ዮሐንስ 8 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዮሐንስ 8:1-59

በምንዝር የተያዘች ሴት

1ኢየሱስ ግን ወደ ደብረ ዘይት ሄደ። 2በማለዳም በቤተ መቅደስ አደባባይ እንደ ገና ታየ፤ ሕዝቡም በዙሪያው ተሰበሰበ፤ ሊያስተምራቸውም ተቀመጠ። 3የኦሪት ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን በምንዝር የተያዘች ሴት አመጡ፤ በሕዝቡም ፊት አቁመዋት፣ 4ኢየሱስን እንዲህ አሉት፤ “መምህር ሆይ፣ ይህች ሴት ስታመነዝር ተያዘች፤ 5ሙሴም፣ እንደዚች ያሉ ሴቶች በድንጋይ እንዲወገሩ በሕጉ አዝዞናል፤ አንተስ ምን ትላለህ?” 6ይህን ጥያቄ ያቀረቡለት፣ እርሱን የሚከስሱበት ምክንያት ለማግኘት ሲፈትኑት ነው።

ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ይጽፍ ጀመር። 7በጥያቄ ሲወተውቱት ቀና ብሎ፣ “ከእናንተ ኀጢአት የሌለበት እርሱ አስቀድሞ ድንጋይ ይወርውርባት” አላቸው። 8እንደ ገናም ጐንበስ ብሎ በምድር ላይ ጻፈ።

9ይህን እንደ ሰሙ፣ ከሽማግሌዎች ጀምሮ አንድ በአንድ ወጡ፤ ሴትዮዋም እዚያው ፊቱ እንደ ቆመች ኢየሱስ ብቻውን ቀረ። 10ኢየሱስም ቀና ብሎ፣ “አንቺ ሴት፣ ሰዎቹ የት ሄዱ? የፈረደብሽ የለምን?” አላት።

11እርሷም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንድም የለም” አለች።

ኢየሱስም፣ “እኔም አልፈርድብሽም፤ በይ ሂጂ፤ ከእንግዲህ ግን ኀጢአት አትሥሪ” አላት።8፥11 ብዙ የጥንት ቅጆች ይህ ክፍል (7፥53–8፥11) የላቸውም፤ ወይም በሌላ ስፍራ ወይም በሌሎች ወንጌሎች ያስገቡታል።

የኢየሱስ ምስክርነት እውነት መሆኑ

12ኢየሱስ እንደ ገና ለሰዎቹ፣ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝም የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ ከቶ በጨለማ አይመላለስም” አላቸው።

13ፈሪሳውያንም፣ “አንተ ስለ ራስህ ስለምትመሰክር ምስክርነትህ ተቀባይነት የለውም” አሉት።

14ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ከየት እንደ መጣሁና ወዴት እንደምሄድ ስለማውቅ ምስክርነቴ እውነት ነው፤ እናንተ ግን ከየት እንደ መጣሁ ወይም ወዴት እንደምሄድ የምታውቁት ነገር የለም። 15እናንተ እንደ ሰው አስተሳሰብ ትፈርዳላችሁ፤ እኔ በማንም አልፈርድም፤ 16ብፈርድም፣ ከላከኝ ከአብ ጋር እንጂ ብቻዬን ስላልሆንሁ ፍርዴ ትክክል ነው። 17የሁለት ሰዎች ምስክርነት ተቀባይነት እንዳለው በሕጋችሁ ተጽፏል። 18ስለ ራሴ የምመሰክር አንዱ እኔ ነኝ፤ ሌላውም ምስክሬ የላከኝ አብ ነው።”

19ከዚያም፣ “አባትህ የት ነው?” አሉት።

ኢየሱስም፣ “አባቴንም እኔንም አታውቁም፤ እኔን ብታውቁኝ ኖሮ፣ አባቴንም ባወቃችሁ ነበር” ሲል መለሰላቸው። 20ኢየሱስ ይህን የተናገረው በቤተ መቅደሱ ግቢ፣ በግምጃ ቤት አጠገብ ሲያስተምር ነበር፤ ይሁን እንጂ ጊዜው ገና ስላልደረሰ ማንም አልያዘውም።

21ኢየሱስም እንደ ገና፣ “እኔ እሄዳለሁ፤ እናንተም ትፈልጉኛላችሁ፤ በኀጢአታችሁም ትሞታላችሁ፤ እኔ ወደምሄድበት ግን ልትመጡ አትችሉም” አላቸው።

