ኤርምያስ 8 – NASV & NAV

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 8:1-22

1“ ‘በዚያን ጊዜ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ የይሁዳ ነገሥታትና መኳንንት ዐፅም፣ የካህናትና የነቢያት ዐፅም፣ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዐፅም ከየመቃብራቸው ይወጣል። 2በወደዷቸውና በአገለገሏቸው እንዲሁም በተከተሏቸው፣ ባማከሯቸውና ባመለኳቸው በፀሓይ፣ በጨረቃና በሰማያት ከዋክብት ሁሉ ፊት ይሰጣል፤ አይሰበሰብም ወይም አይቀበርም፤ ነገር ግን እንደ ተጣለ ጕድፍ በምድር ላይ ይበተናል። 3ከዚህ ክፉ ሕዝብ የተረፉት ሁሉ፣ ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ፤ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።’

ኀጢአትና ያስከተለው ቅጣት

4“እንዲህ በላቸው፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ ‘ሰዎች ቢውድቁ፣ እንደ ገና ከወደቁበት አይነሡምን?

ሰው ተሳስቶ ወደ ኋላ ቢሄድ፣ ከስሕተቱ አይመለስምን?

5ታዲያ፣ ይህ ሕዝብ ለምን ፊቱን አዙሮ ወደ ኋላ ይሄዳል?

ለምንስ ኢየሩሳሌም ዘወትር ወደ ኋላ ትመለሳለች?

ተንኰልን የሙጥኝ ብለው ይዘዋል፤

ሊመለሱም ፈቃደኛ አይደሉም።

6እኔ በጥንቃቄ አደመጥኋቸው፤

ትክክለኛ የሆነውን ግን አይናገሩም።

ማንም ስለ ክፋቱ ንስሓ የገባ የለም፤

“ምን አድርጌአለሁ?” ይላል።

ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ፈረስ፣

እያንዳንዱ በራሱ መንገድ ይሄዳል።

7ሽመላ እንኳ በሰማይ፣

የተወሰነ ጊዜዋን ታውቃለች፤

ዋኖስ፣ ጨረባና ዋርዳም፣

የሚሰደዱበትን ጊዜ ያውቃሉ፤

ሕዝቤ ግን፣

የእግዚአብሔርን ሥርዐት አላወቀም።

8“ ‘የጸሓፊዎቻችሁ ሐሰተኛ ብርዕ ሐሰት

እያስተናገደ እንዴት፣ “ዐዋቂዎች ነን፣

የእግዚአብሔር ሕግ አለን” ትላላችሁ?

9ጥበበኞች ያፍራሉ፤

ይዋረዳሉ፤ በወጥመድም ይያዛሉ።

የእግዚአብሔርን ቃል ተቃውመው፣

ምን ዐይነት ጥበብ ይኖራቸዋል?

10ስለዚህ ሚስቶቻቸውንም ለሌሎች ወንዶች እሰጣለሁ፤

ዕርሻዎቻቸውንም ለባዕዳን እሰጣለሁ፤

ከታናሹ እስከ ታላቁ ድረስ፣

ሁሉም ተገቢ ላልሆነ ጥቅም ይስገበገባሉ፤

ነቢያትና ካህናትም እንዲሁ፤

ሁሉም ያጭበረብራሉ።

11የሕዝቤን ቍስል ብርቱ እንዳይደለ በመቍጠር፣

የተሟላ ፈውስ ሳይኖር እንዲሁ ያክማሉ፤

ሰላም ሳይኖር፣

“ሰላም፣ ሰላም” ይላሉ።

12ርኩሰት ሲፈጽሙ ዐፍረው ነበርን?

