ዘኍል 2 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ዘኍል 2:1-34

የየነገዱ አሰፋፈር

1እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ 2“እስራኤላውያን ከምስክሩ ድንኳን ትይዩ ዙሪያውን ጥቂት ራቅ ብለው እያንዳንዱ ሰው በየዐርማውና በየቤተ ሰቡ ምልክት ሥር ይስፈር።”

3በምሥራቅ በኩል በፀሓይ መውጫ፤

የይሁዳ ምድብ፤ በየሰራዊቱና በዐርማቸው ሥር ይስፈር፤ የይሁዳ ሕዝብ አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነው፤ 4የሰራዊቱም ብዛት ሰባ አራት ሺሕ ስድስት መቶ ነው።

5ከእነዚህ ቀጥሎ የይሳኮር ነገድ ይሰፍራል፤ የይሳኮር ሕዝብ አለቃ የሶገር ልጅ ናትናኤል ሲሆን፣ 6የሰራዊቱም ብዛት አምሳ አራት ሺሕ አራት መቶ ነው።

7ከዚያም የዛብሎን ነገድ ይቀጥላል፤ የዛብሎን ሕዝብ አለቃ የኬሎን ልጅ ኤልያብ ሲሆን፣ 8የሰራዊቱም ብዛት አምሳ ሰባት ሺሕ አራት መቶ ነው።

9በየሰራዊታቸው ሆነው ከአይሁድ ምድብ የተመዘገቡ አንድ መቶ ሰማንያ ስድስት ሺሕ አራት መቶ ናቸው፤ እነዚህ አስቀድመው ይወጣሉ።

10በደቡብ በኩል፤

የሮቤል ምድብ ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ይሆናል፤ የሮቤል ሕዝብ አለቃ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር ሲሆን፣ 11የሰራዊቱም ብዛት አርባ ስድስት ሺሕ አምስት መቶ ነው።

12ከእነዚህ ቀጥሎ የስምዖን ነገድ ይሰፍራል፤ የስምዖን ሕዝብ አለቃ የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል ሲሆን፣ 13የሰራዊቱም ብዛት አምሳ ዘጠኝ ሺሕ ሦስት መቶ ነው።

14ከዚያም የጋድ ነገድ ይቀጥላል፤ የጋድ ሕዝብ አለቃ የራጉኤል2፥14 ብዙ የማሶሬቲክ፣ የኦሪት ሳምራውያንና የቩልጌት ቅጆች ጸዑኤል ይላሉ (ዘኍ 1፥14 ይመ)፤ አያሌ የማሶሬቲክ ቅጆች ግን ከዚህ ይስማማሉ። ልጅ ኤሊሳፍ ሲሆን፣ 15የሰራዊቱም ብዛት አርባ አምስት ሺሕ ስድስት መቶ አምሳ ነው።

16በየሰራዊታቸው ሆነው ከሮቤል ምድብ የተመዘገቡት ወንዶች በሙሉ አንድ መቶ አምሳ አንድ ሺሕ አራት መቶ አምሳ ናቸው፤ እነዚህ ቀጥለው ይመጣሉ።

17ከዚህ በኋላ የመገናኛው ድንኳንና የሌዋውያን ምድብ በመካከል ሆነው ይጓዛሉ፤ እያንዳንዳቸውም አሰፋፈራቸውን በመከተል ቦታቸውን ጠብቀው በዐርማቸው ሥር ይጓዛሉ።

18በምዕራብ በኩል፤

የኤፍሬም ምድብ ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ይሆናል፤ የኤፍሬም ሕዝብ አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ሲሆን፣ 19የሰራዊቱም ብዛት አርባ ሺሕ አምስት መቶ ነው።

20ከእነዚህም የምናሴ ነገድ ይቀጥላል፣ የምናሴ ሕዝብ አለቃ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል ሲሆን፣ 21የሰራዊቱም ብዛት ሠላሳ ሁለት ሺሕ ሁለት መቶ ነው።

22ከዚያም የብንያም ነገድ ይቀጥላል፣ የብንያም ሕዝብ አለቃ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ሲሆን፣ 23የሰራዊቱም ብዛት ሠላሳ አምስት ሺሕ አራት መቶ ነው።

