ኤፌሶን 6 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ኤፌሶን 6:1-24

ወላጆችና ልጆች

1ልጆች ሆይ፤ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ፤ ይህ ተገቢ ነውና። 2“አባትህንና እናትህን አክብር” በሚለው ቀዳሚ ትእዛዝ ውስጥ ያለው ተስፋ፣ 3“መልካም እንዲሆንልህ፣ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም” የሚል ነው።

4አባቶች ሆይ፤ እናንተም ልጆቻችሁን አታስቈጧቸው፤ ነገር ግን በጌታ ምክርና ተግሣጽ አሳድጓቸው።

ጌቶችና ባሪያዎች

5ባሪያዎች ሆይ፤ ለክርስቶስ እንደምትታዘዙ፣ በምድር ጌቶቻችሁ ለሆኑት በአክብሮትና በፍርሀት፣ በልብ ቅንነትም ታዘዙ፤ 6ለታይታና ከእነርሱ ሙገሳን ለማግኘት ሳይሆን፣ እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከልብ በመፈጸም ታዘዟቸው። 7ሰውን ሳይሆን ጌታን እንደምታገለግሉ ሆናችሁ በሙሉ ልብ አገልግሉ፤ 8ምክንያቱም ባሪያም ሆነ ነጻ ሰው ለሚያደርገው በጎ ነገር ሁሉ ሽልማቱን ከጌታ እንደሚቀበል ታውቃላችሁ።

9እናንተም ጌቶች ሆይ፤ ለባሮቻችሁ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የእነርሱም፣ የእናንተም ጌታ የሆነው በሰማይ እንዳለ፣ የሰውንም ፊት አይቶ እንደማያደላ ታውቃላችሁና አታስፈራሯቸው።

የእግዚአብሔር ጦር ዕቃ

10በተረፈ በጌታና ብርቱ በሆነው ኀይሉ ጠንክሩ። 11የዲያብሎስን የተንኰል ሥራ መቋቋም ትችሉ ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ ልበሱ። 12ምክንያቱም ተጋድሏችን ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች፣ ከሥልጣናትና ከኀይላት እንዲሁም በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ከርኩሳን መናፍስት ሰራዊት ጋር ነው። 13ክፉው ቀን ሲመጣ መቋቋም ትችሉ ዘንድ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ ልበሱ፤ ሁሉን ከፈጸማችሁ በኋላ ጸንታችሁ መቆም ትችላላችሁና። 14እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ዝናር ታጥቃችሁ፣ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፣ 15በሰላም ወንጌል ዝግጁነት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ። 16ከእነዚህም ሁሉ ጋር፣ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ 17የመዳንን ራስ ቍር አድርጉ፤ የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው። 18በሁሉ ዐይነት ጸሎትና ልመና፣ በማንኛውም ሁኔታ በመንፈስ ጸልዩ፤ ይህንም በማሰብ ንቁ፤ ስለ ቅዱሳንም ሁሉ በትጋት ልመና አቅርቡ።

19የወንጌልን ምስጢር ለመግለጥ አፌን በምከፍትበት ጊዜ ሁሉ በድፍረት እንድናገር ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ጸልዩልኝ። 20በሰንሰለት የታሰረ መልእክተኛ የሆንሁት ለዚሁ ነውና። ስለዚህ መናገር የሚገባኝን ያለ ፍርሀት እንድናገር ጸልዩልኝ።

የመጨረሻ ሰላምታ

21በምን ሁኔታ እንዳለሁና ምን እንደማደርግ ታውቁ ዘንድ ተወዳጅ ወንድምና በጌታ ታማኝ አገልጋይ የሆነው ቲኪቆስ ሁሉንም ነገር ይነግራችኋል። 22የእኛን ሁኔታ እንድታውቁና ልባችሁን እንዲያበረታ ለዚሁ ስል ወደ እናንተ ልኬዋለሁ።

23ከእግዚአብሔር አብ፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም፣ ፍቅርም ከእምነት ጋር ለወንድሞች ይሁን።

24ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ለሚወድዱ ሁሉ ጸጋ ይሁን።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

以弗所书 6:1-24

父慈子孝

1你们为人子女的,要按主的旨意听从父母,这是理所当然的。 2因为第一条带着应许的诫命就是:“要孝敬父母, 3使你在世上蒙祝福、享长寿。” 4你们为人父母的不要激怒儿女,要照主的教导和警戒养育他们。

主仆之间

5你们做奴仆的,要战战兢兢、诚诚实实、怀着敬畏的心服从你们肉身的主人,就像服从基督一样。 6不要只做一些讨好人的表面工夫,要像基督的奴仆一样从心里遵行上帝的旨意。 7要甘心乐意地工作,像是在事奉主,不是在服侍人。 8要知道:不管是奴仆还是自由人,每个人所做的善事都会得到主的奖赏。 9你们做主人的也一样,要善待奴仆,不可威吓他们。要知道你们主仆同有一位在天上的主人,祂不偏待人。

上帝所赐的军装

10最后,你们要靠着主和祂的大能大力做刚强的人, 11要穿戴上帝所赐的全副军装,以便能够抵挡魔鬼的阴谋。 12因为我们争战的对象不是这世上的血肉之躯,而是在这黑暗世界执政的、掌权的、管辖的和天上属灵的邪恶势力。 13因此,你们要用上帝所赐的全副军装装备自己,好在邪恶的时代抵挡仇敌,到争战结束后依旧昂首挺立。 14务要站稳,用真理当作带子束腰,以公义当作护心镜遮胸, 15把和平的福音当作鞋子穿在脚上准备行动。 16此外,还要拿起信心的盾牌,好灭尽恶者一切的火箭。 17要戴上救恩的头盔,紧握圣灵的宝剑——上帝的话。 18要靠着圣灵随时多方祷告和祈求,警醒不怠地为众圣徒祷告。 19也请你们为我祷告,求上帝赐我口才,让我勇敢地把福音的奥秘讲解明白。 20我为传福音成了披枷带锁的使者。请你们为我祷告,使我能尽忠职守,放胆传福音。

问候

21至于我的近况,推基古会详细告诉各位。他是主内亲爱的弟兄和忠心的仆人。 22我特地派他去你们那里,好让你们知道我们的近况,并且叫他去安慰和鼓励你们。

23愿父上帝和主耶稣基督赐给各位弟兄姊妹平安、爱心和信心! 24愿所有忠贞地爱我们主耶稣基督的人都蒙恩典!