ዘፀአት 24 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዘፀአት 24:1-18

ቃል ኪዳኑ ስለ መጽናቱ

1ከዚያም ሙሴን “አንተና አሮን፣ ናዳብና አብድዩ ከሰባዎቹ የእስራኤል አለቆች ጋር ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ኑ፤ ከሩቅም ስገዱ አለው፤ 2ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሊቀርብ የሚችለው ሙሴ ብቻ ነው። ሌሎቹ መቅረብ የለባቸውም፤ ሕዝቡም ከእርሱ ጋር መምጣት የለበትም።”

3ሙሴ ወደ ሕዝቡ ሄዶ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ቃሎችና ሕጎች ሁሉ በነገራቸው ጊዜ በአንድ ድምፅ ሆነው፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ያለውን ሁሉ እናደርጋለን” አሉ። 4ከዚያም ሙሴ እግዚአብሔር (ያህዌ) ያለውን ሁሉ ጻፈ። በማግስቱም ማልዶ ተነሥቶ፣ በተራራው ግርጌ መሠዊያን ሠራ፤ ዐሥራ ሁለቱን የእስራኤልን ነገዶች የሚወክሉ ዐሥራ ሁለት የድንጋይ ዐምዶችን አቆመ። 5ከዚያም ወጣት ወንድ እስራኤላውያንን ላከ፤ እነርሱም የሚቃጠል መሥዋዕት24፥5 በትውፊት፣ የሰላም መሥዋዕት በመባል ይታወቃል። አቀረቡ፤ ወይፈኖችን የኅብረት መሥዋዕት አድርገው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ሠዉ። 6ሙሴ የደሙን እኩሌታ ወስዶ በጐድጓዳ ሳሕኖች አኖረው፤ የቀረውንም እኩሌታ በመሠዊያው ላይ ረጨው። 7ከዚያም የኪዳኑን መጽሐፍ ወስዶ ለሕዝቡ አነበበላቸው፤ እነርሱም፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ያለውን ሁሉ እናደርጋለን፤ እንታዘዛለን” አሉ።

8ከዚያም ሙሴ ደሙን ወሰደ፤ ሕዝቡም ላይ ረጭቶ፣ “ይህ እነዚህን ቃሎች በሰጠ ጊዜ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ከእናንተ ጋር የገባው የቃል ኪዳኑ ደም ነው” አላቸው።

9ሙሴና አሮን፣ ናዳብና አብድዩ እንደዚሁም ሰባዎቹ የእስራኤል አለቆች ወደ ተራራው ወጡ፣ 10የእስራኤልንም አምላክ (ኤሎሂም) አዩ፤ ከእግሩም በታች እንደ ብሩህ ሰማይ የጠራ የሰንፔር24፥10 ወይም፣ ላፒስ ላዘሊ ተብሎ መተርጐም ይችላል። ወለል ነበር። 11ሆኖም እግዚአብሔር (ኤሎሂም) በእስራኤል ሕዝብ አለቆች ላይ እጁን አላነሣባቸውም። እግዚአብሔርን (ኤሎሂም) አዩ፣ በሉ፤ ጠጡም።

12እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “በተራራው ላይ ወደ እኔ ና፤ በዚህም ቈይ፤ እኔም መመሪያ እንዲሆናቸው ሕግና ትእዛዞች የጻፍኩባቸውን የድንጋይ ጽላቶች እሰጥሃለሁ” አለው።

13ከዚያም ሙሴ ከረዳቱ ከኢያሱ ጋር አብሮ ሄደ፤ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ተራራ ወጣ። 14እርሱም ሽማግሌዎችን “ወደ እናንተ እስክንመለስ ድረስ በዚህ ቈዩ፤ አሮንና ሖር ከእናንተ ጋር ናቸው፤ ክርክር ያለው ሰው ቢኖር ወደ እነርሱ ይሂድ።” አላቸው።

15ሙሴ ወደ ተራራ ሲወጣ ደመናው ተራራውን ሸፈነ፤ 16የእግዚአብሔርም (ያህዌ) ክብር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፤ ደመናውም ተራራውን እስከ ስድስት ቀን ድረስ ሸፈነው፤ በሰባተኛውም ቀን እግዚአብሔር (ያህዌ) በደመናው ውስጥ ሆኖ ሙሴን ጠራው። 17ለእስራኤላውያን የእግዚአብሔር (ያህዌ) ክብር በተራራው ጫፍ ላይ እንደሚባላ እሳት ሆኖ ይታይ ነበር። 18ከዚያም ሙሴ ወደ ተራራው ሲወጣ ደመናው ውስጥ ገባ፤ በተራራውም ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቈየ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

出埃及記 24:1-18

在西奈山立約

1耶和華又指示摩西說:「你和亞倫拿答亞比戶以色列的七十位長老上我這裡來,遠遠地敬拜我。 2只有你可以靠近我,其他人,包括全體百姓,都不得走近。」

3摩西下山把耶和華的話和法令都告訴百姓,百姓齊聲回答:「我們願意遵行耶和華的一切吩咐。」 4摩西把耶和華的這些話記錄下來。第二天清晨,摩西在山腳築了一座壇,立了十二根柱子代表以色列的十二支派。 5他又吩咐以色列的青年去給耶和華獻燔祭,又獻上公牛作平安祭。 6摩西把祭牲的血一半放在盆裡,一半灑在壇上。 7他又把約書念給百姓聽,百姓聽了都說:「我們願意遵行耶和華的一切吩咐,我們願意順服。」 8摩西便把盆中的血灑在百姓身上,說:「這是立約的血,是耶和華按所說的話與你們立約的憑據。」

9之後,摩西亞倫拿答亞比戶及七十位長老便上了山。 10他們都看見了以色列的上帝,祂的腳下好像是一片藍寶石,像天一樣明淨。 11上帝沒有伸手殺這些以色列的首領,允許他們看見祂,在祂面前吃喝。

12耶和華對摩西說:「你上山到我這裡來,留在這裡,我要把寫著律法和誡命的石版賜給你,你可以用來教導百姓。」 13於是,摩西帶著他的助手約書亞動身上了上帝的山。 14離開之前,摩西吩咐長老說:「你們在這裡等候我們回來。亞倫戶珥跟你們在一起,百姓當中有什麼訴訟的事情,可以交給他們處理。」

15摩西上了山,密雲遮蓋著整座山。 16耶和華的榮耀停留在西奈山上,密雲遮蓋了山六天。第七天,耶和華在雲中召喚摩西17以色列人眼中,耶和華的榮耀在山上好像烈火。 18摩西上到山上,走進雲中,在那裡停留了四十晝夜。