ዘፍጥረት 2 – NASV & NIVUK

New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 2:1-25

1የሰማያትና የምድር፣ በውስጣቸውም ያሉት ሁሉ አፈጣጠር በዚህ ሁኔታ ተከናወነ።

2እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ይሠራ የነበረውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ላይ ፈጽሞ ነበር፤ ስለዚህ ከሠራው ሥራ ሁሉ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ።2፥2 ወይም አቆመ፤ በ3 ላይም እንዲሁ፤ 3እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ሰባተኛውን ቀን ባረከው፤ ቀደሰውም፤ ካከናወነው የመፍጠር ሥራው ሁሉ ያረፈው በሰባተኛው ቀን ነውና።

አዳምና ሔዋን

4እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ሰማያትንና ምድርን በፈጠረ ጊዜ የተከናወኑት እንደዚህ ነበረ፤ እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ሰማያትንና ምድርን ሲፈጥር 5የሜዳ ቡቃያ ገና በምድር2፥5 ወይም መሬት፤ በ6 ላይም እንዲሁ ላይ አልታየም፤ የሜዳ ተክልም ገና አልበቀለም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) በመሬት ላይ ገና ዝናብ አላዘነበም ነበር፤ ምድርንም የሚያለማ ሰው አልነበረም። 6ነገር ግን ውሃ2፥6 ወይም ጭጋግ ከመሬት እየመነጨ የምድርን ገጽ ያረሰርስ ነበር። 7እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ከምድር ዐፈር ወስዶ ሰውን2፥7 በዕብራይስጥ ሰው (አዳም) የሚለው ቃል፣ ምድር (አዳማኽ) ከሚለው ቃል ጋር በድምፅ ይመሳሰላል፤ በፍቺም ሳይዛመድ አይቀርም፤ አዳም የመጀመሪያው ሰው ስምም ነው። ዘፍ 2፥20 ይመ አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ሆነ።

8እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) በምሥራቅ፣ በዔድን የአትክልት ስፍራ አዘጋጀ፤ ያበጀውንም ሰው በዚያ አኖረው። 9እግዚአብሔር አምላክም (ያህዌ ኤሎሂም) ለዐይን የሚያስደስት ለመብልም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በአትክልቱ ቦታ መካከልም የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ እንዲሁም መልካምና ክፉን መለየት የሚያስችለው የዕውቀት ዛፍ ነበረ።

10የአትክልት ስፍራውን የሚያጠጣ ወንዝ ከዔድን ይፈስስ ነበር፤ ከዚያም በአራት ተከፍሎ ይወጣ ነበር። 11የመጀመሪያው፣ ወርቅ በሚገኝበት በሐዊላ ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈስሰው የፊሶን ወንዝ ነው። 12ኤውላጥ ምርጥ የሆነ ወርቅ፣ መልካም መዐዛ2፥12 ወይም መልካም ዕንቁ ያለው ከርቤና የከበረ ድንጋይ የሚገኙበት ምድር ነው። 13ሁለተኛው፣ በኢትዮጵያ2፥13 ደቡብ ምሥራቅ መስጴጦምያ ሊሆን ይችላል። ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈስሰው የግዮን ወንዝ ነው። 14ሦስተኛው፣ ከአሦር በስተ ምሥራቅ የሚፈስሰው የጤግሮስ ወንዝ ሲሆን፣ አራተኛው የኤፍራጥስ ወንዝ ነው።

15እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ሰውን ወስዶ እንዲያለማትና እየተንከባከበ እንዲጠብቃት በዔድን የአትክልት ስፍራ አስቀመጠው። 16እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ሰውን እንዲህ በማለት አዘዘው፤ “በአትክልት ስፍራው ውስጥ ከሚገኝ ከማንኛውም ዛፍ ፍሬ ትበላለህ። 17ነገር ግን መልካምና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ፤ ምክንያቱም ከእርሱ በበላህ ቀን በርግጥ ትሞታለህ።”

18ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም)፣ “ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለምና የሚስማማውን ረዳት አበጅለታለሁ” አለ።

19እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) የዱር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ከምድር ሠርቶ ነበር፤ ለእያንዳንዳቸውም ምን ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው። አዳም ሕይወት ላላቸው ፍጡራን ሁሉ ያወጣላቸው ስም መጠሪያቸው ሆነ። 20ስለዚህ አዳም2፥20 ወይም ሰው ለከብቶች፣ ለሰማይ ወፎች፣ ለዱር አራዊት ሁሉ ስም አወጣላቸው።

