ዘፀአት 2 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዘፀአት 2:1-25

የሙሴ መወለድ

1በዚያን ጊዜ ከሌዊ ነገድ የሆነ አንድ ሰው አንዲት ሌዋዊት ሴት አገባ። 2እርሷም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ሕፃኑ መልከ መልካም መሆኑን ባየች ጊዜ ሦስት ወር ሸሸገችው። 3ከዚያ በላይ ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ ግን የደንገል ቅርጫት ወስዳ፣ በዝፍትና በቅጥራን ለቀለቀችው፤ ሕፃኑንም በውስጡ አስተኝታ ቅርጫቱን አባይ ወንዝ ዳር ቄጠማ መካከል አስቀመጠችው። 4የሕፃኑም እኅት የሚደርስበትን ነገር ለማወቅ ራቅ ብላ ቆማ ታይ ነበር።

5በዚህ ጊዜ የፈርዖን ልጅ ልትታጠብ ወደ አባይ ወንዝ ወረደች፤ በምትታጠብበትም ጊዜ ደንገጥሮቿ በወንዙ ዳር ወዲያና ወዲህ ይሉ ነበር፤ በቄጠማውም መካከል የተቀመጠ ቅርጫት አይታ ከደንገጥሮቿ አንዷን እንድታመጣው ላከቻት። 6ቅርጫቱን ስትከፍተው ሕፃኑን በውስጡ አየች፤ ያለቅስ ስለ ነበርም ዐዘነችለትና፣ “ከዕብራውያን ሕፃናት አንዱ መሆን አለበት” አለች።

7የሕፃኑ እኅት ለፈርዖን ልጅ፣ “ሕፃኑን እያጠባች የምታሳድግልሽ ከዕብራውያን ሴቶች መካከል ሞግዚት ላምጣልሽን?” አለቻት።

8የፈርዖንም ልጅ፣ “መልካም፣ ሂጂ” አለቻት። ልጂቱም ሄዳ የሕፃኑን እናት ይዛ መጣች። 9የፈርዖንም ልጅ ሴቲቱን፣ “ይህን ሕፃን ወስደሽ እያጠባሽ አሳድጊልኝ፤ ደመወዝ እከፍልሻለሁ” አለቻት። ሴትዮዋም ሕፃኑን ወስዳ አሳደገችው። 10ሕፃኑም ባደገ ጊዜ ወደ ፈርዖን ልጅ አመጣችው፤ ልጇም ሆነ፤ እርሷም፣ “ከውሃ አውጥቼዋለሁና” ስትል ስሙን ሙሴ2፥10 በዕብራይስጥ ሙሴ የሚለው የቃል ድምፅ፣ ማውጣት ከሚለው ቃል ጋር ተመሳሳይ ድምፅ አለው። ብላ ጠራችው።

ሙሴ ወደ ምድያም ምድር ሸሸ

11ሙሴ ካደገ በኋላ አንድ ቀን ወገኖቹ ወደሚገኙበት ስፍራ ወጣ፤ በዚያም ተገድደው ከባድ ሥራ ሲሠሩ ተመለከተ፤ ዕብራዊ ወገኑንም አንድ ግብፃዊ ሲደበድበው አየ። 12ሙሴም አካባቢውን ቃኝቶ ማንም አለመኖሩን ካረጋገጠ በኋላ፣ ግብፃዊውን ገድሎ አሸዋ ውስጥ ደበቀው። 13በማግስቱም በወጣ ጊዜ ሁለት ዕብራውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አየ፤ ጥፋተኛውንም፣ “የገዛ ወገንህን የምትመታው ለምንድን ነው?” አለው።

14ሰውየውም፣ “አንተን በእኛ ላይ ገዥና ዳኛ ማን አደረገህ? ግብፃዊውን እንደ ገደልኸው እኔንም ልትገድለኝ ትፈልጋለህን?” አለው። ሙሴም፣ “ለካስ ያደረግሁት ነገር ታውቋል!” በማለት ፈራ።

15ፈርዖንም ይህን በሰማ ጊዜ፣ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ፤ ሙሴ ግን ከፈርዖን ሸሽቶ ወደ ምድያም ሄደ፤ እዚያም እንደ ደረሰ በአንድ የውሃ ጕድጓድ አጠገብ ተቀመጠ። 16የምድያም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ወደ ውሃው ጕድጓድ መጥተው የአባታቸውን በጎች ውሃ ለማጠጣት ገንዳውን ሞሉት። 17እረኞችም መጥተው ሴቶቹን ሲያባርሯቸው ሙሴ ከተቀመጠበት ተነሥቶ ተከላከለላቸው፤ በጎቻቸውንም አጠጣላቸው።