22አይሁድም፣ “ ‘እኔ ወደምሄድበት ልትመጡ አትችሉም’ ያለው ራሱን ሊገድል ይሆን?” አሉ።

23እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ከታች ናችሁ፤ እኔ ከላይ ነኝ፤ እናንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፤ እኔ ከዚህ ዓለም አይደለሁም። 24በኀጢአታችሁ እንደምትሞቱ ነግሬአችኋለሁ፤ እኔ እርሱ ነኝ8፥24 ወይም ያ ያልሁት እርሱ እኔ ነኝ፤ እንዲሁም 28 ይመ ስላችሁ እኔ እርሱ እንደ ሆንሁ ካላመናችሁ፣ በኀጢአታችሁ ትሞታላችሁና።”

25እነርሱም፣ “ለመሆኑ፣ አንተ ማን ነህ?” አሉት።

ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እስካሁን የነገርኋችሁ እኔ እርሱ ነኝ፤ 26በእናንተ ላይ ብዙ የምናገረውና ብዙ የምፈርደው ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ ታማኝ ነው፤ ከእርሱም የሰማሁትን ለዓለም እናገራለሁ።”

27እነርሱም ስለ አብ እየነገራቸው እንደ ነበር አላስተዋሉም። 28ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “የሰው ልጅን ከፍ ከፍ ባደረጋችሁት ጊዜ፣ ያ ያልሁት እርሱ እኔ እንደ ሆንሁና አብ ያስተማረኝን እንደምናገር፣ በራሴም ፈቃድ ምንም እንደማላደርግ ታውቃላችሁ፤ 29የላከኝ እርሱ ከእኔ ጋር ነው፤ ምንጊዜም የሚያስደስተውን ስለማደርግ ብቻዬን አልተወኝም።” 30ይህንም እንደ ተናገረ ብዙዎች በእርሱ አመኑ።

የአብርሃም ልጆች

31ኢየሱስም በእርሱ ያመኑትን አይሁድ እንዲህ አላቸው፤ “በትምህርቴ ብትጸኑ እናንተ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤ 32እውነትንም ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል።”

33እነርሱም መልሰው፣ “እኛ የአብርሃም ልጆች ነን8፥33 በግሪኩ ዘር ይላል፤ 37 ይመ፤ ለማንም ባሪያዎች ሆነን አናውቅም፤ ታዲያ፣ ‘ነጻ ትወጣላችሁ’ እንዴት ትለናለህ?” አሉት።

34ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ኀጢአት የሚያደርግ የኀጢአት ባሪያ ነው፤ 35ባሪያ ለዘለቄታ በቤተ ሰቡ ውስጥ አይኖርም፤ ልጅ ግን ምንጊዜም በቤት ይኖራል። 36እንግዲህ ወልድ ነጻ ካወጣችሁ፣ በእውነት ነጻ ትሆናላችሁ። 37የአብርሃም ልጆች መሆናችሁን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ቃሌን ስለማትቀበሉ ልትገድሉኝ ቈርጣችሁ ተነሥታችኋል። 38እኔ በአባቴ ዘንድ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተም ከአባታችሁ የሰማችሁትን ታደርጋላችሁ።”8፥38 ወይም ስለዚህ ከአባታችሁ የሰማችሁትን አድርጉ

39እነርሱም፣ “አባታችንስ አብርሃም ነው” ብለው መለሱለት።

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “የአብርሃም ልጆችስ ብትሆኑ8፥39 አንዳንድ የጥንት ቅጆች የአብርሃም ልጆች ከሆናችሁ ይላሉ።፣ አብርሃም የሠራውን ትሠሩ ነበር። 40ከእግዚአብሔር ሰምቼ እውነቱን የነገርኋችሁን እኔን ለመግደል ቈርጣችሁ ተነሥታችኋል፤ አብርሃም ግን እንዲህ አላደረገም። 41እናንተ የምታደርጉት አባታችሁ የሚያደርገውን ነው።”

እነርሱም፣ “እኛስ በዝሙት የተወለድን አይደለንም፤ አባታችንም አንዱ እግዚአብሔር ብቻ ነው” ሲሉ መለሱለት።

የዲያብሎስ ልጆች

42ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር አባታችሁ ቢሆን ኖሮ፣ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ መጥቻለሁና፣ በወደዳችሁኝ ነበር፤ እርሱ ላከኝ እንጂ በገዛ ራሴ አልመጣሁም። 43የምናገረውን ለምን አታስተውሉም? ምክንያቱም ቃሌን መስማት ስለማትችሉ ነው። 44እናንተ የአባታችሁ የዲያብሎስ ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፍላጎት ለመፈጸም ትሻላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበር፤ በእርሱ ዘንድ እውነት ስለሌለ በእውነት አልጸናም፤ እርሱ ሐሰተኛ፣ የሐሰትም አባት በመሆኑ ሐሰትን ሲናገር፣ የሚናገረው ከራሱ አፍልቆ ነው፤ 45እኔ ግን እውነት ስለምናገር አታምኑኝም። 46ከእናንተ ስለ ኀጢአት በማስረጃ ሊከስሰኝ የሚችል አለን? እውነት የምናገር ከሆነ፣ ለምን አታምኑኝም? 47ከእግዚአብሔር የሆነ እግዚአብሔር የሚለውን ይሰማል፤ እናንተ ግን ከእግዚአብሔር ስላልሆናችሁ አትሰሙም።”

