ኤርምያስ 42 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 42:1-22

1የቃሬያን ልጅ ዮሐናንና የሆሻያን ልጅ ያእዛንያን42፥1 የዕብራይስጡና የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች (43፥2 ይመ) አዛርያ ይላሉ። ጨምሮ፣ የጦር መኰንኖች ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡ ሁሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ ቀርበው፣ 2ነቢዩ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፤ “ቀድሞ ብዙዎች ነበርን አሁን እንደምታየን ግን የቀረነው ጥቂት ነን፤ ስለዚህ እባክህ ልመናችንን ስማ፤ ለዚህ ለተረፈው ሕዝብ ሁሉ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ። 3አምላክህ እግዚአብሔር ወዴት መሄድ እንዳለብንና ምን ማድረግ እንደሚገባን እንዲነግረን ጸልይልን።”

4ነቢዩ ኤርምያስም፣ “ሰምቻችኋለሁ፤ እንዳላችሁት ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር በርግጥ እጸልያለሁ፤ እግዚአብሔር ያለኝን ሁሉ አንዳች ሳላስቀር እነግራችኋለሁ” አላቸው።

5እነርሱም ኤርምያስን እንዲህ አሉት፤ “እግዚአብሔር አምላክህ በአንተ በኩል የሚለውን ነገር ሁሉ ባናደርግ፣ እግዚአብሔር ራሱ በእኛ ላይ እውነተኛና ታማኝ ምስክር ይሁን። 6አምላካችንን እግዚአብሔርን በመታዘዝ መልካም ይሆንልን ዘንድ ነገሩ ቢስማማንም ባይስማማንም፣ አንተን ወደ እርሱ የምንልክህን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንታዘዛለን።”

7ከዐሥር ቀን በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ። 8ስለዚህ የቃሬያን ልጅ ዮሐናንንና፣ ከእርሱም ጋር የነበሩትን የጦር መኰንኖች ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡን ሁሉ ከትንሽ እስከ ትልቅ ጠርቶ፤ 9እንዲህ አላቸው፤ “ልመናችሁን በፊቱ እንዳቀርብ ወደ እርሱ የላካችሁኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ 10‘ባመጣሁባችሁ ጥፋት ዐዝኛለሁና፣ በዚህች ምድር ብትቀመጡ እሠራችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፤ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም። 11አሁን የሚያስፈራችሁን የባቢሎንን ንጉሥ አትፍሩ፤ አድናችሁ ዘንድ ከእጁም አስጥላችሁ ዘንድ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና አትፍሩ ይላል እግዚአብሔር12እርሱ እንዲምራችሁና ወደ አገራችሁ እንዲመልሳችሁ እኔ እምራችኋለሁ።’

13“እናንተ ግን፤ ‘በዚህች ምድር አንቀመጥም’ ብትሉና አምላካችሁን እግዚአብሔርን ባትታዘዙ፣ 14ደግሞም፣ ‘ጦርነት ወደማናይበት፣ የመለከት ድምፅ ወደማንሰማበትና ወደማንራብበት ወደ ግብፅ ምድር ሄደን በዚያ እንኖራለን’ ብትሉ፣ 15እንግዲህ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ወደ ግብፅ ለመሄድ ወስናችሁ እዚያ ለመቀመጥ ብትሄዱ፣ 16የፈራችሁት ሰይፍ በዚያ ያገኛችኋል፤ የሠጋችሁበት ራብ እስከ ግብፅ ድረስ ተከትሏችሁ ይመጣል፤ በዚያም ትሞታላችሁ። 17በዚያም ለመኖር ወደ ግብፅ ለመሄድ የወሰኑ ሁሉ በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር በርግጥ ይሞታሉ፤ ከማመጣባቸውም ጥፋት አንድ እንኳ የሚተርፍ ወይም የሚያመልጥ አይገኝም።’ 18የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ‘ቍጣዬና መዓቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ሁሉ ላይ እንደ ፈሰሰ፣ እንዲሁ ወደ ግብፅ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ በእናንተ ላይ ይፈስሳል፤ እናንተም የመነቀፊያና የድንጋጤ፣ የመረገሚያና የመዘባበቻ ምልክት ትሆናላችሁ፤ ይህንም ስፍራ ዳግመኛ አታዩም።’

