ኤርምያስ 41 – NASV & BPH

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 41:1-18

1ከንጉሣዊ ቤተ ሰብ የሆነው ከንጉሡ የጦር መኰንንኖች አንዱ የነበረው የኤሊሳማ ልጅ የናታንያ ልጅ እስማኤል፣ በሰባተኛው ወር ከዐሥር ሰዎች ጋር ወደ ምጽጳ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ፤ በዚያም በአንድነት ሊበሉ በማእድ ተቀምጠው ሳለ፣ 2የናታንያ ልጅ እስማኤልና አብረውት የነበሩ ዐሥሩ ሰዎች ተነሥተው፣ የባቢሎን ንጉሥ በምድሪቱ ላይ ገዥ አድርጎ የሾመውን የሳፋንን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መቱት፤ ገደሉትም። 3ደግሞም እስማኤል በምጽጳ ከጎዶልያስ ጋር የነበሩትን አይሁድ ሁሉ፣ በዚያም የተገኙትን የባቢሎን41፥3 ወይም የከለዳውያን ወታደሮች ገደላቸው።

4ጎዶልያስ በተገደለ ማግስት፣ ማንም ስለ ሁኔታው ከማወቁ በፊት፣ 5ሰማንያ ሰዎች ጢማቸውን ተላጭተው፣ ልብሳቸውን ቀድደው፣ ገላቸውን ነጭተው የእህል ቍርባንና ዕጣን በመያዝ ከሴኬም፣ ከሴሎና ከሰማርያ ወደ እግዚአብሔር ቤት ለማቅረብ መጡ። 6የናታንያ ልጅ እስማኤል ሊገናኛቸው እያለቀሰ ከምጽጳ ወጣ፤ ሲያገኛቸውም፣ “ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ኑ” አላቸው። 7ወደ ከተማዪቱ በገቡ ጊዜ፣ የናታንያ ልጅ እስማኤልና አብረውት የነበሩ ሰዎች ዐረዷቸው፤ በውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓድ ውስጥም ጣሏቸው። 8ከተገደሉት ጋር የነበሩ ዐሥር ሰዎች ግን እስማኤልን፣ “እባክህ አትግደለን! በዕርሻችን ውስጥ የሸሸግነው ስንዴና ገብስ፣ የወይራ ዘይትና ማር ስላለን እባክህን አትግደለን” አሉት። እርሱም ተዋቸው፤ ከሌሎቹም ጋር አልገደላቸውም። 9እስማኤል ከጎዶልያስ በተጨማሪ የገደላቸው ሰዎች ሁሉ ሬሳ የተጣለበት የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓድ፣ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ስለ ፈራ ለመከላከል ያሠራው ነበር፤ ይህን ጕድጓድ የናታንያ ልጅ እስማኤል በሬሳ ሞላው።

10እስማኤል በምጽጳ የቀረውን ሕዝብ ሁሉ ምርኮኛ አደረገ፤ እነርሱም የባቢሎን የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡረዘረዳን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው ገዥ አድርጎ የሾመባቸው የንጉሡ ሴቶች ልጆችና በዚያ የቀሩት ሌሎች ሰዎች ሁሉ ነበሩ። የናታንያ ልጅ እስማኤል እነዚህን ማርኮ ወደ አሞናውያን ለመሻገር ተነሣ።

11የቃሬያ ልጅ ዮሐናና ከእርሱ ጋር የነበሩት የጦር መኰንኖች ሁሉ የናታንያ ልጅ እስማኤል የፈጸመውን ግፍ ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣ 12የናታንያን ልጅ እስማኤልን ሊወጉ ሰዎቻቸውን ሁሉ ይዘው ሄዱ፤ በገባዖንም ባለው በታላቁ ኵሬ አጠገብ ደረሱበት። 13እስማኤል የያዛቸው ሰዎች ሁሉ የቃሬያን ልጅ ዮሐናንንና አብረውት የነበሩትን የጦር መኰንኖች ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው። 14እስማኤል ከምጽጳ ማርኮ የወሰዳቸው ሰዎች ሁሉ አምልጠው ወደ ቃሬያ ልጅ ወደ ዮሐናን ገቡ። 15የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን አብረውት ከነበሩት ስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ፤ ሸሽቶም ወደ አሞናውያን ገባ።