ኢየሱስ ስለ ራሱ የተናገረው

48አይሁድም መልሰው፣ “አንተ ሳምራዊ ነህ፤ ደግሞም ጋኔን ዐድሮብሃል ማለታችን ትክክል አይደለምን?” አሉት።

49ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እኔስ አባቴን አከብረዋለሁ እንጂ ጋኔን አላደረብኝም፤ እናንተ ግን ታዋርዱኛላችሁ። 50እኔ የራሴን ክብር አልፈልግም፤ የሚፈልግ ግን አለ፤ ፈራጁም እርሱ ነው። 51እውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ቃሌን ቢጠብቅ፣ ሞትን ፈጽሞ አያይም።”

52አይሁድም እንዲህ አሉት፤ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን ዐወቅን፤ አብርሃም ሞተ፤ ነቢያትም እንዲሁ፤ አንተ ግን ማንም ቃልህን ቢጠብቅ ሞትን ፈጽሞ እንደማይቀምስ ትናገራለህ። 53አንተ ከአባታችን ከአብርሃም ትበልጣለህን? እርሱ ሞተ፤ ነቢያቱም እንዲሁ፤ ለመሆኑ አንተ ማን ነኝ ልትል ነው?”

54ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ ራሴን ባከብር፣ ክብሬ ከንቱ ነው፤ የሚያከብረኝ ግን እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው። 55እናንተ ባታውቁትም እኔ ዐውቀዋለሁ፤ አላውቀውም ብል፣ እኔም እንደ እናንተው ሐሰተኛ እሆናለሁ። እኔ ግን ዐውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ። 56አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ለማየት ተስፋ በማድረግ ተደሰተ፤ አየም፤ ሐሤትም አደረገ።”

57አይሁድም፣ “ገና አምሳ ዓመት ያልሞላህ፣ አንተ አብርሃምን አይተሃል!” አሉት።

58ኢየሱስም፣ “እውነት እላችኋለሁ፤ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ፣ እኔ ነኝ” አላቸው። 59በዚህን ጊዜ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወረባቸው፤ ከቤተ መቅደስም ወጥቶ ሄደ።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

约翰福音 8:1-59

淫妇获赦

1众人都回家去了,耶稣却上了橄榄山。 2第二天清晨,祂又回到圣殿。百姓聚集在祂那里,祂就坐下来教导他们。 3这时候,律法教师和法利赛人带来一个通奸时被捉的女人,让她站在众人面前, 4然后问耶稣:“老师,这个女人是在通奸时被捉到的。 5摩西的律法,我们要用石头把她打死,你说该怎么处置她呢?”

6他们这样问是要使耶稣落在他们的圈套里,可以有借口控告祂。耶稣却只是弯着腰用指头在地上写字。 7他们不断地追问耶稣,于是祂直起腰来,对他们说:“你们中间谁没有罪,谁就先拿石头打她吧。” 8说完,又弯下腰在地上写字。

9他们听了这句话,就从老到少一个一个地走了,只剩下耶稣和那个女人在那里。 10耶稣直起腰来,说:“妇人,他们到哪里去了?没有人定你的罪吗?”

11她说:“主啊,没有。”

耶稣说:“我也不定你的罪。回去吧,从今以后不要再犯罪了。”

世界的光

12耶稣又对众人说:“我是世界的光,凡跟从我的,必不会走在黑暗里,必要得到生命的光。”

13法利赛人对祂说:“你自己为自己做见证,你的见证不真实。”

14耶稣说:“即便我自己为自己做见证,我的见证仍是真实的,因为我知道自己从哪里来、要到哪里去,你们却不知道我从哪里来、要到哪里去。 15你们只凭外表判断别人,我却不判断人。 16就算我判断人,我的判断也是正确的,因为我不是独自一人,还有差我来的父与我同在。 17你们的律法不是说两个人做见证就有效吗? 18我是自己为自己做见证,差我来的父也为我做见证。”

19他们问:“你的父在哪里?”

