ዘኍል 36 – NASV & BPH

New Amharic Standard Version

ዘኍል 36:1-13

የሰለጰዓድ ሴት ልጆች ርስት

36፥1-12 ተጓ ምብ – ዘኍ 27፥1-11

1ከዮሴፍ ዝርያ ጐሣዎች የሆኑ የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ጐሣ የቤተ ሰብ አለቆች ወደ ሙሴና የእስራኤላውያን ቤተ ሰቦች አለቆች ወደ ሆኑት መሪዎች ቀርበው ተናገሩ፤ 2እንዲህም አሉ፤ “ምድሪቱን በዕጣ ከፋፍለህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርገህ እንድትሰጣቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) አንተን ጌታዬን ባዘዘ ጊዜ የወንድማችንን የሰለጰዓድን ድርሻ ለሴቶች ልጆቹ እንድትሰጥ አዝዞሃል። 3ከሌሎች የእስራኤል ነገዶች ባል ቢያገቡ ድርሻቸው ከእኛ የዘር ርስት ላይ ተወስዶ የሚያገቧቸው ሰዎች ላሉበት ነገድ ይተላለፋል፤ ይህ ከሆነ ደግሞ በዕጣ ከተደለደለልን ርስት ላይ ከፊሉ ሊቀነስብን ነው። 4የእስራኤላውያን ዓመተ ኢዮቤልዩ በሚመጣበት ጊዜ የእነርሱ ድርሻ ወደ ባሎቻቸው ነገድ ይጨመራል፤ ይህ ከሆነም ድርሻቸው ከአባቶቻችን ነገድ ርስት ላይ ይወሰዳል።”

5ከዚህ በኋላ ሙሴ እግዚአብሔር (ያህዌ) በተናገረው መሠረት እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “የዮሴፍ ነገድ የተናገረው ትክክል ነው፤ 6እንግዲህ የሰለጰዓድን ሴት ልጆች በተመለከተ እግዚአብሔር (ያህዌ) የሚያዝዘው ይህ ነው፤ ከአባታቸው ነገድ ወገን እስከ ሆነ ድረስ የወደዱትን ማግባት ይችላሉ። 7እያንዳንዱ እስራኤላዊም ከቀደሙት አባቶቹ በወረሰው ርስት ይጽና፤ በእስራኤል ከአንዱ ነገድ ወደ ሌላው ነገድ የሚተላለፍ ርስት አይኖርም። 8እያንዳንዱ እስራኤላዊ የየአባቶቹን ርስት መውረስ ስላለበት፣ በማንኛውም የእስራኤል ነገድ ውስጥ ርስት የምትወርስ የትኛዪቱም ሴት፣ ከአባቷ ነገድ ወገን የሆነውን አንዱን ማግባት አለባት። 9እያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ የወረሰውን መሬት እንዳለ ማቈየት ስላለበት፣ ርስት ከአንዱ ነገድ ወደ ሌላው ነገድ አይተላለፍም።”

10ስለዚህም የሰለጰዓድ ሴት ልጆች እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። 11የሰለጰዓድ ሴት ልጆች፤ ማህለህ፣ ቲርጻ፣ ዔግላ፣ ሚልካ፣ ኑዓ ከአባታቸው ወንድሞች ልጆች ጋር ተጋቡ። 12ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ዝርያ ጐሣዎች ጋር በመጋባታቸው፣ ርስታቸው በዚያው በአባታቸው ጐሣና ነገድ እጅ እንዳለ ቀረ።

13ከኢያሪኮ36፥13 በዕብራይስጥ የኢያሪኮ ዮርዳኖስ የሚል ሲሆን፣ ይህም የዮርዳኖስ ወንዝ የጥንት ስም ሳይሆን አይቀርም። ማዶ፣ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ፣ በሞዓብ ሜዳ ሳሉ እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ አማካይነት ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ትእዛዞችና ደንቦች እነዚህ ናቸው።

Bibelen på hverdagsdansk

4. Mosebog 36:1-13

Lov angående kvinders arveret

1Familieoverhovederne i Gileads slægt kom nu til Moses og folkets ledere med et problem. De sagde: 2„Herren har befalet dig at lade Israels folk fordele landet ved lodtrækning, og du har givet os besked på at overdrage vores slægtning Zelofhads jord til hans døtre. 3Men hvis de nu gifter sig med mænd fra en anden stamme, vil deres jordstykke tilfalde den stamme, og vores område vil i så fald blive formindsket, 4uden at vi kan gøre os håb om at få den mistede jord tilbage i det førstkommende jubelår.”

5Derfor bekendtgjorde Moses på Herrens befaling følgende ordning for kvinders arvelod: „Disse mænd fra Manasses stamme har ret. 6Derfor siger Herren, at Zelofhads døtre kun må gifte sig inden for deres egen stamme. 7Derved undgår vi, at deres jordstykke kommer på andre stammers hænder, hvilket ville være forkert, for der må ikke overdrages jord fra en stamme til en anden. 8-9Enhver arveberettiget kvinde skal derfor gifte sig inden for sin egen stamme, så hendes arvelod forbliver på stammens hænder.”

10-12Zelofhads døtre, som hed Mala, Tirtza, Hogla, Milka og Noa, gjorde, som Herren havde befalet Moses. De giftede sig med mænd fra deres egen stamme, Manasses stamme. På den måde forblev deres jord på stammens hænder.

13Alle disse bud og forskrifter gav Herren til Israels folk gennem Moses, mens de lå i lejr på Moabs sletter ved Jordanfloden over for Jeriko.