ዘፀአት 19 – NASV & KJV

New Amharic Standard Version

ዘፀአት 19:1-25

በሲና ተራራ ላይ

1በሦስተኛው ወር እስራኤላውያን ከግብፅ ለቀው በወጡበት በዚያችው ዕለት ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ። 2ከራፊዲም ከተነሡ በኋላ ወደ ሲና ምድረ በዳ ገቡ፤ እስራኤልም በዚያ በምድረ በዳው በተራራው ፊት ለፊት ሰፈሩ።

3ከዚያም ሙሴ ወደ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ወጣ፤ እግዚአብሔርም (ያህዌ) ከተራራው ጠራውና እንዲህ አለው፤ “ለያዕቆብ ቤት የምትለው ለእስራኤልም ሕዝብ የምትናገረው ይህ ነው፤ 4‘በግብፅ ላይ ያደረግሁትን፣ በንስርም ክንፍ ተሸክሜ ወደ ራሴ እንዴት እንዳመጣኋችሁ እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል። 5አሁንም በፍጹም ብትታዘዙኝና ቃል ኪዳኔን ብትጠብቁ እነሆ ከአሕዛብ ሁሉ እናንተ የተወደደ ርስቴ ትሆናላችሁ፤ ምንም እንኳ ምድር ሁሉ የእኔ ብትሆንም፣ 6እናንተ19፥6 ወይም ምድር ሁሉ የእኔ ርስት ናት፤ እናንተ ለእኔ የመንግሥት ካህናት የተቀደሰ ሕዝብ ትሆናላችሁ፤’ ለእስራኤላውያን የምትነግራቸው ቃሎች እነዚህ ናቸው።”

7ስለዚህ ሙሴ ተመልሶ የሕዝቡን አለቆች አስጠራ፤ እንዲናገር እግዚአብሔር (ያህዌ) ያዘዘውን ቃሎች ሁሉ ነገራቸው። 8ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ላይ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ያለውን ሁሉ እናደርጋለን” ብለው መለሱ፤ ስለዚህ ሙሴ እነርሱ ያሉትን መልሶ ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ወሰደ።

9እግዚአብሔርም (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ከአንተ ጋር ስናገር ሕዝቡ እንዲሰሙኝና እምነታቸውን ምንጊዜም በአንተ ላይ እንዲጥሉ በከባድ ደመና ወደ አንተ እመጣለሁ” ከዚያም ሙሴ ሕዝቡ ያሉትን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ነገረው።

10እግዚአብሔርም (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ወደ ሕዝቡ ሂድና ዛሬና ነገ ቀድሳቸው፤ ልብሳቸውን እንዲያጥቡ አድርግ፤ 11በሦስተኛውም ቀን ይዘጋጁ፤ ምክንያቱም በዚያ ቀን በሕዝቡ ፊት እግዚአብሔር (ያህዌ) በሲና ተራራ ላይ ይወርዳል። 12በተራራው ዙሪያ ለሕዝቡ ወሰን አበጅተህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ወደ ተራራው እንዳትወጡ ወይም ግርጌውን እንዳትነኩ ተጠንቀቁ፤ ማንም ተራራውን ቢነካ በርግጥ ይሞታል። 13በድንጋይ ይወገራል ወይም በቀስት ይወጋል፤ ምንም እጅ በእርሱ ላይ አያርፍም፤ ሰውም ሆነ እንስሳ በሕይወት እንዲኖር አይተውም።’ ወደ ተራራው መውጣት የሚችሉት ከፍ ባለ ድምፅ መለከት በተነፋ ጊዜ ብቻ ነው።”

14ሙሴ ከተራራው ወርዶ ወደ ሕዝቡ ከሄደ በኋላ ቀደሳቸው፤ ልብሳቸውንም ዐጠቡ። 15ከዚያም ለሕዝቡ፣ “ለሦስተኛው ቀን ራሳችሁን አዘጋጁ፤ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከማድረግ ተቈጠቡ” አላቸው።

16በሦስተኛውም ቀን ጧት ከባድ ደመና በተራራው ላይ ሆኖ ነጐድጓድና መብረቅ እንዲሁም ታላቅ የቀንደ መለከት ድምፅ ነበር፤ በሰፈሩ ያሉት ሁሉ ተንቀጠቀጡ። 17ከዚያም ሙሴ ከእግዚአብሔር (ያህዌ) ጋር ለማገናኘት ሕዝቡን ከሰፈር ይዞ ወጣ፤ ከተራራውም ግርጌ ቆሙ። 18የሲና ተራራ እግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት ስለወረደበት በጢስ ተሸፍኖ ነበር። ጢሱ ከምድጃ እንደሚወጣ ጢስ ወደ ላይ ተትጐለጐለ፤ ተራራውም በሙሉ19፥18 ብዙ የዕብራይስጥ ቅጆችና የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም፣ ሕዝቡ ሁሉ ይላሉ። በኀይል ተናወጠ። 19የመለከቱም ድምፅ እያየለ መጣ። ከዚያም ሙሴ ተናገረ፤ እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) በድምፅ መለሰለት።19፥19 ወይም፣ እግዚአብሔርም በነጐድጓድ መለሰለት

