ፊልጵስዩስ 2 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ፊልጵስዩስ 2:1-30

ትሕትናን ከክርስቶስ መማር

1ከክርስቶስ ጋር ካላችሁ አንድነት የተነሣ የትኛውም መበረታታት፣ ከፍቅር የሆነ መጽናናት፣ የመንፈስ ኅብረት፣ ምሕረትና ርኅራኄ ካላችሁ፣ 2በአንድ ሐሳብ፣ በአንድ ፍቅር፣ በአንድ መንፈስና በአንድ ዐላማ በመሆን ደስታዬን ፍጹም አድርጉልኝ። 3ሌሎች ከእናንተ እንደሚሻሉ በትሕትና ቍጠሩ እንጂ፣ በራስ ወዳድነት ምኞት ወይም ከንቱ ውዳሴ ለማግኘት አንዳች አታድርጉ። 4እያንዳንዳችሁ ሌሎችን የሚጠቅመውንም እንጂ፣ ራሳችሁን የሚጠቅመውን ብቻ አትመልከቱ።

5በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረው ያ አስተሳሰብ፣ በእናንተም ዘንድ ይሁን፤

6እርሱ በባሕርዩ2፥6 ወይም መልክ አምላክ ሆኖ ሳለ፣

ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን ሊለቅቀው እንደማይገባ አድርጎ አልቈጠረውም፤

7ነገር ግን የባሪያን መልክ2፥7 ወይም ባሕርይ ይዞ፣

በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣

ራሱን ባዶ አደረገ፤

8ሰው ሆኖ ተገልጦም፣

ራሱን ዝቅ አደረገ፤

እስከ ሞት፣ ያውም በመስቀል ላይ እስከ

መሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ።

9ስለዚህ እግዚአብሔር እጅግ ከፍ አደረገው፤

ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጠው፤

10ይኸውም በሰማይና በምድር፣ ከምድርም በታች፣

ጕልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይንበረከክ ዘንድ፣

11ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር፣

ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።

እንደ ከዋክብት ማብራት

12ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ፤ ሁልጊዜም ታዛዦች እንደ ነበራችሁ ሁሉ፣ አሁንም እኔ በአጠገባችሁ ሳለሁ ብቻ ሳይሆን፣ ይልቁንም አሁን በሌለሁበት ጊዜ በፍርሀትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤ 13እንደ በጎ ፈቃዱ መፈለግንና ማድረግን በእናንተ ውስጥ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።

14ማንኛውንም ነገር ሳታጕረመርሙና ሳትከራከሩ አድርጉ፤ 15ይኸውም በጠማማና በክፉ ትውልድ መካከል ንጹሓንና ያለ ነቀፋ፣ ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች ሆናችሁ፣ እንደ ከዋክብት በዓለም ሁሉ ታበሩ ዘንድ ነው። 16የሕይወትንም ቃል ስታቀርቡ2፥16 ስትይዙ፣ በከንቱ እንዳልሮጥሁ ወይም በከንቱ እንዳልደከምሁ በክርስቶስ ቀን የምመካበት ይሆንልኛል። 17ነገር ግን በእምነታችሁ መሥዋዕትና አገልግሎት ላይ እንደ መጠጥ ቍርባን ብፈስስ እንኳ ከሁላችሁ ጋር ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አደርጋለሁ። 18እናንተም እንደዚሁ ከእኔ ጋር ደስ ልትሰኙና ሐሤት ልታደርጉ ይገባል።

ጢሞቴዎስና አፍሮዲጡ

19ስለ እናንተ ሰምቼ ደስ እንዲለኝ፣ ጢሞቴዎስን ቶሎ ወደ እናንተ ልልክላችሁ በጌታ ኢየሱስ ተስፋ አደርጋለሁ። 20ስለ እናንተ ደኅንነት ከልቡ የሚገድደው እንደ እርሱ ያለ ማንም የለኝም፤ 21ሁሉም የኢየሱስ ክርስቶስን ሳይሆን የራሳቸውን ፍላጎት ለማሟላት ይሯሯጣሉና። 22ነገር ግን እንደምታውቁት ጢሞቴዎስ ማንነቱን አስመስክሯል፤ ልጅ ከአባቱ ጋር እንደሚያገለግል፣ ከእኔ ጋር በወንጌል ሥራ አገልግሏልና። 23እንግዲህ የራሴን የወደ ፊት ሁኔታ እንዳጣራሁ ልልከው ተስፋ አደርጋለሁ። 24እኔም ራሴ ቶሎ እንደምመጣ በጌታ ታምኛለሁ።

