ዘፀአት 34 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዘፀአት 34:1-35

አዲሶቹ የድንጋይ ጽላቶች

1እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን አለው፤ “እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጥረብ፤ እኔም አንተ በሰበርካቸው በመጀመሪያዎቹ ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ። 2በማለዳ ተዘጋጅተህ ወደ ሲና ተራራ ውጣ፤ በዚያ በተራራው ጫፍ ላይ በፊቴ ቁም፤ 3ከአንተ ጋር ማንም እንዳይመጣ ወይም በተራራው ላይ በየትኛውም ቦታ እንዳይታይ፤ የበግና የፍየል መንጋዎች የቀንድ ከብቶችም እንኳ፣ በተራራው ፊት ለፊት መጋጥ የለባቸውም።”

4ስለዚህ ሙሴ እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠርቦ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው በማለዳ ወደ ሲና ተራራ ወጣ፤ ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶችም በእጆቹ ያዘ። 5ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) በደመና ወረደ፤ በዚያም ከእርሱ ጋር ቆሞ ስሙን እግዚአብሔርን (ያህዌ) ዐወጀ። 6እርሱም በሙሴ ፊት እንዲህ እያለ እያወጀ ዐለፈ፤ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ርኅሩኅ ቸር አምላክ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩና ታማኝነቱ የበዛ፣ 7ፍቅርን ለሺዎች የሚጠብቅ፣ ክፋትን፣ ዐመፅንና ኀጢአትን ይቅር የሚል፣ በደለኛውን ግን ሳይቀጣ ዝም ብሎ አይተውም፤ በአባቶች ኀጢአት ልጆችን የልጅ ልጆቻቸውን እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ይቀጣል።”

8ሙሴም ወዲያውኑ ወደ መሬት ዝቅ ብሎ ሰገደ፤ 9“አቤቱ ጌታ (አዶናይ) ሆይ፤ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ ጌታ (አዶናይ) ከእኛ ጋር ይሂድ፤ ይህ ዐንገተ ደንዳና ሕዝብ ቢሆንም እንኳ፣ ክፋታችንንና ኀጢአታችንን ይቅር በል፤ እንደ ርስትህም አድርገህ ውሰደን።”

10ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዲህ አለ፤ “ከአንተ ጋር ኪዳን እገባለሁ፤ ከዚህ ቀደም በዓለም ሁሉ ለየትኛውም ሕዝብ ከቶ ያልተደረገ፣ በሕዝብህ ሁሉ ፊት ድንቅ አደርጋለሁ፤ በመካከላቸው አብረሃቸው የምትኖር ሕዝብ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ለአንተ የማደርግልህ ሥራ የቱን ያህል አስፈሪ እንደ ሆነ ያያሉ። 11ዛሬ የማዝህን ፈጽም፤ አሞራውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ ኬጢያውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኤዊያውያንንና ኢያቡሳውያንን በፊትህ አስወጣቸዋለሁ። 12ከምትሄድበት አገር ነዋሪዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ አለዚያ በመካከልህ ወጥመድ ይሆኑብሃል። 13መሠዊያዎቻቸውን ሰባብሩ፤ የማምለኪያ ዐምዶቻቸውን አድቅቁ34፥13 አሼራ የምትባለውን ጣዖት አምላክ ምስል ማለት ነው።፤ የአሼራ ዐፀዶቻቸውንም ቍረጡ። 14ስሙ ቀናተኛ የሆነው እግዚአብሔር (ያህዌ) ቀናተኛ አምላክ (ኤሎሂም) ነውና ሌላ አምላክ አታምልክ።

15“በምድሪቱ ከሚኖሩት ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም አምላኮቻቸውን ተከትለው ባመነዘሩና መሥዋዕትም ባቀረቡላቸው ጊዜ ይጋብዙሃል፤ አንተም መሥዋዕታቸውን ትበላለህ። 16ለወንዶች ልጆችህም ሴቶች ልጆቻቸውን ስታጭላቸውና እነዚህም ሴቶች ልጆች አምላኮቻቸውን በመከተል ሲያመነዝሩ፣ ወንዶች ልጆችህን ተመሳሳይ ድርጊት እንዲፈጽሙ ያነሣሷቸዋል።

