ዘዳግም 27 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ዘዳግም 27:1-26

በጌባል ተራራ ላይ የቆመ መሠዊያ

1ሙሴና የእስራኤል አለቆች ሕዝቡን እንዲህ ብለው አዘዙ፤ “ዛሬ የማዝዛችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቁ፤ 2አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ወደሚሰጥህ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፣ ጥቂት ትልልቅ ድንጋዮችን አቁምና በኖራ ቅባቸው። 3የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሰጠህ ተስፋ መሠረት፣ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ወደሚሰጥህ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን ስትሻገር፣ የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ ጻፍባቸው። 4ዮርዳኖስን እንደ ተሻገርህም፣ ዛሬ ባዘዝሁህ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በጌባል ተራራ ላይ ትከላቸው፤ በኖራም ቅባቸው። 5እዚያም ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የድንጋይ መሠዊያ ሥራ፤ በድንጋዮቹም ላይ ማናቸውንም የብረት መሣሪያ አታሳርፍባቸው። 6የአምላክህን የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) መሠዊያ ካልተጠረበ ድንጋይ ሥራ፤ በላዩም ለአምላክህ ለእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርብበት። 7በዚያም የኅብረት መሥዋዕት27፥7 በትውፊት የሰላም መሥዋዕት በመባል ይታወቃል ሠዋ፤ ብላም፤ በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት ደስ ይበልህ። 8በድንጋዮቹ ላይ የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ ግልጽ አድርገህ ጻፍባቸው።”

በጌባል ተራራ ላይ የተነገረ መርገም

9ሙሴና ሌዋውያን ካህናትም ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ አሉ፤ “እስራኤል ሆይ፤ ጸጥ ብለህ አድምጥ! አንተ ዛሬ የአምላክህ የእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ሕዝብ ሆነሃል፤ 10አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ታዘዝ፤ ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዙንና ሥርዐቱን ጠብቅ።”

11ሙሴ በዚያኑ ዕለት ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዘ፦

12ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዮሴፍና ብንያም ሕዝቡን ለመባረክ በገሪዛን ተራራ ላይ ይቁሙ። 13ሮቤል፣ ጋድ፣ አሴር፣ ዛብሎን፣ ዳንና ንፍታሌምም በጌባል ተራራ ላይ ለመርገም ይቁሙ።

14ሌዋውያን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብለው ይናገሩ፦

15“የእጅ ጥበብ ባለሙያ የሠራውን፣ በእግዘአብሔር (ያህዌ) ዘንድ አስጸያፊ የሆነውን ምስል የሚቀርጽ ወይም ጣዖትን የሚያበጅ፣ በስውርም የሚያቆም ሰው የተረገመ ይሁን።”

ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

16“አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል የተረገመ ይሁን።”

ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን! ይበል።

17“የባልንጀራውን የድንበር ድንጋይ ከቦታው የሚያንቀሳቅስ የተረገመ ይሁን።”

ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

18“ዐይነ ስውሩን በተሳሳተ መንገድ የሚመራ፣ የተረገመ ይሁን።”

ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

19“በመጻተኛው፣ አባት በሌለውና በመበለቲቱ ላይ ፍትሕ የሚያዛባ የተረገመ ይሁን።”

ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

20“ከአባቱ ሚስት ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን፤ የአባቱን መኝታ ያረክሳልና።”

ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

21“ከማናቸውም እንስሳ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚያደርግ የተረገመ ይሁን።”

ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

22“የአባቱ ወይም የእናቱ ልጅ ከሆነችው እኅቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን።”

ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

23“ከዐማቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን።”

ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

24“በድብቅ ባልንጀራውን የሚገድል የተረገመ ይሁን።”

ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

25“ንጹሕን ሰው ለመግደል ጕቦ የሚቀበል የተረገመ ይሁን።”

ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

26“የዚህን ሕግ ቃሎች በመፈጸም የማይጸና የተረገመ ይሁን።”

ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

申命記 27:1-26

以巴路山上的律法

1摩西以色列眾長老吩咐民眾說:「你們要遵守我今天吩咐你們的一切誡命。 2你們渡過約旦河、進入你們的上帝耶和華應許給你們的土地那天,要豎立幾塊大石,塗上石灰。 3你們渡過約旦河、進入你們祖先的上帝耶和華應許要賜給你們的奶蜜之鄉後,要把這律法一字不漏地寫在大石上。 4你們渡過約旦河後,要照我今日的吩咐在以巴路山上豎立這些石頭,塗上石灰。 5要在那裡為你們的上帝耶和華築一座石壇,不要用鐵器鑿刻石頭。 6要用未鑿過的石頭為你們的上帝耶和華築一座壇,在上面獻燔祭給祂; 7又要獻上平安祭,在祂面前吃喝快樂。 8你們要把這律法一字不漏、清清楚楚地寫在那幾塊大石上。」

9摩西利未祭司對全體以色列人說:「以色列人啊,要肅靜聆聽!你們今天已成為你們上帝耶和華的子民。 10你們要聽從祂,遵守祂今天藉我吩咐你們的誡命和律例。」

違命必受咒詛

11那天,摩西吩咐民眾說: 12「你們渡過約旦河後,西緬利未猶大以薩迦約瑟便雅憫支派要站在基利心山上為民眾祝福; 13呂便迦得亞設西布倫拿弗他利支派要站在以巴路山上宣告咒詛。 14利未人要對所有以色列人高聲說,

15『凡雕刻或鑄造耶和華所憎惡的神像,並偷偷供奉的必受咒詛!』

全體民眾要回答說,『阿們!』

16『凡不尊敬父母的必受咒詛!』

全體民眾要回答說,『阿們!』

17『凡挪移鄰居界石的必受咒詛!』

全體民眾要回答說,『阿們!』

18『凡故意帶領盲人走錯路的必受咒詛!』

全體民眾要回答說,『阿們!』

19『不公正地對待寄居者和孤兒寡婦的必受咒詛!』

全體民眾要回答說,『阿們!』

20『凡與父親的妻妾亂倫,使父親蒙羞的必受咒詛!』

全體民眾要回答說,『阿們!』

21『凡與獸交合的必受咒詛!』

全體民眾要回答說,『阿們!』

22『凡與同父或同母姊妹亂倫的必受咒詛!』

全體民眾要回答說,『阿們!』

23『凡與岳母亂倫的必受咒詛!』

全體民眾要回答說,『阿們!』

24『凡暗殺鄰居的必受咒詛!』

全體民眾要回答說,『阿們!』

25『凡因收受賄賂而殺害無辜的必受咒詛!』

全體民眾要回答說,『阿們!』

26『凡不遵行這律法的必受咒詛!』

全體民眾要回答說,『阿們!』