ዘፀአት 31 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

ዘፀአት 31:1-18

ባስልኤልና ኤልያብ

31፥2-6 ተጓ ምብ – ዘፀ 35፥30-35

1ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“እነሆ፤ ከይሁዳ ነገድ የሆር የልጅ ልጅ የሆነውን የኡሪን ልጅ ባስልኤልን መርጬዋለሁ። 3በሁሉም ዐይነት የእጅ ጥበብ ሥራ፣ ብልኀት፣ ችሎታና ዕውቀት እንዲኖረው የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም) መንፈስ ሞልቼዋለሁ። 4ይኸውም በወርቅ፣ በብርና በናስ ለሚሠሩት ሥራዎች በጥበብ የተሠሩ ጌጦችን እንዲያበጅ፣ 5ድንጋዮችን እንዲቈፍርና እንዲጠርብ ከዕንጨትም ጥርብ እንዲያወጣ፣ ሁሉንም ዐይነት የእጅ ጥበብ ሥራዎችን እንዲያከናውን ነው። 6በተጨማሪም ከዳን ነገድ የሆነውን የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን እንዲረዳው መርጬዋለሁ፤ እንዲሁም ያዘዝሁህን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ ለእጅ ጥበብ ዐዋቂዎች ሁሉ ብልኀትን ሰጥቻቸዋለሁ፤

7“ይኸውም የመገናኛውን ድንኳን፣

የምስክሩን ታቦት በላዩ ላይ ካለው ከስርየት መክደኛው ጋር፣

ሌሎች የድንኳኑን መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ፣

8ጠረጴዛውን ከነዕቃዎቹ፣

ከንጹሕ ወርቅ የተሠራውን የወርቅ መቅረዝ ከነዕቃዎቹ፣

የዕጣኑን መሠዊያ፣

9የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያውን ከነዕቃዎቹ፣

ሰኑን፣ ከነማስቀመጫው፣

10ከፈትል የተሠሩ ልብሶችን ይኸውም የካህኑን የአሮንን የተቀደሱ ልብሶችንና ካህናት ሆነው ሲያገለግሉ የሚለብሷቸውን የወንድ ልጆቹ ልብሶች፣

11እንዲሁም የመቅደሱ የሆነውን ቅብዐ ዘይትና ጣፋጭ ሽታ ያለውን ዕጣን እንዲሠሩ ነው።

“ልክ እኔ እንዳዘዝሁህ ያብጇቸው።”

ሰንበት

12ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ 13“ለእስራኤላውያን ንገራቸው፤ ‘ሰንበቴን ማክበር አለባችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል በሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ምልክት ይሆናል፤ ይኸውም የምቀድሳችሁ31፥13 ወይም፣ ቅዱስ አድርጌ የምለያችሁ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) እንደ ሆንሁ እንድታውቁ ነው።

14“ ‘ለእናንተ ቅዱስ ነውና ሰንበትን አክብሩ፤ ማንም ቢሽረው በሞት ይቀጣል፤ በዚያ ቀን ማንም የሚሠራ ቢኖር ከወገኑ ተነጥሎ ይለይ። 15ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ በሰንበት ቀን ማንም ቢሠራ በሞት መቀጣት አለበት። 16እስራኤላውያን በሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ሰንበትን በመጠበቅ የዘላለም ኪዳን አድርገው ማክበር አለባቸው፤ 17በእኔና በእስራኤላውያን መካከል ለዘላለም ምልክት ይሆናል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ሠርቶ፣ በሰባተኛው ቀን ከሥራ ታቅቦ ዐርፏልና።’ ”

18እግዚአብሔር (ያህዌ) በሲና ተራራ ላይ ለሙሴ መናገሩን ከፈጸመ በኋላ፣ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ጣት የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላቶች፣ ሁለቱን የምስክር ጽላቶች ለእርሱ ሰጠው።

Thai New Contemporary Bible

อพยพ 31:1-18

เบซาเลลและโอโฮลีอับ

(อพย.35:30-35)