17“ቀልጠው የሚሠሩ አማልክትን አታብጅ።

18“የቂጣን በዓል አክብር። እንዳዘዝሁህም ለሰባት ቀን እርሾ ያልገባበት ቂጣ ብላ፤ ይህንም በተወሰነው ጊዜ በአቢብ ወር አድርግ፤ በዚያ ወር ከግብፅ ወጥተሃልና።

19“የመንጋህ ወይም የበግና የፍየልህ፣ የቀንድ ከብትህ ተባዕት በኵር ሁሉ ሳይቀር፣ ከማሕፀን በኵር ሆኖ የሚወጣ ሁሉ የእኔ ነው። 20የአህያን በኵር በበግ ጠቦት ዋጀው፤ ካልዋጀኸው ግን ዐንገቱን ስበረው። በኵር ወንድ ልጆችህን ሁሉ ዋጅ።

“ማንም በፊቴ ባዶ እጁን አይቅረብ።

21“ስድስት ቀን ሥራ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ዕረፍ፤ በዕርሻና በመከር ወቅት እንኳ ቢሆን ማረፍ አለብህ።

22“የሰባቱን ሱባዔ በዓል ከስንዴው መከር በኵራቶች ጋር፣ እንዲሁም የመክተቻ በዓልን በዓመቱ መጨረሻ34፥22 በዚያ አካባቢ ክረምት መግቢያ ላይ ማለት ነው። ላይ አክብር። 23በዓመት ሦስት ጊዜ ወንድ ሁሉ በእስራኤል አምላክ (ኤሎሂም) በጌታ እግዚአብሔር (አዶናይ ያህዌ) ፊት ይቅረብ። 24አሕዛብን ከፊትህ አስወጣለሁ፤ ድንበርህን አሰፋለሁ፤ በዓመት ሦስት ጊዜ በአምላክህ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ለመቅረብ ስትወጣ፣ ምድርህን ማንም አይመኝም።

25“እርሾ ካለው ከማንኛውም ነገር ጋር የደም መሥዋዕት ለእኔ አታቅርብ፤ ከፋሲካ በዓል የተረፈው መሥዋዕት እስከ ማለዳ አይቈይ።

26“የዐፈርህን ምርጥ በኵራት ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ቤት አምጣ።

“ጠቦት ፍየልን በእናቱ ወተት አትቀቅል።”

27ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “እነዚህን ቃሎች ጻፋቸው፤ በእነዚህ ቃሎች መሠረት ከአንተና ከእስራኤል ጋር ቃል ኪዳን አድርጌአለሁና” አለው። 28ሙሴ እህል ሳይበላ፣ ውሃም ሳይጠጣ ከእግዚአብሔር (ያህዌ) ጋር አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በዚያ ነበር፤ በጽላቶቹ ላይ የቃል ኪዳኑን ቃሎች፣ ዐሥርቱ ትእዛዛትን ጻፈ።

የሚያበራው የሙሴ ፊት

29ሙሴ ሁለቱን የምስክር ጽላቶች በእጆቹ ይዞ ከሲና ተራራ በወረደ ጊዜ ከእግዚአብሔር (ያህዌ) ጋር ከመነጋገሩ የተነሣ ፊቱ እንደሚያበራ አላወቀም ነበር። 30አሮንና እስራኤላውያን ሁሉ ሙሴን ባዩት ጊዜ ፊቱ ያበራ ነበር፤ ወደ እርሱ ለመቅረብም ፈርተው ነበር። 31ሙሴ ግን ጠራቸው፤ ስለዚህ አሮንና የማኅበሩ መሪዎች ወደ እርሱ ተመለሱ፤ እርሱም አናገራቸው። 32ከዚያም በኋላ እስራኤላውያን ሁሉ ወደ እርሱ ቀረቡ፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) በሲና ተራራ የሰጠውን ትእዛዞች ሁሉ ሰጣቸው። 33ሙሴ ለእነርሱ ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ በፊቱ ላይ መሸፈኛ አደረገ። 34ከእርሱ ጋር ለመነጋገር ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሀልዎት በሚገባበት ጊዜ ሁሉ ግን፣ እስከሚወጣ ድረስ መሸፈኛውን ያነሣ ነበር፤ በወጣም ጊዜ የታዘዘውን ለእስራኤላውያን ነገራቸው። 35ፊቱ የሚያበራ መሆኑን አዩ፤ ከዚያም ሙሴ ከእግዚአብሔር (ያህዌ) ጋር ለመነጋገር ተመልሶ እስኪሄድ ድረስ መሸፈኛውን መልሶ በፊቱ ላይ ያደርግ ነበር።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

