ዘካርያስ 14 – NASV & NIV

New Amharic Standard Version

ዘካርያስ 14:1-21

እግዚአብሔር ይመጣል፤ ይነግሣልም

1እነሆ፤ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል፤ ብዝበዛሽንም በውስጥሽ ይካፈላሉ።

2ኢየሩሳሌምን እንዲወጉ አሕዛብን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ከተማዪቱ ትያዛለች፤ ቤቶች ይበዘበዛሉ፤ ሴቶችም ይደፈራሉ፤ የከተማዪቱ እኩሌታ ይማረካል፤ የሚቀረው ሕዝብ ግን ከከተማዪቱ አይወሰድም።

3እግዚአብሔርም በጦርነት ጊዜ እንደሚዋጋ፣ እነዚያን አሕዛብ ሊወጋ ይወጣል። 4በዚያን ቀን እግሮቹ ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ይቆማሉ፤ የደብረ ዘይት ተራራም ታላቅ ሸለቆን በመሥራት የተራራውን እኩሌታ ወደ ሰሜን፣ እኩሌታውንም ወደ ደቡብ በማድረግ ምሥራቅና ምዕራብ ሆኖ ለሁለት ይከፈላል፤ 5እናንተም በእግዚአብሔር ተራራ ሸለቆ በኩል በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን በምድር ትሸሻላችሁ፤ ሸለቆው እስከ አጸል ይደርሳልና። በምድር መናወጥ14፥5 ወይም ተራራዬ ሸለቆ ይሮጣል፤ እስከ አጸል ይስፋፋል። በርዕደ መሬት ሳቢያ እንደ ተዘጋው ሁሉ ለወደፊቱም እንደዚያ ይሆናል ምክንያት ሸሽታችሁ እንደ ነበረ ትሸሻላችሁ፤ ከዚያም አምላኬ እግዚአብሔር ይመጣል፤ ቅዱሳኑም ሁሉ አብረውት ይመጣሉ።

6በዚያ ቀን በረዶ ውርጭና ብርሃን አይኖርም። 7ቀኑም የብርሃን ወይም የጨለማ ጊዜ የሌለበት ልዩ ቀን ይሆናል፤ ያም ቀን በእግዚአብሔር የታወቀ ቀን ይሆናል፤ ሲመሽም ብርሃን ይሆናል።

8በዚያን ቀን የሕይወት ውሃ ከኢየሩሳሌም ይፈልቃል፤ እኩሌታው ወደ ምሥራቁ ባሕር14፥8 ሙት ባሕር ነው።፣ እኩሌታውም ወደ ምዕራቡ ባሕር14፥8 ሜድትራኒያን ነው። ይፈስሳል፤ ይህም በበጋና በክረምት ይሆናል።

9እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያን ቀን እግዚአብሔር አንድ፣ ስሙም አንድ ብቻ ይሆናል።

10ምድር ሁሉ ከጌባ አንሥቶ በኢየሩሳሌም ደቡብ እስካለችው ሬሞን ድረስ ተለውጣ ደልዳላ ሜዳ ትሆናለች፤ ኢየሩሳሌም ግን ከብንያም በር እስከ መጀመሪያው በር፣ ከማእዘን በርና ከሐናንኤል ግንብ እስከ ንጉሡ የወይን ጠጅ መጥመቂያ ድረስ በዚያው በቦታዋ ላይ ከፍ እንዳለች ትኖራለች። 11የሰው መኖሪያም ትሆናለች፤ ከቶም ዳግመኛ አትፈርስም፤ ኢየሩሳሌም ያለ ሥጋት በሰላም ትኖራለች። 12እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን የወጓትን አሕዛብ ሁሉ የሚመታበት መቅሠፍት ይህ ነው፤ ገና በእግራቸው ቆመው ሳሉ ሥጋቸው ይበሰብሳል፤ ዐይኖቻቸው በጕድጓዶቻቸው ውስጥ እንዳሉ ይበሰብሳሉ፤ ምላሶቻቸውም በአፎቻቸው ውስጥ እንዳሉ ይበሰብሳሉ። 13በዚያ ቀን ከእግዚአብሔር ዘንድ በሰዎች ላይ ታላቅ ሽብር ይወርዳል፤ እያንዳንዱ ሰው የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፤ አንዱም ሌላውን ይወጋዋል። 14ይሁዳም ደግሞ ኢየሩሳሌምን ይወጋል። በዙሪያው ያሉ የአሕዛብ ሁሉ ሀብት፣ ብዙ ወርቅ፣ ብርና ልብስ ይሰበሰባል። 15ይህንኑ የሚመስል መቅሠፍት ፈረሶችን፣ በቅሎዎችን ግመሎችንና አህዮችን እንዲሁም በየሰፈሩ ያሉትን እንስሶች ሁሉ ይመታል።

