንዲሆን ወሰነ፤ በመሠዊያውም ላይ መሥዋዕት አቀረበ። ለሠራቸው ጥጆች መሥዋዕት በማቅረብም እንዲህ ያለውን ድርጊት በቤቴል ፈጸመ። በማምለኪያ ኰረብቶች ላይ ላሠራቸው አብያተ ጣዖታት በቤቴል ካህናቱን መደበ። 33ራሱ በመረጠው በስምንተኛው ወር፣ በዐሥራ አምስተኛው ቀን በቤቴል ባቆመው መሠዊያ ላይ መሥዋዕት አቀረበ፤ ስለዚህ ለእስራኤላውያን በዓል ወሰነላቸው፤ ዕጣንም ለማቅረብ ወደ መሠዊያው ወጣ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

列王纪上 12:1-33

北方支派背叛罗波安

1罗波安前往示剑,因为以色列人都去了那里,要立他为王。 2尼八的儿子耶罗波安曾为了躲避所罗门王而逃往埃及,并一直住在那里。他听到消息后,便返回以色列3以色列人派人去请他,他就和以色列会众去见罗波安,说: 4“你父亲使我们负担沉重,求你减轻我们的负担吧,我们一定效忠你。”

5罗波安对他们说:“你们先回去,三天之后再来见我。”众人就离开了。

6罗波安王去征询曾服侍他父亲所罗门的老臣的意见,说:“你们认为我该怎样回复众民?” 7他们建议说:“现今王若像仆人一样服侍民众,对他们好言相待,他们会永远做王的仆人。”

8罗波安却没有采纳老臣的意见。他又去征询那些和他一起长大的青年臣僚的意见, 9说:“民众求我减轻我父亲加给他们的重担。你们认为我该怎样回复他们?”

10他们说:“民众说你父亲使他们负担沉重,请求你减轻他们的负担。你可以这样回复他们,‘我的小指头比我父亲的腰还粗。 11我父亲使你们负重担,我要使你们负更重的担子;我父亲用鞭子打你们,我要用刺鞭打你们。’”

12过了三天,耶罗波安和民众遵照罗波安王的话来见他。 13-14王没有采纳老臣的建议,而是照青年臣僚的建议,疾言厉色地对他们说:“我父亲使你们负重担,我要使你们负更重的担子!我父亲用鞭子打你们,我要用刺鞭打你们!” 15王不听民众的请求。这事是出于耶和华的旨意,为要应验祂借示罗亚希雅先知对尼八的儿子耶罗波安说的话。

16以色列人见王不听他们的请求,就说:

“我们与大卫有何相干?

我们与耶西的儿子没有关系!

以色列人啊,各自回家吧!

大卫家啊,自己照顾自己吧!”

于是,以色列人各自回家了。 17但住在犹大城邑的以色列人仍受罗波安统治。 18罗波安王派劳役总管亚多兰以色列人那里,以色列人却用石头打死了他,罗波安王连忙上车逃回耶路撒冷19从此,以色列人反叛大卫家,一直到今天。 20以色列人听说耶罗波安回来了,就请他到会众面前,拥立他做以色列人的王。只有犹大支派仍然效忠大卫家。

21罗波安回到耶路撒冷,从犹大便雅悯支派召集了十八万精兵,要攻打以色列人,收复全国。 22然而,上帝对祂的仆人示玛雅说: 23“你去告诉所罗门的儿子犹大罗波安犹大便雅悯支派的人以及其他民众, 24耶和华这样说,‘你们不要上去与以色列同胞交战,都回家吧!今日的景况是出于我的旨意。’”众人听从了耶和华的话,各自回家去了。

耶罗波安背弃上帝

25耶罗波安以法莲山区修建示剑城,住在那里。他后来又去修建毗努伊勒26他心想:“国权恐怕会重归大卫家。 27若百姓去耶路撒冷,在耶和华的殿献祭,他们的心必重新归向他们的主——犹大罗波安。他们会杀了我,然后投奔犹大罗波安。” 28他征询臣僚的意见后,就铸造了两个金牛犊,对民众说:“以色列人啊,你们上耶路撒冷敬拜太麻烦了。这两个金牛犊就是领你们出埃及的神明。” 29他把一个金牛犊安置在伯特利,另一个安置在30这使民众陷入罪中,因为他们开始到去拜金牛犊。

31耶罗波安又在高岗上修建神庙,任命各样的人做祭司,他们并非利未人。 32耶罗波安规定每年八月十五日为节期,好像犹大的节期一样。他自己在伯特利的祭坛上向金牛犊献祭烧香,又派神庙的祭司在献祭中司职。 33在八月十五日,就是他私自为以色列人定为节期的日子,他在伯特利的祭坛上烧香。