ዘፀአት 27 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዘፀአት 27:1-21

የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረቢያ መሠዊያ

27፥1-8 ተጓ ምብ – ዘፀ 38፥1-7

1“ከፍታው ሦስት ክንድ27፥1 ወደ 1.3 ሜትር ያህል ነው። የሆነ መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሥራ፤ ርዝመቱ አምስት፣ ስፋቱም አምስት ክንድ ሆኖ ባለ አራት ማእዘን27፥1 ርዝመቱ ወርዱ 2.3 ሜትር ያህል ነው። ይሁን። 2ቀንዶቹና መሠዊያው አንድ ወጥ ይሆኑ ዘንድ በአራቱም ማእዘኖች ላይ ቀንድ አድርግለት፤ መሠዊያውንም በነሐስ ለብጠው። 3ዕቃዎቹን ሁሉ ይኸውም የዐመድ ማስወገጃ ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፣ ሜንጦዎችንና የፍም መያዣዎችን ከነሐስ አብጃቸው። 4ዐመድ ማውረጃ የሚሆን እንደ መረብ የሆነ የነሐስ ፍርግርግ አድርግለት በአራቱም የመረብ ማእዘኖች ላይ የነሐስ ቀለበቶች አብጅ። 5እስከ መሠዊያው ወገብ እንዲደርስ በመሠዊያው ዙሪያ ባለው እርከን ሥር አድርገው። 6የግራር ዕንጨት መሎጊያዎችን ለመሠዊያው ሠርተህ በነሐስ ለብጣቸው። 7በሸክም ጊዜ በመሠዊያው ሁለቱም ጐኖች እንዲሆኑ፣ መሎጊያዎቹ በቀለበቶቹ ውስጥ ይግቡ። 8መሠዊያውን ውስጡን ባዶ ከሆኑ ሳንቃዎች አብጀው፤ ልክ በተራራው ላይ ባየኸው መሠረት ይበጅ።

የመገናኛው ድንኳን አደባባይ

27፥9-19 ተጓ ምብ – ዘፀ 38፥9-20

9“ለመገናኛው ድንኳን አደባባይ አብጅለት፤ በደቡብ በኩል ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ27፥9 በዚህና በቍጥር 11 ላይ ወደ 46 ሜትር ያህል ነው። ይሁን፤ ከቀጭን በፍታ የተፈተሉ መጋረጃዎች፣ 10ሃያ ምሰሶዎች፣ ሃያ የነሐስ መቆሚያዎች፣ የብር ኵላቦችና በምሰሶዎቹም ላይ ዘንጎች ይኑሩት። 11በሰሜኑም በኩል አንድ መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ይሁኑ፤ ሃያ ምሰሶዎቹ፣ ሃያ የነሐስ መቆሚያዎች፣ የብር ኵላቦችና በምሰሶዎችም ላይ ዘንጎች ይኑሩ።

12“የአደባባዩ ምዕራብ ጫፍ ስፋቱ አምሳ ክንድ27፥12 በዚህና በቍጥር 13 ላይ ወደ 23 ሜትር ያህል ነው። ሆኖ ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር መቆሚያዎች ያሉት መጋረጃዎች ይኑሩት። 13በምሥራቅ ጫፍ በፀሓይ መውጫ በኩል ያለው አደባባይ አሁንም አምስት ክንድ ስፋት ይኑረው። 14ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው ርዝመታቸው ዐሥራ አምስት ክንድ27፥14 በዚህና በቍጥር 15 ላይ ወደ 6.9 ሜትር ያህል ነው። የሆነ መጋረጃዎች በአንድ በኩል ባለው ደጃፍ ይሁኑ። 15ሦስት ምሰሶዎች ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው ርዝመታቸው ዐሥራ አምስት ክንድ የሆነ መጋረጃዎች በሌላው በኩል ይሁኑ።