16ከዚያም ኢየሩሳሌምን ከወጓት አሕዛብ ከሞት የተረፉት ሁሉ ለንጉሡ፣ ለእግዚአብሔር ጸባኦት ለመስገድና የዳስን በዓል ለማክበር በየዓመቱ ይወጣሉ። 17የምድር ሕዝብ ሁሉ ለንጉሡ፣ ለእግዚአብሔር ጸባኦት ሊሰግዱ ወደ ኢየሩሳሌም የማይወጡ ከሆነ ዝናብ አያገኙም። 18የግብፅም ሰዎች ወደዚያ ሳይወጡ ቢቀሩ፣ ዝናብ አያገኙም፤ እግዚአብሔር ወጥተው የዳስ በዓልን በማያከብሩ አሕዛብ ላይ የሚያደርሰውን መቅሠፍት በእነርሱም ላይ ያመጣል። 19የዳስን በዓል ወጥተው ለማያከብሩ ግብፃውያንና አሕዛብ ሁሉ የተወሰነው ቅጣት ይህ ነው።

20በዚያ ቀን በፈረሶች ሻኵራ ላይ፣ “ቅዱስ ለእግዚአብሔር” የሚል ጽሑፍ ይቀረጻል፤ በእግዚአብሔር ቤት ያሉ የማብሰያ ምንቸቶች ከመሠዊያው ፊት ለፊት እንዳሉ ሳሕኖች የተቀደሱ ይሆናሉ። 21በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶች ሁሉ ለእግዚአብሔር ጸባኦት የተቀደሱ ይሆናሉ፤ መሥዋዕት ለማቅረብ የሚመጡ ሁሉ ምንቸቶቹን በመውሰድ ያበስሉባቸዋል፤ በዚያን ቀን በእግዚአብሔር ጸባኦት ቤት ከእንግዲህ ወዲያ ከነዓናዊ14፥21 ወይም ነጋዴ እነዚህ ሕዝቦች በአብዛኛው በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሳይሆኑ አይቀሩም። አይገኝም።

New International Version

Zechariah 14:1-21

The Lord Comes and Reigns

1A day of the Lord is coming, Jerusalem, when your possessions will be plundered and divided up within your very walls.

2I will gather all the nations to Jerusalem to fight against it; the city will be captured, the houses ransacked, and the women raped. Half of the city will go into exile, but the rest of the people will not be taken from the city. 3Then the Lord will go out and fight against those nations, as he fights on a day of battle. 4On that day his feet will stand on the Mount of Olives, east of Jerusalem, and the Mount of Olives will be split in two from east to west, forming a great valley, with half of the mountain moving north and half moving south. 5You will flee by my mountain valley, for it will extend to Azel. You will flee as you fled from the earthquake14:5 Or 5 My mountain valley will be blocked and will extend to Azel. It will be blocked as it was blocked because of the earthquake in the days of Uzziah king of Judah. Then the Lord my God will come, and all the holy ones with him.

6On that day there will be neither sunlight nor cold, frosty darkness. 7It will be a unique day—a day known only to the Lord—with no distinction between day and night. When evening comes, there will be light.

8On that day living water will flow out from Jerusalem, half of it east to the Dead Sea and half of it west to the Mediterranean Sea, in summer and in winter.

9The Lord will be king over the whole earth. On that day there will be one Lord, and his name the only name.

10The whole land, from Geba to Rimmon, south of Jerusalem, will become like the Arabah. But Jerusalem will be raised up high from the Benjamin Gate to the site of the First Gate, to the Corner Gate, and from the Tower of Hananel to the royal winepresses, and will remain in its place. 11It will be inhabited; never again will it be destroyed. Jerusalem will be secure.

12This is the plague with which the Lord will strike all the nations that fought against Jerusalem: Their flesh will rot while they are still standing on their feet, their eyes will rot in their sockets, and their tongues will rot in their mouths. 13On that day people will be stricken by the Lord with great panic. They will seize each other by the hand and attack one another. 14Judah too will fight at Jerusalem. The wealth of all the surrounding nations will be collected—great quantities of gold and silver and clothing. 15A similar plague will strike the horses and mules, the camels and donkeys, and all the animals in those camps.

16Then the survivors from all the nations that have attacked Jerusalem will go up year after year to worship the King, the Lord Almighty, and to celebrate the Festival of Tabernacles. 17If any of the peoples of the earth do not go up to Jerusalem to worship the King, the Lord Almighty, they will have no rain. 18If the Egyptian people do not go up and take part, they will have no rain. The Lord14:18 Or part, then the Lord will bring on them the plague he inflicts on the nations that do not go up to celebrate the Festival of Tabernacles. 19This will be the punishment of Egypt and the punishment of all the nations that do not go up to celebrate the Festival of Tabernacles.

20On that day Holy to the Lord will be inscribed on the bells of the horses, and the cooking pots in the Lord’s house will be like the sacred bowls in front of the altar. 21Every pot in Jerusalem and Judah will be holy to the Lord Almighty, and all who come to sacrifice will take some of the pots and cook in them. And on that day there will no longer be a Canaanite14:21 Or merchant in the house of the Lord Almighty.