19“እናንተ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ፤ እግዚአብሔር፤ ‘ወደ ግብፅ አትሂዱ’ ብሏችኋል፤ እኔም ዛሬ እንዳስጠነቀቅኋችሁ በርግጥ ዕወቁ፤ 20‘ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን፤ እርሱ ያለህን ሁሉ ንገረን፤ እኛም እንታዘዛለን’ ብላችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር በላካችሁኝ ጊዜ ሕይወታችሁን የሚያጠፋ ስሕተት42፥20 ወይም በልባችሁ ስሕተት ሠራችሁ ፈጸማችሁ። 21እነሆ፤ ዛሬ በግልጥ ነገርኋችሁ፤ እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ልኮኝ የነገርኋችሁን ሁሉ አሁንም አልታዘዛችሁም፤ 22እንግዲህ ሄዳችሁ ልትኖሩበት በፈለጋችሁት ስፍራ በሰይፍ፣ በራብና በቸነፈር እንደምትሞቱ በርግጥ ዕወቁ።”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

耶利米书 42:1-22

耶利米警告犹大人勿去埃及

1加利亚的儿子约哈难何沙雅的儿子耶撒尼亚和其他将领及各阶层的民众前来, 2耶利米先知说:“求你答应我们的恳求,为我们这些余民向我们的上帝耶和华祈求。你也看见了,我们本来人数众多,现在却寥寥无几。 3愿你的上帝耶和华指示我们该去哪里,该做什么。” 4耶利米先知说:“好。我必照你们说的向你们的上帝耶和华祈求,并把祂的话毫不隐瞒地告诉你们。” 5他们说:“倘若我们不照你的上帝耶和华说的去做,愿诚实可靠的耶和华作证指控我们! 6不论我们的上帝耶和华说什么,我们都愿意听从。我们若听祂的话,就必亨通。”

7十天之后,耶和华的话传给了耶利米8耶利米便召集加利亚的儿子约哈难和众将领及各阶层的民众, 9对他们说:“你们让我向以色列的上帝耶和华祈求,耶和华这样说, 10‘如果你们留在这地方,我必扶持你们,决不毁灭你们;我必栽培你们,决不铲除你们。因为我为降在你们身上的灾祸而难过。 11不要惧怕巴比伦王,不要怕他,因为我必与你们同在,拯救你们脱离他的权势。这是耶和华说的。 12我必怜悯你们,也要让他怜悯你们,使你们重归故土。’ 13然而,如果你们不听你们的上帝耶和华的话,不留在这地方, 14非要去埃及住,以为那里没有战争,听不见号角声,也不会忍饥挨饿, 15那么,你们这些犹大的余民就要听听耶和华的话。以色列的上帝——万军之耶和华说,‘如果你们决意去埃及住, 16你们所害怕的战争和饥荒必紧紧地跟着你们。你们必死在埃及17凡决意去埃及住的人必要死于战争、饥荒和瘟疫,无人能逃脱我降的灾祸。’

18以色列的上帝——万军之耶和华说,‘我曾把烈怒倾倒在耶路撒冷人身上,如果你们去埃及,我也要把我的怒气倾倒在你们身上。你们的下场将很可怕,被人责骂、咒诅和羞辱,再也见不到故土。’ 19犹大的余民啊,耶和华已告诉你们不要去埃及。别忘了我今日给你们的警告, 20你们是在自欺,因为原是你们请我去向我们的上帝耶和华祈求,让我毫不隐瞒地把祂的话告诉你们,你们也答应遵行。 21今日,我把你们上帝耶和华的话告诉了你们,你们却不听从。 22因此,你们要清楚知道,你们如果决意去埃及住,必死于战争、饥荒和瘟疫。”