ገላትያ 1 – NASV & KJV

New Amharic Standard Version

ገላትያ 1:1-24

1ከሰዎች ወይም በሰው ከተላከው ሳይሆን፣ በኢየሱስ ክርስቶስና ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፤ 2አብረውኝም ካሉት ወንድሞች ሁሉ፤

በገላትያ ላሉት አብያተ ክርስቲያናት፤

3ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። 4እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ፣ ከዚህ ክፉ ዓለም ያድነን ዘንድ ስለ ኀጢአታችን ራሱን ሰጠ፤ 5ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ክብር ይሁን፤ አሜን።

ወንጌል አንዲት ናት

6በክርስቶስ ጸጋ የጠራችሁን እርሱን ትታችሁ፣ ወደ ተለየ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ መዞራችሁ ደንቆኛል፤ 7እንደ እውነቱ ከሆነ ሌላ ወንጌል የለም። የሚያደነጋግሯችሁና የክርስቶስን ወንጌል ለማጣመም ጥረት የሚያደርጉ አንዳንድ ሰዎች አሉ። 8ነገር ግን እኛም ብንሆን ወይም የሰማይ መልአክ፣ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የተለየ ወንጌል ቢሰብክላችሁ እርሱ ለዘላለም የተረገመ ይሁን። 9ቀደም ብለን እንዳልነው፣ አሁንም ደግሜ እላለሁ፤ ማንም ከተቀበላችሁት ሌላ የተለየ ወንጌል ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።

10አሁን እኔ ጐሽ ለመባል የምሻው በሰዎች ዘንድ ነው ወይስ በእግዚአብሔር ዘንድ? ወይስ ሰዎችን ደስ ለማሰኘት እየተጣጣርሁ ነው? ሰዎችን ደስ ለማሰኘት የምጥር ብሆን ኖሮ፣ የክርስቶስ አገልጋይ ባልሆንሁ ነበር።

ጳውሎስ በእግዚአብሔር መጠራቱ

11ወንድሞች ሆይ፤ የሰበክሁላችሁ ወንጌል ሰው ሠራሽ አለመሆኑን እንድታውቁ እፈልጋለሁ፤ 12ከማንም ሰው አልተቀበልሁትም፤ ከማንም አልተማርሁትም፤ ይልቁንስ በመገለጥ ከኢየሱስ ክርስቶስ ተቀበልሁት።

13ቀድሞ በአይሁድ ሃይማኖት እንዴት እንደ ኖርሁ፣ የእግዚአብሔርንም ቤተ ክርስቲያን እንዴት በእጅጉ እንዳሳደድሁ፣ ለማጥፋትም እንዴት እንደ ጣርሁ ሰምታችኋል። 14በእኔ ዕድሜ ዘመን ከነበሩት ከብዙዎቹ አይሁድ ይበልጥ በአይሁድ ሃይማኖት እልቅ ነበር፤ ስለ አባቶቼም ወግ እጅግ ቀናተኛ ነበርሁ። 15ነገር ግን፣ ከእናቴ ማሕፀን1፥15 ወይም ከመወለዴ ጀምሮ የለየኝና በጸጋው የጠራኝ እግዚአብሔር፣ 16በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ እንድሰብክ ልጁን በእኔ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፣ ከማንም ሥጋ ለባሽ ጋር አልተማከርሁም፤ 17ከእኔ በፊት ሐዋርያት ወደሆኑትም ወደ ኢየሩሳሌም አልወጣሁም፤ ነገር ግን ወዲያው ወደ ዐረብ አገር ሄድሁ፤ በኋላም ወደ ደማስቆ ተመለስሁ።

18ከዚያም ከሦስት ዓመት በኋላ፣ ጴጥሮስን1፥18 ግሪኩ ኬፋ ይለዋል። አገኘው ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣሁ፤ ከእርሱም ጋር ዐሥራ አምስት ቀን ተቀመጥሁ። 19ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ በቀር፣ ከሐዋርያት ማንንም አላየሁም። 20በምጽፍላችሁ ነገር በእግዚአብሔር ፊት ሐሰት እንደማልናገር አስረግጬ እነግራችኋለሁ። 21ከዚያም በኋላ፣ ወደ ሶርያና ወደ ኪልቅያ አገር ሄድሁ። 22በክርስቶስ ያሉት የይሁዳ አብያተ ክርስቲያናትም ፊቴን አይተው አያውቁም ነበር፤ 23እነርሱ ግን፣ “ቀድሞ እኛን ሲያሳድድ የነበረ ሰው፣ ከዚህ በፊት ሊያጠፋው ይፈልግ የነበረውን እምነት አሁን እየሰበከ ነው” የሚለውን ወሬ ብቻ ሰምተው ነበር፤ 24በእኔም ምክንያት እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

King James Version

Galatians 1:1-24

1Paul, an apostle, (not of men, neither by man, but by Jesus Christ, and God the Father, who raised him from the dead;) 2And all the brethren which are with me, unto the churches of Galatia: 3Grace be to you and peace from God the Father, and from our Lord Jesus Christ, 4Who gave himself for our sins, that he might deliver us from this present evil world, according to the will of God and our Father: 5To whom be glory for ever and ever. Amen.

6I marvel that ye are so soon removed from him that called you into the grace of Christ unto another gospel: 7Which is not another; but there be some that trouble you, and would pervert the gospel of Christ. 8But though we, or an angel from heaven, preach any other gospel unto you than that which we have preached unto you, let him be accursed. 9As we said before, so say I now again, If any man preach any other gospel unto you than that ye have received, let him be accursed.

10For do I now persuade men, or God? or do I seek to please men? for if I yet pleased men, I should not be the servant of Christ. 11But I certify you, brethren, that the gospel which was preached of me is not after man. 12For I neither received it of man, neither was I taught it, but by the revelation of Jesus Christ. 13For ye have heard of my conversation in time past in the Jews’ religion, how that beyond measure I persecuted the church of God, and wasted it: 14And profited in the Jews’ religion above many my equals in mine own nation, being more exceedingly zealous of the traditions of my fathers. 15But when it pleased God, who separated me from my mother’s womb, and called me by his grace, 16To reveal his Son in me, that I might preach him among the heathen; immediately I conferred not with flesh and blood: 17Neither went I up to Jerusalem to them which were apostles before me; but I went into Arabia, and returned again unto Damascus. 18Then after three years I went up to Jerusalem to see Peter, and abode with him fifteen days. 19But other of the apostles saw I none, save James the Lord’s brother. 20Now the things which I write unto you, behold, before God, I lie not. 21Afterwards I came into the regions of Syria and Cilicia; 22And was unknown by face unto the churches of Judaea which were in Christ: 23But they had heard only, That he which persecuted us in times past now preacheth the faith which once he destroyed. 24And they glorified God in me.