የለም! በጭራሽ አላፈሩም፤

ኀፍረት ምን እንደ ሆነም አያውቁም።

ስለዚህ ከወደቁት ጋር ይወድቃሉ፤

በምቀጣቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፣

ይላል እግዚአብሔር

13“ ‘ያመረቱትን ሁሉ እወስድባቸዋለሁ፤

ይላል እግዚአብሔር

በወይን ተክል ላይ የወይን ፍሬ አይኖርም፤

በበለስ ዛፍ ላይ የበለስ ፍሬ አይገኝም፤

ቅጠሎቻቸውም ይረግፋሉ።

የሰጠኋቸው በሙሉ፣

ከእነርሱ ይወሰድባቸዋል።8፥13 በዕብራይስጡ የዚህ ስንኝ ወይም ዐረፍተ ነገር ትርጕም በግልጽ አይታወቅም።

14“ለምን እዚህ እንቀመጣለን?

በአንድነት ተሰብሰቡ!

ወደ ተመሸጉት ከተሞች እንሽሽ፤

በዚያም እንጥፋ!

በእርሱ ላይ ኀጢአትን ስላደረግን፣

እግዚአብሔር አምላካችን እንድንጠፋ አድርጎናል፤

የተመረዘ ውሃ እንድንጠጣ ሰጥቶናል።

15ሰላምን ተስፋ አደረግን፤

መልካም ነገር ግን አልመጣም፤

የፈውስ ጊዜን ተመኘን፤

ነገር ግን ሽብር ብቻ ሆነብን።

16የጠላት ፈረሶች ፉርፉርታ፣

ከዳን ይሰማል፤

በድንጉላ ፈረሶቻቸው ማሽካካት፣

መላዋ ምድር ተንቀጠቀጠች።

ምድሪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣

ከተማዪቱንና በውስጧ የሚኖሩትን ሁሉ፣

ሊውጡ መጡ።

17“እነሆ፤ በመካከላችሁ መርዘኛ እባቦችን፣

የአስማተኛ ብልኀት የማይገታቸው እፉኝቶችን እሰድዳለሁ፤

እነርሱም ይነድፏችኋል፤”

ይላል እግዚአብሔር

18በሐዘኔ የምታጽናናኝ8፥18 የምታጽናናኝ በዕብራይስጡ የዚህ ቃል ትርጕም በግልጽ አይታወቅም። ሆይ፤

ልቤ በውስጤ ዝላለች።

19እንዲህ የሚለውን የሕዝቤን ጩኸት፣

ከሩቅ ምድር ስማ፤

እግዚአብሔር በጽዮን የለምን?

ንጉሧስ በዚያ አይኖርምን?”

“በተቀረጹ ምስሎቻቸው፣

እንዲሁም ከንቱ በሆኑ ባዕዳን ለምን አስቈጡኝ?”

20“መከሩ ዐለፈ፤

በጋው አበቃ፤

እኛም አልዳንም።”

21ሕዝቤ ሲቈስል፣

እኔም ቈሰልሁ፤

አለቀስሁ፤ ድንጋጤ ያዘኝ።

22በገለዓድ የሚቀባ መድኀኒት የለምን?

ወይስ በዚያ ሐኪም አልነበረምን?

ለሕዝቤ ቍስል፣

ለምን ፈውስ አልተገኘም?

Ketab El Hayat

إرميا 8:1-22

1وَيَقُولُ الرَّبُّ: «فِي ذَلِكَ الْحِينِ يَنْبِشُونَ مِنَ الْقُبُورِ عِظَامَ مُلُوكِ يَهُوذَا وَعِظَامَ رُؤَسَائِهِمْ وَكَهَنَتِهِمْ وَأَنْبِيَائِهِمْ، وَعِظَامَ سُكَّانِ أُورُشَلِيمَ. 2وَيَعْرِضُونَهَا أَمَامَ الشَّمْسِ وَالْقَمَرِ وَكَوَاكِبِ السَّمَاءِ الَّتِي أَحَبُّوهَا وَعَبَدُوهَا وَضَلُّوا وَرَاءَهَا، وَاسْتَشَارُوهَا وَسَجَدُوا لَهَا، فَلا تُجْمَعُ وَلا تُدْفَنُ، بَلْ تَصِيرُ نُفَايَةً فَوْقَ وَجْهِ الأَرْضِ، 3وَجَمِيعُ الْبَقِيَّةِ الْبَاقِيَةِ مِنْ هَذِهِ الْعَشِيرَةِ الشِّرِّيرَةِ الْمُشَتَّتَةِ فِي جَمِيعِ الْبِقَاعِ الَّتِي نَفَيْتُهُمْ إِلَيْهَا، يُؤْثِرُونَ الْمَوْتَ عَلَى الْحَيَاةِ».