ይሁን እንጂ ለአዳም ተስማሚ ረዳት አልተገኘለትም ነበር። 21እግዚአብሔር አምላክም (ያህዌ ኤሎሂም) በአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ ጣለበት፤ አንቀላፍቶም ሳለ ከጐድኑ አንዲት ዐጥንት2፥21 ወይም ከሰው የጐን ክፍል ወስዶ ወስዶ፣ ስፍራውን በሥጋ ሞላው። 22እግዚአብሔር አምላክ (ያህዌ ኤሎሂም) ከአዳም የወሰዳትን ዐጥንት2፥22 ወይም ክፍል ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት።

23አዳምም እንዲህ አለ፤

“እነሆ፤ ይህች ዐጥንት ከዐጥንቴ፣

ሥጋም ከሥጋዬ ናት።

ከወንድ ተገኝታለችና ሴት2፥23 ሰው የሚል ትርጕም ያለው የዕብራይስጥ ቃል ሴት የሚል ትርጕም ካለው የዕብራይስጥ ቃል ጋር ተመሳሳይ ድምፅ አለው። ትባል።”

24ስለዚህ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ተለይቶ ከሚስቱ ጋር ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።

25አዳምና ሚስቱ፣ ሁለቱም ዕራቍታቸውን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ አይተፋፈሩም ነበር።

New International Version – UK

Genesis 2:1-25

1Thus the heavens and the earth were completed in all their vast array.

2By the seventh day God had finished the work he had been doing; so on the seventh day he rested from all his work. 3Then God blessed the seventh day and made it holy, because on it he rested from all the work of creating that he had done.

Adam and Eve

4This is the account of the heavens and the earth when they were created, when the Lord God made the earth and the heavens.

5Now no shrub had yet appeared on the earth2:5 Or land; also in verse 6 and no plant had yet sprung up, for the Lord God had not sent rain on the earth and there was no-one to work the ground, 6but streams2:6 Or mist came up from the earth and watered the whole surface of the ground. 7Then the Lord God formed a man2:7 The Hebrew for man (adam) sounds like and may be related to the Hebrew for ground (adamah); it is also the name Adam (see verse 20). from the dust of the ground and breathed into his nostrils the breath of life, and the man became a living being.

8Now the Lord God had planted a garden in the east, in Eden; and there he put the man he had formed. 9The Lord God made all kinds of trees grow out of the ground – trees that were pleasing to the eye and good for food. In the middle of the garden were the tree of life and the tree of the knowledge of good and evil.

10A river watering the garden flowed from Eden; from there it was separated into four headwaters. 11The name of the first is the Pishon; it winds through the entire land of Havilah, where there is gold. 12(The gold of that land is good; aromatic resin2:12 Or good; pearls and onyx are also there.) 13The name of the second river is the Gihon; it winds through the entire land of Cush.2:13 Possibly south-east Mesopotamia 14The name of the third river is the Tigris; it runs along the east side of Ashur. And the fourth river is the Euphrates.

15The Lord God took the man and put him in the Garden of Eden to work it and take care of it. 16And the Lord God commanded the man, ‘You are free to eat from any tree in the garden; 17but you must not eat from the tree of the knowledge of good and evil, for when you eat from it you will certainly die.’

18The Lord God said, ‘It is not good for the man to be alone. I will make a helper suitable for him.’

19Now the Lord God had formed out of the ground all the wild animals and all the birds in the sky. He brought them to the man to see what he would name them; and whatever the man called each living creature, that was its name. 20So the man gave names to all the livestock, the birds in the sky and all the wild animals.

But for Adam2:20 Or the man no suitable helper was found. 21So the Lord God caused the man to fall into a deep sleep; and while he was sleeping, he took one of the man’s ribs2:21 Or took part of the man’s side and then closed up the place with flesh. 22Then the Lord God made a woman from the rib2:22 Or part he had taken out of the man, and he brought her to the man.

23The man said,

‘This is now bone of my bones

and flesh of my flesh;

she shall be called “woman”,

for she was taken out of man.’

24That is why a man leaves his father and mother and is united to his wife, and they become one flesh.

25Adam and his wife were both naked, and they felt no shame.