ዮናስ 3 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዮናስ 3:1-10

ዮናስ ወደ ነነዌ ሄደ

1የእግዚአብሔርም ቃል ለሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል ወደ ዮናስ መጣ፤

2“ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሄደህ የምነግርህን መልእክት ስበክላት።”

3ዮናስም የእግዚአብሔርን ቃል ታዘዘ፤ ወደ ነነዌም ሄደ። በዚህ ጊዜ ነነዌ ታላቅ ከተማ ነበረች፤ እርሷንም ከዳር እስከ ዳር ለመጐብኘት ሦስት ቀን ያስፈልግ ነበር። 4ዮናስም ወደ ከተማዪቱ ገብቶ የመጀመሪያውን ቀን ከተጓዘ በኋላ “ነነዌ በአርባ ቀን ውስጥ ትገለበጣለች” ብሎ ዐወጀ። 5የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ጾምንም ዐወጁ፤ ሰዎቹም ሁሉ ከትልቁ እስከ ትንሹ ማቅ ለበሱ።

6ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ በደረሰ ጊዜ፣ ከዙፋኑ ወረደ፤ ልብሱንም አወለቀ፤ ማቅም ለብሶ በዐመድ ላይ ተቀመጠ። 7ከዚያም እንዲህ ሲል በነነዌ ዐዋጅ አስነገረ፤

“ከንጉሡና ከመሳፍንቱ የወጣ ዐዋጅ፤

“ማንም ሰው ወይም እንስሳ፣ የከብት መንጋም ሆነ የበግ መንጋ፣ ምንም ነገር አይቅመስ፤ አይብላ፤ ውሃም አይጠጣ። 8ነገር ግን ሰውም እንስሳም ማቅ ይልበስ፤ ሁሉም አጥብቆ ወደ እግዚአብሔር ይጩኽ፤ ሰዎችም ሁሉ ክፉ መንገዳቸውንና የግፍ ሥራቸውን ይተዉ። 9እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ራርቶ ከጽኑ ቍጣው ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?”

10እግዚአብሔርም ምን እንዳደረጉና ከክፉ መንገዳቸውም እንዴት እንደ ተመለሱ ባየ ጊዜ ራራላቸው፤ በእነርሱም ላይ ሊያመጣ ያሰበውን ጥፋት አላደረገም።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

约拿书 3:1-10

1耶和华第二次对约拿说: 2“你起身前往尼尼微大城,向那里的居民宣告我先前吩咐你的话。” 3约拿便照耶和华的吩咐前往尼尼微城。尼尼微城很大,要三天才能走遍。 4约拿进城走了一天,宣告说:“再过四十天尼尼微就要毁灭了!” 5尼尼微城的人相信了上帝的话,便宣告禁食,所有的人,无论大小贵贱都换上麻衣。 6尼尼微王听到这消息后,便走下宝座,脱下王袍,披上麻衣,坐在炉灰中。 7王又向全城颁布命令,说:“王和大臣有令,所有的人都必须禁食,牛羊牲畜都不许吃草也不许喝水。 8人和牲畜都必须披上麻衣,众人要向上帝恳切呼求,改邪归正,停止作恶。 9上帝或许会施怜悯,收回烈怒,使我们不致灭亡,也未可知。” 10上帝看见他们改邪归正,不再作恶,就怜悯他们,没有像所说的那样毁灭他们。