الخطية والعقاب

4وَتَقُولُ لَهُمْ: «هَذَا مَا يُعْلِنُهُ الرَّبُّ: عِنْدَمَا يَسْقُطُ الرِّجَالُ، أَلا يَقُومُونَ ثَانِيَةً؟ وَعِنْدَمَا يَرْتَدُّونَ مُخْطِئِينَ أَلا يَرْجِعُونَ؟ 5فَمَا بَالُ شَعْبِ أُورُشَلِيمَ قَدِ ارْتَدُّوا ارْتِدَاداً دَائِماً مُتَشَبِّثِينَ بِالْخَدِيعَةِ وَرَافِضِينَ الرُّجُوعَ؟ 6قَدْ أَصْغَيْتُ وَسَمِعْتُ، وَإذَا بِهِمْ يَنْطِقُونَ بِمَا يُنَافِي الْحَقَّ، وَمَا مِنْ أَحَدٍ يَتُوبُ عَنْ شَرِّهِ قَائِلاً: مَا هَذَا الَّذِي أَرْتَكِبُ؟ بَلْ كُلُّ وَاحِدٍ مَضَى فِي طَرِيقِهِ كَفَرَسٍ مُنْدَفِعٍ لِخَوْضِ مَعْرَكَةٍ. 7إِنَّ اللَّقْلَقَ فِي السَّمَاءِ يَعْرِفُ مِيعَادَ هِجْرَتِهِ، وَالْيَمَامَةَ وَالسُّنُونَةَ الْمُغَرِّدَةَ تَحْفَظَانِ أَوَانَ عَوْدَتِهِمَا مِنْ هِجْرَتِهِمَا. أَمَّا شَعْبِي فَلا يَعْرِفُ قَضَاءَ الرَّبِّ! 8كَيْفَ تَدَّعُونَ أَنَّكُمْ حُكَمَاءُ وَلَدَيْكُمْ شَرِيعَةَ الرَّبِّ بَيْنَمَا حَوَّلَهَا قَلَمُ الْكَتَبَةِ المُخَادِعُ إِلَى أُكْذُوبَةٍ؟ 9سَيَلْحَقُ الْخِزْيُ بِالْحُكَمَاءِ وَيَعْتَرِيهِمِ الْفَزَعُ وَالذُّهُولُ، لأَنَّهُمْ رَفَضُوا كَلِمَةَ الرَّبِّ. إِذاً أَيَّةُ حِكْمَةٍ فِيهِمْ؟ 10لِذَلِكَ أُعْطِي نِسَاءَهُمْ لآخَرِينَ وَحُقُولَهُمْ لِلْوَارِثِينَ الْقَاهِرِينَ، لأَنَّهُمْ جَمِيعاً مِنْ صَغِيرِهِمْ إِلَى كَبِيرِهِمْ مُوْلَعُونَ بِالرِّبْحِ. حَتَّى النَّبِيُّ وَالْكَاهِنُ يَرْتَكِبَانِ الزُّورَ فِي أَعْمَالِهِمَا، 11وَيُعَالِجُونَ جِرَاحَ شَعْبِي بِاسْتِخْفَافٍ قَائِلِينَ: سَلامٌ، سَلامٌ فِي حِينِ لَا يُوْجَدُ سَلامٌ. 12هَلْ خَجِلُوا عِنْدَمَا اقْتَرَفُوا الرِّجْسَ؟ كَلَّا! لَمْ يَخْزَوْا قَطُّ وَلَمْ يَعْرِفُوا الْخَجَلَ. لِذَلِكَ سَيَسْقُطُونَ بَيْنَ السَّاقِطِينَ، وَحِينَ أُعَاقِبُهُمْ يُطَوَّحُ بِهِمْ»، يَقُولُ الرَّبُّ.