20እግዚአብሔር (ያህዌ) በሲና ተራራ ጫፍ ላይ ወረደ፤ ሙሴን ወደ ተራራው ጫፍ ጠራው፤ ሙሴም ወጣ። 21እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲህ አለው፤ “ሕዝቡ እግዚአብሔርን (ያህዌ) ለማየት በመጣደፍ ብዙዎቹ እንዳይጠፉ ውረድና አስጠንቅቃቸው 22ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) የሚቀርቡት ካህናት እንኳ ራሳቸውን መቀደስ አለባቸው፤ አለዚያ እግዚአብሔር (ያህዌ) ቍጣውን ያወርድባቸዋል።”

23ሙሴ እግዚአብሔርን (ያህዌ) እንዲህ አለው፤ “ሕዝቡ ወደ ሲና ተራራ ሊወጡ አይችሉም፤ ምክንያቱም አንተ ራስህ ‘በተራራው ዙሪያ ወሰን አድርግ፤ የተቀደሰም በማድረግ ለየው’ በማለት አስጠንቅቀኸናልና።”

24እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲህ አለ፤ “ውረድና አሮንን ከአንተ ጋር ይዘኸው ውጣ፤ ካህናቱና ሕዝቡ ግን ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ለመምጣት መጣደፍ የለባቸውም፤ አለዚያ እርሱ ቍጣውን ያወርድባቸዋል።”

25ስለዚህ ሙሴ ወደ ሕዝቡ ወርዶ ነገራቸው።

King James Version

Exodus 19:1-25

1In the third month, when the children of Israel were gone forth out of the land of Egypt, the same day came they into the wilderness of Sinai. 2For they were departed from Rephidim, and were come to the desert of Sinai, and had pitched in the wilderness; and there Israel camped before the mount. 3And Moses went up unto God, and the LORD called unto him out of the mountain, saying, Thus shalt thou say to the house of Jacob, and tell the children of Israel; 4Ye have seen what I did unto the Egyptians, and how I bare you on eagles’ wings, and brought you unto myself. 5Now therefore, if ye will obey my voice indeed, and keep my covenant, then ye shall be a peculiar treasure unto me above all people: for all the earth is mine: 6And ye shall be unto me a kingdom of priests, and an holy nation. These are the words which thou shalt speak unto the children of Israel.

7¶ And Moses came and called for the elders of the people, and laid before their faces all these words which the LORD commanded him. 8And all the people answered together, and said, All that the LORD hath spoken we will do. And Moses returned the words of the people unto the LORD.

9And the LORD said unto Moses, Lo, I come unto thee in a thick cloud, that the people may hear when I speak with thee, and believe thee for ever. And Moses told the words of the people unto the LORD.

10¶ And the LORD said unto Moses, Go unto the people, and sanctify them to day and to morrow, and let them wash their clothes, 11And be ready against the third day: for the third day the LORD will come down in the sight of all the people upon mount Sinai. 12And thou shalt set bounds unto the people round about, saying, Take heed to yourselves, that ye go not up into the mount, or touch the border of it: whosoever toucheth the mount shall be surely put to death: 13There shall not an hand touch it, but he shall surely be stoned, or shot through; whether it be beast or man, it shall not live: when the trumpet soundeth long, they shall come up to the mount.19.13 trumpet: or, cornet

14¶ And Moses went down from the mount unto the people, and sanctified the people; and they washed their clothes. 15And he said unto the people, Be ready against the third day: come not at your wives.

16¶ And it came to pass on the third day in the morning, that there were thunders and lightnings, and a thick cloud upon the mount, and the voice of the trumpet exceeding loud; so that all the people that was in the camp trembled. 17And Moses brought forth the people out of the camp to meet with God; and they stood at the nether part of the mount. 18And mount Sinai was altogether on a smoke, because the LORD descended upon it in fire: and the smoke thereof ascended as the smoke of a furnace, and the whole mount quaked greatly. 19And when the voice of the trumpet sounded long, and waxed louder and louder, Moses spake, and God answered him by a voice. 20And the LORD came down upon mount Sinai, on the top of the mount: and the LORD called Moses up to the top of the mount; and Moses went up. 21And the LORD said unto Moses, Go down, charge the people, lest they break through unto the LORD to gaze, and many of them perish.19.21 charge: Heb. contest 22And let the priests also, which come near to the LORD, sanctify themselves, lest the LORD break forth upon them. 23And Moses said unto the LORD, The people cannot come up to mount Sinai: for thou chargedst us, saying, Set bounds about the mount, and sanctify it. 24And the LORD said unto him, Away, get thee down, and thou shalt come up, thou, and Aaron with thee: but let not the priests and the people break through to come up unto the LORD, lest he break forth upon them. 25So Moses went down unto the people, and spake unto them.