ገላትያ 6 – NASV & KJV

New Amharic Standard Version

ገላትያ 6:1-18

ለሰው ሁሉ በጎ ማድረግ

1ወንድሞች ሆይ፤ አንድ ሰው በኀጢአት ውስጥ ገብቶ ቢገኝ፣ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ በገርነት ልትመልሱት ይገባል። ነገር ግን አንተም እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ። 2አንዱ የሌላውን ከባድ ሸክም ይሸከም፤ በዚህም ሁኔታ የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ። 3አንድ ሰው ምንም ሳይሆን ትልቅ የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላል። 4እያንዳንዱ የራሱን ተግባር ይመርምር፤ ከዚያም በኋላ፣ ከሌላ ሰው ጋር ራሱን ሳያወዳድር፣ ስለ ራሱ የሚመካበትን ያገኛል፤ 5እያንዳንዱ የራሱን ሸክም ሊሸከም ይገባዋልና።

6ማንም ቃሉን የሚማር፣ መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ ከመምህሩ ጋር ይካፈል።

7አትታለሉ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳል። 8ሥጋዊ ምኞቱን ለማርካት የሚዘራ፣ ከሥጋ6፥8 ወይም ኀጢአተኛ ተፈጥሮውን ለማርካት የሚዘራ፣ ከዚሁ ተፈጥሮ ጥፋትን ያጭዳል፤ መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል። 9በጎ ነገር ከማድረግ አንታክት፤ ተስፋ ካልቈረጥን ጊዜው ሲደርስ መከሩን እናጭዳለን። 10ስለዚህ ዕድሉ ካለን ለሰው ሁሉ፣ በተለይም ለእምነት ቤተ ሰቦች መልካም እናድርግ።

አዲስ ፍጥረት መሆን

11እንዴት ባሉ ታላላቅ ፊደላት በእጄ እንደ ጻፍሁላችሁ ተመልከቱ።

12ውጫዊ በሆነ ነገር ለመታየት የሚፈልጉ ሰዎች ትገረዙ ዘንድ ሊያስገድዷችሁ ይጥራሉ፤ ይህንም የሚያደርጉት ስለ ክርስቶስ መስቀል እንዳይሰደዱ ነው። 13እነርሱ በሥጋችሁ ለመመካት ሲሉ እንድትገረዙ ፈለጉ እንጂ፣ የተገረዙት ራሳቸው እንኳ ሕግን የሚጠብቁ አይደሉም። 14ነገር ግን ዓለም ለእኔ ከተሰቀለበት፣ እኔም ለዓለም ከተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር፣ ሌላው ትምክሕት ከእኔ የራቀ ይሁን። 15መገረዝም ሆነ አለመገረዝ አይጠቅምም፤ የሚጠቅመው አዲስ ፍጥረት መሆን ነው። 16ይህን ትእዛዝ በሚከተሉ ሁሉ፣ የእግዚአብሔር በሆነው እስራኤልም ላይ ሰላምና ምሕረት ይሁን።

17እኔ የኢየሱስን ምልክት በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና፣ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አያስቸግረኝ።

18ወንድሞች ሆይ፤ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።

King James Version

Galatians 6:1-18

1Brethren, if a man be overtaken in a fault, ye which are spiritual, restore such an one in the spirit of meekness; considering thyself, lest thou also be tempted. 2Bear ye one another’s burdens, and so fulfil the law of Christ. 3For if a man think himself to be something, when he is nothing, he deceiveth himself. 4But let every man prove his own work, and then shall he have rejoicing in himself alone, and not in another. 5For every man shall bear his own burden. 6Let him that is taught in the word communicate unto him that teacheth in all good things. 7Be not deceived; God is not mocked: for whatsoever a man soweth, that shall he also reap. 8For he that soweth to his flesh shall of the flesh reap corruption; but he that soweth to the Spirit shall of the Spirit reap life everlasting. 9And let us not be weary in well doing: for in due season we shall reap, if we faint not. 10As we have therefore opportunity, let us do good unto all men, especially unto them who are of the household of faith. 11Ye see how large a letter I have written unto you with mine own hand. 12As many as desire to make a fair shew in the flesh, they constrain you to be circumcised; only lest they should suffer persecution for the cross of Christ. 13For neither they themselves who are circumcised keep the law; but desire to have you circumcised, that they may glory in your flesh. 14But God forbid that I should glory, save in the cross of our Lord Jesus Christ, by whom the world is crucified unto me, and I unto the world. 15For in Christ Jesus neither circumcision availeth any thing, nor uncircumcision, but a new creature. 16And as many as walk according to this rule, peace be on them, and mercy, and upon the Israel of God. 17From henceforth let no man trouble me: for I bear in my body the marks of the Lord Jesus. 18Brethren, the grace of our Lord Jesus Christ be with your spirit. Amen.