1แล้วองค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับโมเสสว่า 2“เราได้เลือกสรรเบซาเลลบุตรชายของอูรีซึ่งเป็นบุตรชายของเฮอร์จากเผ่ายูดาห์ 3และเราให้เขาเปี่ยมด้วยพระวิญญาณของพระเจ้า มีความรู้ ความสามารถ และความชำนาญในเชิงช่างทุกแบบ 4เพื่อออกแบบเครื่องทอง เงิน และทองสัมฤทธิ์อย่างวิจิตร 5เจียระไนเพชรพลอย แกะสลักไม้ และงานฝีมือทุกแบบ 6ยิ่งกว่านั้นเราได้แต่งตั้งโอโฮลีอับบุตรชายของอาหิสะมัคจากเผ่าดานให้เป็นผู้ช่วยของเขา ทั้งเราได้ให้ความเชี่ยวชาญแก่ช่างฝีมือทุกคน เพื่อทำทุกสิ่งที่เราได้สั่งเจ้าไว้ 7ไม่ว่าจะเป็นเต็นท์นัดพบ หีบพันธสัญญาซึ่งมีพระที่นั่งกรุณาวางอยู่ และเครื่องใช้อื่นๆ ทั้งหมดในเต็นท์ 8โต๊ะพร้อมทั้งภาชนะใช้สอย คันประทีปทองคำบริสุทธิ์พร้อมอุปกรณ์ครบครัน แท่นเผาเครื่องหอม 9แท่นเผาเครื่องบูชาพร้อมภาชนะใช้สอย อ่างและฐานรองอ่าง 10รวมทั้งเครื่องแต่งกายบริสุทธิ์สำหรับอาโรนผู้เป็นปุโรหิต และเครื่องแต่งกายสำหรับบรรดาบุตรชายเมื่อปฏิบัติหน้าที่ปุโรหิต 11น้ำมันเจิมและเครื่องหอมสำหรับวิสุทธิสถานให้พวกเขาทำสิ่งเหล่านี้ตามที่เราได้สั่งเจ้าไว้”

วันสะบาโต

12แล้วองค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับโมเสสว่า 13“จงสั่งประชากรอิสราเอลว่า ‘พวกเจ้าจะต้องถือรักษาวันสะบาโตของเรา เพราะนี่จะเป็นหมายสำคัญระหว่างเรากับเจ้าสืบไปทุกชั่วอายุ เพื่อเจ้าจะรู้ว่าเราคือพระยาห์เวห์ผู้ทำให้เจ้าบริสุทธิ์31:13 หรือเป็นผู้ชำระเจ้าให้บริสุทธิ์หรือเป็นผู้แยกเจ้าไว้ให้บริสุทธิ์

14“ ‘ฉะนั้นจงถือรักษาวันสะบาโต เพราะเป็นวันบริสุทธิ์สำหรับเจ้า ผู้ใดลบหลู่จะต้องมีโทษถึงตาย ผู้ใดทำงานในวันนั้นจะต้องถูกตัดออกจากหมู่ประชากรของเขา 15จงทำงานในช่วงหกวัน ส่วนวันที่เจ็ดเป็นสะบาโตเพื่อการหยุดพัก เป็นวันบริสุทธิ์แด่องค์พระผู้เป็นเจ้าผู้ใดทำงานในวันสะบาโตต้องถูกประหาร 16ชนอิสราเอลจะถือวันสะบาโตและเฉลิมฉลองวันนั้นสืบไปทุกชั่วอายุ เป็นพันธสัญญานิรันดร์ 17นี่เป็นหมายสำคัญตลอดไประหว่างเรากับประชากรอิสราเอล เพราะในหกวันองค์พระผู้เป็นเจ้าได้ทรงสร้างฟ้าสวรรค์และแผ่นดินโลก ในวันที่เจ็ดทรงหยุดทำงานและพักผ่อน’ ”

18เมื่อองค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสกับโมเสสบนภูเขาซีนายจบแล้ว พระองค์ประทานศิลาสองแผ่นซึ่งจารึกพระบัญญัติสิบประการโดยนิ้วพระหัตถ์ของพระเจ้าเองแก่โมเสส