ሽሽት ወደ ግብፅ

16የቃሬያ ልጅ ዮሐናንና ከእርሱ ጋር የነበሩት የጦር መኰንንኖች ሁሉ የናታንያ ልጅ እስማኤል የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ከገደለ በኋላ፣ በምጽጳ ከማረካቸው የተረፉትን ሰዎች በማስመለስ ይዘው ሄዱ፤ እነዚህም፣ ወታደሮች፣ ሴቶች ሕፃናትና ከገባዖን ያመጧቸው የቤተ መንግሥት ባለ ሥልጣኖች ነበሩ። 17ከዚያም ተነሥተው ሄዱ፤ ወደ ግብፅም በማምራት በቤተ ልሔም አጠገብ ባለችው በጌሮት ከመዓም ዐረፉ፤ 18ወደ ግብፅም የሄዱት ከባቢሎናውያን41፥18 ወይም ከከለዳውያን ለማምለጥ ነበር፤ ባቢሎናውያንንም የፈሩት የናታንያ ልጅ እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ የምድሪቱ ገዥ አድርጎ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በመግደሉ ነው።

Bibelen på hverdagsdansk

Jeremiasʼ Bog 41:1-18

Ishmaels oprør og Gedaljas død

1Men allerede samme år i den syvende måned kom Ishmael til Mitzpa med ti mand og opsøgte Gedalja. Ishmael var af kongelig herkomst og en af den tidligere konges betroede embedsmænd. Gedalja inviterede dem til spisning dér i Mitzpa. 2Under måltidet sprang Ishmael og hans mænd pludselig op, trak deres sværd og dræbte Gedalja. 3Derefter løb de ud og dræbte samtlige judæiske embedsmænd og babyloniske soldater i guvernørens hovedkvarter.

4Næste dag, før nogen vidste noget om mordet på Gedalja, 5var en gruppe på 80 mænd fra Sikem, Shilo og Samaria på vej til Jerusalem med korn og røgelse for at ofre til Herren. De havde raget skægget af, revet flænger i tøjet og skåret sig i huden for at vise deres sorg over Jerusalems fald. 6Da de nærmede sig Mitzpa, kom Ishmael dem grædende i møde og sagde: „Kom og se, hvad der er sket med Gedalja.”

7Men så snart de var kommet ind i byen, begyndte Ishmael og hans mænd at slå dem ihjel og kaste ligene i et vandreservoir. 8Ti af dem undgik døden ved at love at give ham deres forråd af hvede, byg, olivenolie og honning, som de havde skjult i nærheden af byen. 9Det vandreservoir, som Ishmael kastede de 70 mænd ned i, havde kong Asa ladet bygge, dengang han befæstede Mitzpa i krigen mod kong Basha af Israel.

10Ishmael tog så resten af byens indbyggere til fange, både kongens døtre og alle dem, som Nebuzaradan havde overladt i Gedaljas varetægt i Mitzpa, og flygtede til ammonitternes land.

11Men da Johanan og de øvrige officerer hørte, hvad Ishmael havde gjort, 12samlede de alle deres mænd og satte efter ham, og de indhentede ham ved dammen nær Gibeon. 13-14Så snart Ishmaels fanger fra Mitzpa fik øje på Johanan og hans mænd, jublede de af glæde og sluttede sig til ham. 15Ishmael undslap med nød og næppe sammen med otte af sine mænd og nåede i sikkerhed i Ammon.

16-17Johanan og hans mænd tog nu alle dem, de havde befriet, soldater, kvinder, børn og hoffolk, og førte dem til landsbyen Gidrot-Kimham ved Betlehem. De havde nemlig planer om at tage til Egypten, 18for de var bange for, hvordan babylonierne ville reagere på budskabet om Gedaljas død. Gedalja var jo blevet indsat som guvernør af selveste den babyloniske konge.