ዘፍጥረት 40 – NASV & PCB

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 40:1-23

የመጠጥ አሳላፊውና የእንጀራ ቤቱ

1ከዚህም በኋላ የግብፅ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊና እንጀራ ቤቱ ጌታቸውን የግብፅን ንጉሥ በደሉት። 2ፈርዖንም በመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና በእንጀራ ቤቱ አዛዥ፣ በሁለቱም ሹማምቱ ላይ ክፉኛ ተቈጣ፤ 3በዘበኞቹ አለቃ ቤት ወዳለው ዮሴፍ ወደ ተጋዘበትም እስር ቤት አስገባቸው።

4የዘበኞቹም አለቃ እስረኞቹን ለዮሴፍ አስረከባቸው፤ ዮሴፍም በሚያስፈልጋቸው ይረዳቸው ነበር።

እስር ቤት ገብተው ጥቂት እንደ ቈዩም፣ 5ታስረው የነበሩት የግብፅ የንጉሥ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ ቤቱ አዛዥ፣ በአንድ ሌሊት የየራሳቸውን ሕልም አዩ፤ የሁለቱም ሕልም ለየራሱ የተለየ ፍቺ ነበረው።

6በማግስቱም ጧት ዮሴፍ ወደ እነርሱ ሲገባ ተክዘው አገኛቸው። 7ስለዚህም፣ “ምነው ዛሬስ ፊታችሁ ላይ ሐዘን ይነበባል?” በማለት አብረውት በጌታው ግቢ የታሰሩትን የፈርዖን ሹማምት ጠየቃቸው።

8እነርሱም “ሁለታችንም ሕልም አየን፤ ነገር ግን የሚተረጕምልን ሰው አጣን” ሲሉ መለሱለት።

ዮሴፍም፣ “ሁልጊዜስ ቢሆን የሕልም ትርጓሜ ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም) የሚገኝ አይደለምን? እስቲ ያያችሁትን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።

9ስለዚህ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ እንዲህ ሲል ሕልሙን ለዮሴፍ ነገረው፤ “ከፊት ለፊቴ አንዲት የወይን ተክል አየሁ፤ 10ተክሏም ሦስት ሐረጎች ነበሯት፤ ወዲያው አቈጥቍጣ አበበች፤ ዘለላዎቿም ተንዠርግገው በሰሉ። 11የፈርዖንንም ጽዋ ይዤ ነበረ፤ የወይኑን ፍሬ ለቅሜ በጽዋው ውስጥ ጨምቄ ጽዋውን በእጁ ሰጠሁት።”

12ዮሴፍም እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ የሕልሙ ትርጓሜ ይህ ነው፤ ሦስቱ ሐረግ ሦስት ቀን ነው፤ 13በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ከእስር ቤት ያወጣሃል፣ ወደ ቀድሞ ሹመትህም ይመልስሃል፤ በፊት የመጠጥ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ታደርግ እንደ ነበረው ሁሉ የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጣለህ። 14እንግዲህ፣ በጎ ነገር በገጠመህ ጊዜ፣ እኔን አስበህ ቸርነት አድርግልኝ፤ ስለ እኔም ለፈርዖን ንገርልኝ፤ ከዚህም እስር ቤት አስወጣኝ፤ 15ከዕብራውያን ምድር ወደዚህ የመጣሁት በዐፈና ነው፤ አሁንም ቢሆን እዚህ እስር ቤት የተጣልሁት አንዳች ጥፋት ኖሮብኝ አይደለም።”

16የእንጀራ ቤት አዛዡም፣ ለመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ሕልም፣ የተሰጠው ፍቺ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን ሲሰማ፣ የራሱን ሕልም ለዮሴፍ እንዲህ ሲል ነገረው፤ “እኔም ደግሞ ሕልም አይቻለሁ፤ ሦስት መሶቦች40፥16 ወይም ሦስት የሸንበቆ ቅርጫቶች በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤ 17በላይኛው መሶብ ውስጥ ለፈርዖን የተዘጋጀ የተለያየ ምግብ ነበረበት፤ ወፎችም ራሴ ላይ ካለው መሶብ ይበሉ ነበር።”