16“ለአደባባዩ መግቢያ አራት ምሰሶዎችና አራት መቆሚያዎች ያሉት ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከቀጭን በፍታ የተፈተለ፣ ጥልፍ ጠላፊ የጠለፈበት ሃያ ክንድ ርዝመት27፥16 ወደ 9 ሜትር ያህል ነው። ያለው መጋረጃ ይሁን። 17በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎች፣ ኵላቦችና የነሐስ መቆሚያዎች ይኑሯቸው። 18አደባባዩ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ፣ ስፋቱ አምሳ ክንድ27፥18 ርዝመቱ 46 ሜትር፣ ወርዱ 23 ሜትር ያህል ነው። ሆኖ፣ በቀጭኑ ከተፈተለ ማግ ቁመታቸው አምስት ክንድ27፥18 ወደ 2.3 ሜትር ያህል ነው። የሆነ መጋረጃዎችና የነሐስም መቆሚያዎች ያሉት ይሁን። 19ጥቅማቸው ምንም ዐይነት ይሁን፣ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በሙሉ የድንኳኑና የአደባባዩ ካስማዎችም ሁሉ ሳይቀሩ ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ።

የመቅረዙ ዘይት

27፥20-21 ተጓ ምብ – ዘሌ 24፥1-3

20“መብራቶቹ ባለማቋረጥ እንዲበሩ ለመብራቱ የሚሆን ተወቅጦ የተጠለለ ንጹሕ ዘይት እንዲያመጡልህ እስራኤላውያንን እዘዛቸው። 21በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው በስተውጭ ይኸውም ከምስክሩ ታቦት ፊት ለፊት፣ አሮንና ወንድ ልጆቹ መብራቶቹን ከምሽት እስከ ንጋት በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት እንዲበሩ ያድርጉ፤ ይህም በእስራኤላውያን ዘንድ ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ሥርዐት ይሆናል።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

出埃及記 27:1-21

造燔祭壇的條例

1「要用皂莢木造一個四方形的祭壇,長寬各二點三米,高一點三米。 2要在壇的四角造四個角狀物,與壇連成一體,壇外面要包上銅。 3用銅造盛壇灰的盆和其他祭壇用具,即鏟、碗、肉叉、火鼎。 4要造一個銅網,在銅網的四角裝置四個銅環。 5銅網在祭壇圍邊的下方,向下伸展到祭壇的腰部。 6要用皂莢木為祭壇造兩根橫杠,外面包上銅。 7要將兩根橫杠穿在祭壇兩旁的銅環裡,以便抬祭壇。 8整座壇都用木板製成,壇是中空的。一切都要照我在山上給你的指示去做。

聖幕院子的規劃

9「要為聖幕圍出一個院子。院子的南面要用細麻線做帷幔,長四十六米, 10帷幔有二十根柱子,二十個帶凹槽的銅底座,柱子上的鉤子和橫杆都是銀的。 11北面的帷幔也是長四十六米,柱子、銅底座、鉤子、橫杆的樣式都與南面的一樣。 12院子西面的帷幔寬二十三米,有十根柱子和十個帶凹槽的底座。 13院子東面的帷幔也是寬二十三米。 14-15入口兩邊的帷幔都是寬六點九米,各有三根柱子和三個帶凹槽的底座。 16院子的入口要有門簾,長九米,用細麻線和藍色、紫色、朱紅色的線織成,上面有精緻的刺繡,還有四根柱子和四個帶凹槽的底座。 17所有繞著院子的柱子都要用銀製的橫杆連接,所有的鉤子都要用銀製作,帶凹槽的底座要用銅製作。 18整個院子長四十四米,寬二十二米,高二點三米,所有的帷幔都要用細麻線精工製作,帶凹槽的底座要用銅製作。 19聖幕裡其他一切器具以及聖幕、院子所用的橛子都要用銅製作。

20「你要吩咐以色列百姓,把榨出的純橄欖油拿來做會幕內的燈油,使燈臺上的燈經常亮著。 21亞倫和他的子孫要負責照看聖所內約櫃前的幔子外的燈,使燈在耶和華面前日夜亮著。這是以色列百姓世世代代當守的條例。