25እንዲሁም ወንድሜን፣ የሥራ ባለደረባዬንና አብሮኝ ወታደር የሆነውን፣ በሚያስፈልገኝ ሁሉ እንዲንከባከበኝ የላካችሁትን፣ የእናንተ መልእክተኛ የሆነውን አፍሮዲጡን መልሼ እንድልክላችሁ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። 26እርሱ ሁላችሁንም ይናፍቃልና፤ መታመሙን ስለ ሰማችሁም ተጨንቋል። 27በርግጥም ታምሞ ለሞት ተቃርቦ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ምሕረት አደረገለት፤ በሐዘን ላይ ሐዘን እንዳይደራረብብኝ ለእኔም ጭምር እንጂ ለእርሱ ብቻ አይደለም። 28ስለዚህ እርሱን እንደ ገና ስታዩ ደስ እንዲላችሁና የእኔም ጭንቀት እንዲቀልል ልልከው በጣም ጓጕቻለሁ። 29በሙሉ ደስታ በጌታ ተቀበሉት፤ እንደ እርሱ ያሉትንም ሰዎች አክብሯቸው። 30እርሱም እናንተ ልትሰጡኝ ያልቻላችሁትን አገልግሎት ለማሟላት ሲል ለሕይወቱ እንኳ ሳይሳሳ፣ ለክርስቶስ ሥራ ከሞት አፋፍ ደርሶ ነበርና።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

腓立比书 2:1-30

效法基督

1所以,如果你们在基督里受到鼓励,得到爱的安慰,与圣灵相通,有慈悲和怜悯之心, 2就要同心合意,彼此相爱,灵里合一,思想一致,好让我的喜乐更充足。 3凡事不可自私自利、爱慕虚荣,要心存谦卑,看别人比自己强。 4各人不要只顾自己的事,也要为别人的需要着想。 5你们应当有基督耶稣那样的心肠。

6祂虽然本质上是上帝,

却没有紧紧抓住自己与上帝平等的地位不放,

7反而甘愿放下一切,

取了奴仆的形象,

降生为人的样子。

8祂以人的样子出现后,

就自愿卑微,顺服至死,

而且死在十字架上。

9因此,上帝将祂升为至尊,

赐给祂超乎万名之上的名,

10使一切天上的、

地上的和地底下的,

无不屈膝跪拜在耶稣的名下,

11无不口称耶稣基督是主,

将荣耀归于父上帝。

暗世明灯

12所以,我亲爱的弟兄姊妹,既然我在你们那里的时候,你们一向都很顺服;如今我不在你们那里,你们更要顺服,要战战兢兢地活出得救后应有的生命。 13因为你们立志和行事都是上帝在你们心中工作,为要成就祂美好的旨意。

14无论做什么事,都不要抱怨,也不要与人争论, 15好使你们在这个弯曲败坏的时代中无可指责、诚实无伪,做上帝纯洁无瑕的儿女,如同明光照耀在世上, 16坚守生命之道。这样,到了基督再来的时候,我可以夸口自己没有空跑一场,也没有白费功夫。 17你们的信心就是献给上帝的事奉和祭物,即使在上面浇奠我的生命,我也很喜乐,并且和你们大家一同喜乐。 18同样,你们也要喜乐,要和我一同喜乐。

保罗的得力同工

19如果主耶稣许可,我希望尽快派提摩太去你们那里,我好知道你们的近况,心里得到安慰。 20因为没有人像他那样跟我一同真正关心你们的事。 21别人都只顾自己的事,并不关心耶稣基督的事。 22但你们知道提摩太的为人,我与他情同父子,一起事奉和传扬福音。 23所以,我的案子一旦明朗了,我会立刻派他去见你们。 24我深信如果主许可,我自己很快也会去你们那里。

25另外,我觉得有必要让以巴弗提回到你们那里。他是我的弟兄、同工和战友,也是你们差遣来服侍我、供应我需用的。 26他很想念你们,并且感到不安,因为你们听说了他患病的事。 27他确实病了,几乎丧命,但上帝怜悯了他,不但怜悯他,也怜悯了我,没让我忧上加忧。 28所以,我想尽快派他回去与你们相聚,好让你们喜乐,也可以减少我的挂虑。 29你们要在主里欢欢喜喜地接待他,而且要敬重像他这样的人。 30他为了基督的工作,将生死置之度外,几乎丧命,以弥补你们服侍我的不足之处。