耶稣回答说:“你们不认识我,也不认识我的父。如果你们认识我,也会认识我的父。” 20耶稣在圣殿的库房这样教导人,但没有人抓祂,因为祂的时候还没有到。

警告不信的人

21耶稣又对他们说:“我要走了,你们会寻找我,你们将死在自己的罪中。我去的地方,你们不能去。”

22犹太人说:“祂说祂去的地方我们不能去,难道祂想自杀吗?”

23耶稣对他们说:“你们是从下面来的,我是从上面来的。你们属于这世界,我不属于这世界。 24所以我说你们将死在自己的罪中,你们如果不相信我就是8:24 耶稣用“我就是”这个词提醒听众祂就是出埃及记3:14节提到的那位自有永有的上帝,8:28同。那一位,一定会死在自己的罪中。”

25他们问:“你到底是谁?”

耶稣回答说:“我不是早就告诉你们了吗? 26关于你们,我有许多要说、要审判的,但差我来的那位是真实的,我把从祂那里听到的告诉世人。” 27他们不明白耶稣是指着父说的。

28于是耶稣说:“你们举起人子以后,必知道我就是那一位,并且知道我没有一件事是凭自己做的,我所说的都是父教导我的。 29差我来的那位跟我在一起,祂没有撇下我,让我孤单一人,因为我做的都是祂所喜悦的。” 30许多人因为这番话而信了耶稣。

真正的自由

31耶稣对信祂的犹太人说:“你们若持守我的道,就真是我的门徒了。 32你们必认识真理,真理必叫你们得到自由。”

33他们说:“我们是亚伯拉罕的子孙,从来没有做过奴隶,你为什么说我们可以得到自由呢?”

34耶稣说:“我实实在在地告诉你们,所有犯罪的人都是罪的奴隶。 35奴隶不能永远留在主人的家里,只有儿子才可以。 36所以,如果上帝的儿子释放了你们,你们就真正自由了!

耶稣和亚伯拉罕

37“我知道你们是亚伯拉罕的子孙,但你们却想杀我,因为你们心里容不下我的道。 38我所说的,是我从父那里看到的,你们却照着你们父8:38 犹太文化中,“父”可指生身的父,亦可泛指祖先。的话去做。”

39他们说:“我们的父就是亚伯拉罕!”

耶稣说:“你们如果真是亚伯拉罕的子孙,一定会做他所做的事。 40我把从上帝那里听到的真理告诉你们,你们反要杀我,亚伯拉罕绝不做这样的事。 41你们是在做你们父所做的事。”

他们说:“我们不是从淫乱生的!我们只有一位父,就是上帝。”

42耶稣说:“如果上帝是你们的父,你们一定会爱我,因为我来自上帝。如今我在这里,我不是凭自己来的,而是上帝差我来的, 43你们为什么不明白我的话呢?因为你们听不进去我的道。 44你们是出于你们的父魔鬼,你们乐意顺着它的私欲行。魔鬼从起初就是个杀人凶手,从不站在真理这一边,因为它心里根本没有真理。撒谎是它的本性,因为它是撒谎者,又是撒谎者的始祖。 45所以,我讲真理的时候,你们不信我。 46你们谁能指证我有罪呢?我既然把真理告诉了你们,你们为什么还不信我呢? 47出于上帝的人听上帝的话,你们不听上帝的话,因为你们不是出于上帝。”

48犹太人对祂说:“我们说你是撒玛利亚8:48 撒玛利亚人血统不纯,常被犹太人藐视,并当作骂人的话。,被鬼附身了,难道不对吗?”

49耶稣说:“我没有被鬼附身。我尊敬我的父,你们却侮辱我。 50我不为自己寻求荣耀,但有一位会为我寻求,祂也会断定谁是谁非。 51我实实在在地告诉你们,人如果遵行我的道,必永远不死。”

52那些犹太人说:“现在我们的确知道你是被鬼附身了!亚伯拉罕和众先知都死了,你还说人如果遵行你的道,必永远不死。 53难道你比我们的祖先亚伯拉罕还大吗?他死了,先知们也死了,你以为你是谁?”

54耶稣说:“如果我为自己争取荣耀,那荣耀算不了什么。但使我得荣耀的是我的父,你们也称祂为你们的上帝。 55你们不认识祂,我却认识祂。如果我说我不认识祂,那我就像你们一样是说谎的。然而,我认识祂,并且遵行祂的道。 56你们的祖先亚伯拉罕曾经欢欢喜喜地盼望看见我来的日子。他看见了,就欢喜快乐。”

57犹太人说:“你还不到五十岁,怎么会见过亚伯拉罕呢?”

58耶稣说:“我实实在在地告诉你们,亚伯拉罕还没有出生,我就已经存在了8:58 我就已经存在了”希腊文是“我是”,参见8:24注。。” 59于是,他们就拿起石头要打祂,耶稣却避开他们,离开了圣殿。