24በየሰራዊታቸው ሆነው ከኤፍሬም ምድብ የተመዘገቡት ወንዶች በሙሉ አንድ መቶ ስምንት ሺሕ አንድ መቶ ናቸው፤ እነዚህ ሦስተኛ ሆነው ይመጣሉ።

25በሰሜን በኩል፤

የዳን ምድብ ሰራዊት በዐርማው ሥር ይሆናል፤ የዳን ሕዝብ አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ሲሆን፣ 26የሰራዊቱም ብዛት ስድሳ ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ነው።

27የአሴር ነገድ ከእነዚህ ቀጥሎ ይሰፍራል፤ የአሴር ሕዝብ አለቃ የኤክራን ልጅ ፋግኤል ሲሆን፣ 28የሰራዊቱም ብዛት አርባ አንድ ሺሕ አምስት መቶ ነው።

29ከዚያም የንፍታሌም ነገድ ይቀጥላል፤ የንፍታሌም ሕዝብ አለቃ የዔናን ልጅ አኪሬ ሲሆን፣ 30የሰራዊቱም ብዛት አምሳ ሦስት ሺሕ አራት መቶ ነው።

31በየሰራዊታቸው ሆነው ከዳን ምድብ የተመዘገቡት ወንዶች ሁሉ አንድ መቶ አምሳ ሰባት ሺሕ ስድስት መቶ ናቸው፤ እነርሱም በዐርማቸው ሥር በመጨረሻ ይመጣሉ።

32በየቤተ ሰባቸው፣ በየምድባቸውና በየሰራዊታቸው የተመዘገቡት እስራኤላውያን ስድስት መቶ ሦስት ሺሕ አምስት መቶ አምሳ ናቸው፤ 33ያም ሆኖ ግን እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሌዋውያኑ ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋር አልተቈጠሩም።

34ስለዚህ እስራኤላውያን እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ በየዐርማውም ሥር የሰፈሩትና፣ እያንዳንዳቸው በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የተጓዙት በዚህ ሁኔታ ነበር።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

民数记 2:1-34

营地的安排

1耶和华对摩西亚伦说: 2以色列人要各归本旗,按本族的旗号,在会幕四围稍远的地方安营。” 3东边,即日出的方向,是犹大营区及其旗号。犹大人的首领是亚米拿达的儿子拿顺4率领七万四千六百人。 5犹大支派旁边安营的是以萨迦支派,首领是苏押的儿子拿坦业6率领五万四千四百人。 7然后是西布伦支派,首领是希伦的儿子以利押8率领五万七千四百人。 9犹大营区的人共十八万六千四百人,他们是开路先锋。

10南边是吕便营区及其旗号。吕便人的首领是示丢珥的儿子以利苏11率领四万六千五百人。 12吕便支派旁边安营的是西缅支派,首领是苏利沙代的儿子示路蔑13率领五万九千三百人。 14然后是迦得支派,首领是丢珥的儿子以利雅萨15率领四万五千六百五十人。 16吕便营区共十五万一千四百五十人,他们是第二队。 17随后是会幕和利未人的营区,在其他各营中间。他们各就各位,各归本旗,照安营时的次序出发。

18西边是以法莲营区及其旗号。以法莲人的首领是亚米忽的儿子以利沙玛19率领四万零五百人。 20以法莲支派旁边是玛拿西支派,首领是比大苏的儿子迦玛列21率领三万二千二百人。 22然后是便雅悯支派,首领是基多尼的儿子亚比但23率领三万五千四百人。 24以法莲营区共十万八千一百人,他们是第三队。

25北边是营区及其旗号。人的首领是亚米沙代的儿子亚希以谢26率领六万二千七百人。 27支派旁边安营的是亚设支派,首领是俄兰的儿子帕结28率领四万一千五百人。 29然后是拿弗他利支派,首领是以南的儿子亚希拉30率领五万三千四百人。 31营区共有十五万七千六百人,他们是后队。

32以上照宗族和队伍统计的以色列人共六十万三千五百五十名。 33照耶和华对摩西的吩咐,利未人没被统计在其中。

34于是,以色列人照耶和华对摩西的吩咐,各按自己的旗号安营,各按自己的宗族启行。