出埃及记 34:1-35

新的约版

1耶和华对摩西说:“你要凿出两块石版,跟你之前摔碎的两块一样,我要把前两块石版上的字刻在上面。 2你要预备好,明天清早你要上西奈山顶来见我。 3谁也不可与你同来,整座山上都不可有人,就是牛羊也不得在山前吃草。” 4于是,摩西凿出两块石版,跟先前的两块一样。他清早起来,照着耶和华的吩咐把石版带到西奈山上。 5耶和华在云中降临和摩西一同站在那里,宣告祂的名——耶和华。 6耶和华在摩西面前经过,并且宣告说:“我是耶和华,我是耶和华,是有怜悯和恩典的上帝,不轻易发怒,充满慈爱,无比信实, 7向千万人彰显慈爱,赦免罪恶和过犯,但决不免除罪责,必向子孙追讨父辈的罪债,直到三四代。” 8摩西急忙俯伏在地上敬拜, 9说:“主啊,如果我在你面前蒙了恩,求你与我们同行。虽然百姓顽固不化,求你赦免我们的过犯和罪恶,接纳我们做你的子民。”

10耶和华说:“我要与你立约,我要在你的同胞面前行奇事,是天下万国从未有过的奇事,你周围的外族人必看见我为你做的伟大而可畏的事。 11你要遵行我今天的吩咐。我必从你面前驱逐亚摩利人、迦南人、人、比利洗人、希未人和耶布斯人。 12你要谨慎,到了目的地后,不可与当地的居民立约,免得因此而陷入网罗。 13相反,要拆掉他们的祭坛,打碎他们的神柱,砍掉他们的亚舍拉神像。 14不可拜别的神明,因为耶和华是痛恨不贞的上帝,祂名为‘痛恨不贞’。

15“不可与当地的居民立约,免得他们与自己的神明苟合时邀请你,你就吃他们的祭物, 16给儿子娶他们的女儿为妻,以致她们与自己的神明苟合时诱使你的儿子犯同样的罪。

17“不可为自己铸造神像。

18“要守除酵节,照我的吩咐在亚笔月所定的时间吃七天的无酵饼,因为你是在亚笔月离开埃及的。

19“凡是头胎生的儿子都属于我,包括牲畜中一切头胎生的公牛和公羊。 20头胎生的驴要用羊赎回,如果不用羊赎回,就要打断它的脖子。凡头胎生的男婴,都要赎回他的性命。谁也不可空手来朝见我。

21“一周工作六天,第七天要休息,就是耕种和收割时也要休息。

22“在收割初熟麦子的时候,要守七七收割节,年底要守收藏节。 23所有的男子都要一年三次来朝见主耶和华——以色列的上帝。 24我要从你面前赶走外族人,扩张你的领土。你一年三次来朝见你的上帝耶和华时,必没有人贪恋你的土地。

25“不可把祭牲的血和有酵的饼一起献给我。逾越节的祭物也不可留到第二天早晨。

26“要把田中最好的初熟之物送到你们的上帝耶和华的殿中。

“不可用母山羊的奶煮它的小羊羔。”

27耶和华又对摩西说:“你要把我说的这些话记录下来,因为我要按这些话跟你和以色列人立约。” 28摩西在耶和华那里待了四十昼夜,没吃也没喝。耶和华把约的内容,就是十条诫命,写在石版上。

29摩西手里拿着两块约版下西奈山,他不知道自己因为曾与耶和华说话而脸上发光。 30亚伦和所有的以色列百姓看见摩西脸上发光,都不敢走近他。 31摩西召他们过来,亚伦和会众的首领便上前来。摩西与他们说话。 32之后,所有的以色列人都来到他面前,他就把耶和华在西奈山上的吩咐都告诉他们。 33说完之后,他就用帕子遮住自己的脸。 34每当进到会幕跟耶和华说话时,他就揭开帕子,出来后便把耶和华的吩咐告诉以色列百姓。 35百姓会看到他脸上发光,于是他再用帕子遮住脸,直到下次与耶和华说话的时候才揭开。