18ዮሴፍም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፤ ሦስቱ መሶብ ሦስት ቀን ነው፤ 19በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ከእስር ቤት ያወጣሃል፤ በዕንጨትም ላይ ይሰቅልሃል፤40፥19 ወይም በእንጨትም ላይ ይወጋሃል ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።”

20በሦስተኛውም ቀን የፈርዖን የልደት በዓል ነበረ፤ ለሹማምቱም ሁሉ ግብር አበላ። በዚያኑ ዕለትም የመጠጥ አሳላፊዎችን አለቃና የእንጀራ ቤት አዛዡን ሹማምቱ ባሉበት ከእስር ቤት አወጣቸው።

21የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃ ወደ ቀድሞ ሹመቱ መለሰው፤ እርሱም እንደ ቀድሞው ጽዋውን ለፈርዖን በእጁ ይሰጠው ጀመር። 22የእንጀራ ቤት አዛዡን ግን ልክ ዮሴፍ እንደ ተረጐመላቸው ሰቀለው።40፥22 ወይም ወጋው

23የሆነው ሆኖ፣ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ረሳው እንጂ።

Persian Contemporary Bible

پيدايش 40:1‏-23

يوسف خواب زندانيان را تعبير می‌كند

1‏-3مدتی پس از زندانی شدن يوسف، فرعون رئيس نانوايان و رئيس ساقيان خود را به زندان انداخت، زيرا خشم او را برانگيخته بودند. آنها را به زندان فوطيفار، رئيس محافظان دربار كه يوسف در آنجا بود انداختند. 4آنها مدت درازی در زندان ماندند و فوطيفار يوسف را به خدمت آنها گماشت. 5يک شب هر دو آنها خواب ديدند. 6صبح روز بعد، يوسف ديد كه آنها ناراحت هستند. 7پس، از آنها پرسيد: «چرا امروز غمگين هستيد؟»

8گفتند: «ديشب ما هر دو خواب ديديم و كسی نيست كه آن را تعبير كند.»

يوسف گفت: «تعبير كردن خوابها كار خداست. به من بگوييد چه خوابهايی ديده‌ايد؟»

9‏-10اول رئيس ساقيان خوابی را كه ديده بود، چنين تعريف كرد: «ديشب در خواب درخت انگوری را ديدم كه سه شاخه داشت. ناگاه شاخه‌ها شكفتند و خوشه‌های زيادی انگور رسيده دادند. 11من جام شراب فرعون را در دست داشتم، پس خوشه‌های انگور را چيده، در جام فشردم و به او دادم تا بنوشد.»

12يوسف گفت: «تعبير خواب تو اين است: منظور از سه شاخه، سه روز است. 13تا سه روز ديگر فرعون تو را از زندان آزاد كرده، دوباره ساقی خود خواهد ساخت. 14پس خواهش می‌كنم وقتی دوباره مورد لطف او قرار گرفتی، مرا به ياد آور و سرگذشتم را برای فرعون شرح بده و از او خواهش كن تا مرا از اين زندان آزاد كند. 15زيرا مرا كه عبرانی هستم از وطنم دزديده، به اينجا آورده‌اند. حالا هم بدون آنكه مرتكب جرمی شده باشم، مرا در زندان انداخته‌اند.»

16وقتی رئيس نانوايان ديد كه تعبير خواب دوستش خير بود، او نيز خواب خود را برای يوسف بيان كرده، گفت: «در خواب ديدم كه سه سبد پر از نان روی سر خود دارم. 17در سبد بالايی چندين نوع نان برای فرعون گذاشته بودم، اما پرندگان آمده آنها را خوردند.»

18‏-19يوسف به او گفت: «مقصود از سه سبد، سه روز است. سه روز ديگر فرعون سرت را از تنت جدا كرده، بدنت را به دار می‌آويزد و پرندگان آمده گوشت بدنت را خواهند خورد.»

20سه روز بعد، جشن تولد فرعون بود و به همين مناسبت ضيافتی برای مقامات مملكتی ترتيب داد. او فرستاد تا رئيس ساقيان و رئيس نانوايان را از زندان به حضورش آورند. 21سپس رئيس ساقيان را به كار سابقش گمارد، 22ولی رئيس نانوايان را به دار آويخت، همانطور كه يوسف گفته بود. 23اما رئيس ساقيان يوسف را به ياد نياورد.