ዘፍጥረት 25 – NASV & NIRV

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 25:1-34

የአብርሃም መሞት

25፥1-4 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥32-33

1አብርሃም ኬጡራ የተባለች ሌላ ሚስት አገባ።25፥1 ወይም አግብቶ ነበር 2እርሷም፦ ዘምራንን፣ ዮቅሳንን፣ ሜዳንን፣ ምድያምን፣ የስቦቅንና ስዌሕን ወለደችለት። 3ዮቅሳንም ሳባንና ድዳንን ወለደ፤ የድዳንም ልጆች፦ አሦራውያን፣ ለጡሳውያንና ለኡማውያን ናቸው። 4የምድያም ልጆች፦ ጌፌር፣ ዔፌር፣ ሄኖኅ፣ አቢዳዕና ኤልዳድ ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው።

5አብርሃም ያለውን ሀብት ሁሉ ለይስሐቅ አወረሰው፤ 6ለቁባቶቹ ልጆች ግን በሕይወት እያለ ስጦታ አደረገላቸው፤ ከልጁ ከይስሐቅም ርቀው እንዲኖሩ ወደ ምሥራቅ ምድር ሰደዳቸው።

7አብርሃም በጠቅላላው መቶ ሰባ አምስት ዓመት ኖረ። 8ከዚያም ዐረፈ፤ ዕድሜ ጠግቦ በመልካም ሽምግልና ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ። 9ልጆቹ ይስሐቅና እስማኤል በመምሬ አጠገብ በምትገኝ በኬጢያዊው በሰዓር ልጅ በኤፍሮን ዕርሻ በመክፈላ ዋሻ ቀበሩት፤ 10ይህም የዕርሻ ቦታ አብርሃም ከኬጢያውያን25፥10 ወይም የኬጢ ልጆች የገዛው ነበር፤ ከሚስቱ ከሣራ አጠገብ በዚያ ተቀበረ። 11አብርሃም ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ይስሐቅን ባረከው፤ በዚህ ጊዜ ይስሐቅ በብኤርላሃይሮኢ አቅራቢያ ይኖር ነበር።

የእስማኤል ልጆች

25፥12-16 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥29-31

12ግብፃዊቷ የሣራ አገልጋይ አጋር፣ ለአብርሃም የወለደችለት የእስማኤል ትውልድ ይህ ነው።

13የእስማኤል ልጆች ስም እንደ ዕድሜያቸው ቅደም ተከተል እንዲህ ነው፦

የእስማኤል በኵር ልጅ ነባዮት፣

ቄዳር፣ ነብዳኤል፣ መብሳም፣

14ማስማዕ፣ ዱማ፣ ማሣ፣

15ኩዳን፣ ቴማን፣ ኢጡር፣

ናፌስና ቄድማ።

16እነዚህ የእስማኤል ልጆች ነበሩ፤ እነርሱም በኖሩባቸውና በሰፈሩባቸው ቦታዎች የዐሥራ ሁለት ነገድ አለቆች ስሞች ናቸው።

17እስማኤል በጠቅላላው መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ። 18ዘሮቹም መኖሪያቸውን ከግብፅ ድንበር አጠገብ፣ ወደ አሦር በሚወስደው መንገድ፣ በኤውላጥና በሱር መካከል አደረጉ፤ ከወንድሞቻቸውም ሁሉ ጋር በጠላትነት ኖሩ።25፥18 ወይም በስተ ምሥራቅ ኖሩ

ያዕቆብና ዔሳው

19የአብርሃም ልጅ የይስሐቅ ትውልድ ይህ ነው፤

አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ 20ይስሐቅ ርብቃን ሲያገባ ዕድሜው አርባ ዓመት ነበር፤ ርብቃ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ የሚኖረው የሶርያዊው የባቱኤል ልጅ፣ የሶርያዊውም የላባ እኅት ነበረች።

21ይስሐቅ፣ ርብቃ መካን ስለ ነበረች ስለ እርሷ ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ጸለየ፤ እግዚአብሔርም (ያህዌ) ጸሎቱን ሰማ፤ ርብቃም ፀነሰች። 22ልጆቹም በማሕፀኗ ውስጥ እርስ በርሳቸው ይጋፉ ጀመር፤ እርሷም “ለምን እንዲህ ይሆንብኛል?” ብላ እግዚአብሔርን (ያህዌ) ለመጠየቅ ሄደች።

23እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲህ አላት፤

“ወገኖች በማሕፀንሽ አሉ፤

ሁለትም ሕዝቦች ከውስጥሽ ተለያይተው ይወጣሉ፤

አንደኛው ከሌላው ይበረታል፤

ታላቁም ለታናሹ አገልጋይ ይሆናል” አላት።

24የመውለጃዋ ጊዜ ሲደርስም፣ እነሆ፤ በማሕፀኗ መንታ ወንዶች ልጆች ነበሩ። 25በመጀመሪያ የተወለደው መልኩ ቀይ፣ ሰውነቱም በሙሉ ጠጕር የለበሰ ነበር፤ ስለዚህ ስሙ ዔሳው25፥25 ዔሳው ማለት ጠጕራማ ማለት ነው፤ በተጨማሪ ኤዶም ተብሎ ተጠርቷል፤ ትርጕሙም ቀይ ማለት ነው። ተባለ። 26ከዚያም ወንድሙ ተወለደ፤ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ወጣ፤ ከዚህም የተነሣ ስሙ ያዕቆብ25፥26 ያዕቆብ ማለት ተረከዝ ይይዛል ማለት ነው፤ በምሳሌያዊ አገላለጽ ያታልላል ማለት ነው። ተባለ። ርብቃ ልጆቿን ስትወልድ፣ ይስሐቅ የስድሳ ዓመት ሰው ነበር።