18ሴቶቹም ወደ አባታቸው ወደ ራጉኤል በተመለሱ ጊዜ፣ “ዛሬስ ያለወትሯችሁ እንዴት ፈጥናችሁ ተመለሳችሁ?” አላቸው።

19እነርሱም፣ “አንድ ግብፃዊ ከእረኞች እጅ አዳነን፤ እንዲያውም ውሃ ቀድቶ በጎቻችንን አጠጣልን” አሉት።

20አባታቸውም፣ “ሴቶች ልጆቹን የት አለ? ለምን ትታችሁት መጣችሁ? ጥሩትና አብሮን እንጀራ ይብላ” አላቸው።

21ሙሴም ከሰውየው ጋር ለመኖር ተስማማ፤ ራጉኤልም ልጁን ሲፓራን ዳረለት። 22ሲፓራም ወንድ ልጅ ወለደች፤ ሙሴም፣ “በባዕድ አገር መጻተኛ ነኝ” ሲል የልጁን ስም ጌርሳም2፥22 በዕብራይስጥ ጌርሳም የሚለው ቃል ድምፅ፣ መጻተኛ በዚያ አለ ከሚለው ሐረግ ጋር ተመሳሳይ ድምፅ አለው። ብሎ ጠራው።

23ከብዙ ዓመት በኋላ የግብፅ ንጉሥ ሞተ፤ እስራኤላውያንም በባርነት ከደረሰባቸው ግፍ የተነሣ ይጮኹ ነበር፤ ከባርነት ቀንበር ለመላቀቅ ያሰሙትም ጩኸት ወደ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ደረሰ። 24እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) የጩኸታቸውን ሲቃ ሰማ፤ ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር የገባውንም ቃል ኪዳን ዐሰበ። 25እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) እስራኤላውያንን ተመለከተ፤ ስለ እነርሱም ገደደው።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

出埃及記 2:1-25

摩西出生

1有一個利未族人跟他同族的女子結婚。 2那女子懷孕,生了一個男嬰。她看見孩子可愛,就把他藏了三個月。 3後來無法再藏下去,她就拿來一個蒲草籃子,外面塗上防水的瀝青和柏油,然後把嬰兒放在裡面,又把籃子放在尼羅河邊的蘆葦叢中。 4嬰兒的姐姐遠遠地站著,要看看她的弟弟究竟會怎樣。

5這時,法老的女兒來到河邊沐浴,宮女們在河邊行走。公主發現了蘆葦叢中的籃子,便吩咐一個婢女去把它取來。 6公主打開一看,原來是一個男嬰。公主看見孩子在哭,就可憐他,說:「他是希伯來人的孩子。」 7嬰兒的姐姐對公主說:「我去找一個希伯來婦女當奶媽,為你哺養他好嗎?」 8公主回答說:「好!」那女孩就跑去把嬰孩的母親帶來。 9公主對那婦女說:「你把孩子抱去,替我哺養他,我會給你工錢。」她便把孩子抱去哺養。 10孩子漸漸長大,她便把他帶到公主那裡,孩子就做了公主的兒子。公主給孩子取名叫摩西,意思是「我把他從水中拉了上來」。

11後來,摩西長大了,他去看望做苦工的希伯來同胞,看見一個埃及人在毆打他的一個希伯來同胞。 12他左右觀望,見四下無人,便下手殺了那埃及人,把屍體埋藏在沙地裡。 13第二天,他又出去,看見兩個希伯來人在打架,便過去對理虧的人說:「你為什麼打自己的同胞呢?」 14那人說:「你以為你是誰啊?誰立你做我們的首領和審判官?難道你要殺我,像殺那個埃及人一樣嗎?」摩西聽了,害怕起來,心想:「我做的事一定被人知道了。」 15法老聽說這件事後,便想殺死摩西摩西為了躲避法老,就逃到米甸居住。一天他坐在一口井旁, 16米甸祭司的七個女兒來打水,要把水倒進槽裡飲她們父親的羊。 17這時,來了另外一群牧人要把她們趕走。摩西便起來幫助她們,打水飲她們的羊群。 18她們回到父親流珥2·18 流珥」又名「葉忒羅」。那裡,父親問她們:「你們今天怎麼這麼快就回來了?」 19她們答道:「有一個埃及人救我們免遭牧人的欺負,還幫我們打水飲羊群。」 20他又問女兒們:「現在那人在哪裡?你們怎麼可以丟下他不管呢?去請他來吃點東西。」 21後來,摩西同意住在那人家裡。那人把女兒西坡拉許配給他。 22後來,西坡拉生了一個兒子,摩西給他取名叫革舜,意思是「我成了在異鄉寄居的人」。

23過了多年,埃及王死了。以色列人受盡奴役,就哀歎呼求,聲音傳到上帝那裡。 24上帝聽見他們的哀聲,顧念從前跟亞伯拉罕以撒雅各所立的約, 25就垂顧他們,體恤他們。