13«وَسَأُبِيدُهُمْ حَقّاً، إِذْ لَا يَكُونُ فِي الْكَرْمَةِ عِنَبٌ وَلا فِي التِّينَةِ تِينٌ، حَتَّى أَوْرَاقُ الأَشْجَارِ تَذْوِي وَتَتَسَاقَطُ، وَمَا أَغْدَقْتُهُ عَلَيْهِمْ مِنْ نِعَمٍ يُسْلَبُ مِنْهُمْ. 14فَمَا لَنَا قَابِعُونَ هُنَا؟ اجْتَمِعُوا مَعاً وَلْنَلْجَأْ إِلَى الْمُدُنِ الْحَصِينَةِ وَنَهْلِكْ هُنَاكَ، لأَنَّ الرَّبَّ إِلَهَنَا قَدْ قَضَى عَلَيْنَا بِالْهَلاكِ، وَأَعْطَانَا مَاءً مَسْمُوماً لِنَشْرَبَهُ، لأَنَّنَا أَخْطَأْنَا فِي حَقِّهِ. 15طَلَبْنَا السَّلامَ فَلَمْ يُسْفِرْ عَنْ خَيْرٍ. نَشَدْنَا وَقْتاً لِلْمُدَاوَاةِ فَابْتُلِينَا بِالأَهْوَالِ. 16قَدْ تَرَدَّدَتْ حَمْحَمَةُ خَيْلِهِمْ مِنْ أَرْضِ دَانَ، وَارْتَعَدَتِ الأَرْضُ مِنْ صَهِيلِ جِيَادِهِمْ. قَدْ أَقْبَلُوا وَاكْتَسَحُوا الأَرْضَ وَكُلَّ مَا فِيهَا، وَالْمَدِينَةَ وَأَهْلَهَا. 17انْظُرُوا، هَا أَنَا أُرْسِلُ عَلَيْكُمْ أَفَاعِيَ مُمِيتَةً لَا تَنْجَعُ مَعَهَا رُقىً فَتَلْدَغُكُمْ»، يَقُولُ الرَّبُّ.

18قَدْ غَلَبَ عَلَيَّ الْحُزْنُ وَقَلْبِي فِيَّ سَقِيمٌ. 19هُوَذَا صَرْخَةُ اسْتِغَاثَةِ أُورُشَلِيمَ تَتَجَاوَبُ مِنْ أَرْضٍ نَائِيَةٍ قَائِلَةً: «أَلَيْسَ الرَّبُّ فِي صِهْيَوْنَ؟ أَلَيْسَ مَلِكُهَا فِيهَا؟ لِمَاذَا أَثَارُوا غَيْظِي بِمَنْحُوتَاتِهِمْ وَأَوْثَانِهِمِ الْغَرِيبَةِ الْبَاطِلَةِ؟ 20قَدِ انْقَضَى مَوْسِمُ الْحَصَادِ، وَانْتَهَى الصَّيْفُ، وَنَحْنُ لَمْ نَخْلُصْ». 21لأَنَّ سَحْقَ أُورُشَلِيمَ هُوَ سَحْقِي، لِذَلِكَ أَنُوحُ وَقَدِ اشْتَدَّ بِيَ الرُّعْبُ. 22أَلا يُوْجَدُ بَلَسَانٌ فِي جِلْعَادَ؟ أَلَيْسَ هُنَاكَ طَبِيبٌ؟ فَلِمَاذَا إِذَنْ لَمْ تُشفَ جُرُوحُ شَعْبِي.