27ልጆቹም ዐደጉ፤ ዔሳው ጐበዝ ዐዳኝ፣ የበረሓም ሰው ሆነ፤ ያዕቆብ ግን ጭምት፣ ከድንኳኑ የማይወጣ ሰው ነበር። 28ይስሐቅ ከዐደን የመጣ ሥጋ ደስ ይለው ስለ ነበር፣ ዔሳውን ይወድደው ነበር፤ ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድደው ነበር።

29አንድ ቀን ያዕቆብ ወጥ እየሠራ ሳለ ዔሳው እጅግ ተርቦ ከዱር መጣ። 30ዔሳውም ያዕቆብን፣ “ቶሎ በል፤ በጣም ርቦኛልና ከዚህ ቀይ ወጥ አብላኝ” አለው። ስለዚህም ስሙ ኤዶም ተባለ።

31ያዕቆብም፣ “በመጀመሪያ ብኵርናህን ሽጥልኝ” አለው።

32ዔሳውም፣ “እነሆ፤ ልሞት ደርሻለሁ፤ ታዲያ ብኵርናው ምን ያደርግልኛል!” አለ።

33ያዕቆብም ዔሳውን፣ “እንግዲያማ፣ አስቀድመህ ማልልኝ” አለው፤ ስለዚህም ማለለት፤ ብኵርናውንም ለያዕቆብ ሸጠለት።

34ያዕቆብም ለዔሳው እንጀራና የምስር ወጥ ሰጠው፤ እርሱም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ።

ዔሳው ብኵርናውን እንዲህ አድርጎ አቃለላት።

New International Reader’s Version

Genesis 25:1-34

Abraham Dies

1Abraham had married another woman. Her name was Keturah. 2She had Zimran, Jokshan, Medan, Midian, Ishbak and Shuah by Abraham. 3Jokshan was the father of Sheba and Dedan. The children of Dedan were the Ashurites, the Letushites and the Leummites. 4The sons of Midian were Ephah, Epher, Hanok, Abida and Eldaah. All of them were members of Keturah’s family line.

5Abraham left everything he owned to Isaac. 6But while he was still living, he gave gifts to the sons of his concubines. Then he sent them away from his son Isaac. He sent them to the land of the east.

7Abraham lived a total of 175 years. 8He took his last breath and died when he was very old. He had lived a very long time. Then he joined the members of his family who had already died. 9Abraham’s sons Isaac and Ishmael buried him. They put his body in the cave of Machpelah near Mamre. It was in the field of Ephron, the son of Zohar the Hittite. 10Abraham had bought the field from the Hittites. He was buried there with his wife Sarah. 11After Abraham died, God blessed his son Isaac. At that time Isaac was living near Beer Lahai Roi.

The Sons of Ishmael

12Here is the story of the family line of Abraham’s son Ishmael. Hagar gave birth to Ishmael by Abraham. Hagar was Sarah’s slave from Egypt.

13Here are the names of the sons of Ishmael. They are listed in the order they were born.

Nebaioth was Ishmael’s oldest son.

Then came Kedar, Adbeel, Mibsam,

14Mishma, Dumah, Massa,

15Hadad, Tema, Jetur,

Naphish and Kedemah.

16All of them were Ishmael’s sons. They were rulers of 12 tribes. They all lived in their own settlements and camps.

17Ishmael lived a total of 137 years. Then he took his last breath and died. He joined the members of his family who had already died. 18His children settled in the area between Havilah and Shur. It was near the eastern border of Egypt, as you go toward Ashur. Ishmael’s children weren’t friendly toward any of the tribes related to them.

Jacob and Esau

19Here is the story of the family line of Abraham’s son Isaac.

Abraham was the father of Isaac. 20Isaac was 40 years old when he married Rebekah. She was the daughter of Bethuel, the Aramean from Paddan Aram. She was also the sister of Laban, the Aramean.

21Rebekah couldn’t have children. So Isaac prayed to the Lord for her. And the Lord answered his prayer. His wife Rebekah became pregnant. 22The babies struggled with each other inside her. She said, “Why is this happening to me?” So she went to ask the Lord what she should do.

23The Lord said to her,

“Two nations are in your body.

Two tribes that are now inside you will be separated.

One nation will be stronger than the other.

The older son will serve the younger one.”

24The time came for Rebekah to have her babies. There were twin boys in her body. 25The first one to come out was red. His whole body was covered with hair. So they named him Esau. 26Then his brother came out. His hand was holding onto Esau’s heel. So he was named Jacob. Isaac was 60 years old when Rebekah had them.

27The boys grew up. Esau became a skillful hunter. He liked the open country. But Jacob was content to stay at home among the tents. 28Isaac liked the meat of wild animals. So Esau was his favorite son. But Rebekah’s favorite was Jacob.

29One day Jacob was cooking some stew. Esau came in from the open country. He was very hungry. 30He said to Jacob, “Quick! I’m very hungry! Let me have some of that red stew!” That’s why he was also named Edom.

31Jacob replied, “First sell me the rights that belong to you as the oldest son in the family.”

32“Look, I’m dying of hunger,” Esau said. “What good are those rights to me?”

33But Jacob said, “First promise to sell me your rights.” So Esau promised to do it. He sold Jacob all the rights that belonged to him as the oldest son.

34Then Jacob gave Esau some bread and some lentil stew. Esau ate and drank. Then he got up and left.

So Esau didn’t value the rights that belonged to him as the oldest son.