ኤርምያስ 36 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 36:1-32

ኢዮአቄም የኤርምያስን ብራና አቃጠለ

1የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ የነበረው ኢዮአቄም በነገሠ በአራተኛው ዓመት እንዲህ የሚል ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ፤ 2“የብራና ጥቅልል ውሰድ፤ ለአንተም መናገር ከጀመርሁበት ከኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት አንሥቶ እስካሁን ድረስ ስለ እስራኤል፣ ስለ ይሁዳና ስለ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉ የነገርሁህን ቃል ሁሉ ጻፍበት፤ 3ምናልባትም የይሁዳ ሕዝብ ላመጣባቸው ያሰብሁትን ጥፋት ሁሉ ሲሰሙ፣ እያንዳንዳቸው ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም ክፋታቸውንና ኀጢአታቸውን ይቅር እላለሁ።”

4ኤርምያስም የኔርያን ልጅ ባሮክን ጠራው፤ ባሮክም እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ ተቀብሎ በብራናው ላይ ጻፈ። 5ኤርምያስም ባሮክን እንዲህ አለው፤ “እኔ ተከልክያለሁና ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መግባት አልችልም፤ 6ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሄደህ፣ በቃል እየነገርሁህ በብራናው ላይ የጻፍኸውን የእግዚአብሔርን ቃል በጾም ቀን ለተሰበሰበው ሕዝብ አንብብ፤ ከየከተሞቻቸው ለመጡት ለይሁዳ ሕዝብ ሁሉ አንብብ። 7እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቍጣና መቅሠፍት ታላቅ ስለሆነ፣ ምናልባት ልመናቸውን በእግዚአብሔር ፊት በማቅረብ እያንዳንዳቸው ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል።”

8የኔርያ ልጅ ባሮክ ነቢዩ ኤርምያስ የነገረውን ሁሉ አደረገ፤ በእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ የእግዚአብሔርን ቃል ከብራናው አነበበ። 9የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ የሆነው ኢዮአቄም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር በኢየሩሳሌም የሚኖረው ሕዝብ ሁሉና ከይሁዳ ከተሞች የመጡት ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ጾም ዐወጁ። 10ባሮክም በብራና ላይ የተጻፈውን የኤርምያስን ቃል በእግዚአብሔር ቤት በላይኛው አደባባይ፤ “አዲሱ በር” በሚባለው በቤተ መቅደሱ መግቢያ ላይ በሚገኘው በጸሓፊው በሳፋን ልጅ በገማርያ ክፍል ውስጥ ሆኖ ለሕዝቡ ሁሉ አነበበው።

11የሳፋን ልጅ የገማርያ ልጅ ሚክያስ ከብራናው የተነበበውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ በሰማ ጊዜ፣ 12በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ወዳለው ወደ ጸሓፊው ክፍል ወረደ፤ በዚያም መኳንንቱ ሁሉ፦ ጸሓፊው ኤሊሳማ፣ የሸማያ ልጅ ድላያ፣ የዓክቦር ልጅ ኤልናታን፣ የሳፋን ልጅ ገማርያ፣ የሐናንያ ልጅ ሴዴቅያስ እንዲሁም ሌሎች መኳንንት ሁሉ ተቀምጠው ነበር። 13ባሮክ ለሕዝቡ ከብራናው ሲያነብ ሚክያስ የሰማውን ሁሉ ከነገራቸው በኋላ፣ 14መኳንንቱ ሁሉ የኩሲን ልጅ የሴሌምያን ልጅ የናታንያን ልጅ ይሁዲን፣ “ለሕዝቡ ያነበብኸውን ብራና ይዘህ እንድትመጣ” ብለው ወደ ባሮክ ላኩ። የኔርያም ልጅ ባሮክ ብራናውን ይዞ ወደ እነርሱ መጣ፤ 15እነርሱም፣ “እስቲ ተቀምጠህ አንብብልን” አሉት። ባሮክም አነበበላቸው፤ 16እነርሱም ቃሉን ሁሉ በሰሙ ጊዜ እርስ በርሳቸው በፍርሀት በመተያየት ባሮክን፣ “ይህን ሁሉ ቃል ለንጉሡ መንገር ይገባናል።” አሉት፤ 17ደግሞም፣ “ይህን ሁሉ እንዴት ልትጽፍ እንደ ቻልህ ንገረን፤ ኤርምያስ በቃል እየነገረህ ነውን?” ብለው ባሮክን ጠየቁት።

18ባሮክም፣ “አዎን ይህን ሁሉ በቃሉ ነገረኝ፤ እኔም በብራናው ላይ በቀለም ጻፍሁ” ብሎ መለሰላቸው።

19መኳንንቱም ባሮክን፣ “እንግዲያውስ አንተና ኤርምያስ ሄዳችሁ ተሸሸጉ፤ የት እንዳላችሁም ማንም አይወቅ” አሉት።

20የብራናውን ጥቅልል በጸሓፊው በኤሊሳማ ክፍል ካስቀመጡት በኋላ፣ ንጉሡ ወዳለበት አደባባይ ሄደው የሆነውን ሁሉ ነገሩት። 21ንጉሡም ብራናውን ያመጣ ዘንድ ይሁዲን ላከው፤ ይሁዲም ከጸሓፊው ከኤሊሳማ ክፍል ብራናውን አምጥቶ፣ ለንጉሡና በንጉሡ አጠገብ ቆመው ለነበሩት መኳንንት ሁሉ አነበበላቸው። 22ዘጠነኛው ወር እንደ መሆኑ፣ ንጉሡ የክረምትን ወራት በሚያሳልፍበት ቤት ተቀምጦ ነበር፤ በምድጃ የሚነድድ እሳትም ፊት ለፊቱ ነበር። 23ይሁዲ ከብራናው ሦስት ወይም አራት ዐምድ ባነበበ ቍጥር ንጉሡ ብራናው ሁሉ እስከሚያልቅ ድረስ በጸሓፊ ቢላዋ እየቈረጠ እንዲቃጠል ወደ እሳቱ ምድጃ ይጥል ነበር። 24ንጉሡም ሆነ ይህን ሁሉ ቃል የሰሙት መኳንንት ሁሉ አንዳች አልፈሩም፤ ልብሳቸውንም አልቀደዱም። 25ኤልናታን፣ ድላያ፣ ገማርያም ንጉሡ ብራናውን እንዳያቃጥል ቢለምኑትም እንኳ አልሰማቸውም፣ 26ይልቁንም ጸሓፊውን ባሮክንና ነቢዩን ኤርምያስን ይዘው ያስሩ ዘንድ የንጉሡን ልጅ ይረምሕኤልን፣ የዓዝርኤልን ልጅ ሠራያንና የአብድኤልን ልጅ ሰሌምያን አዘዘ፤ እግዚአብሔር ግን ሰውሯቸው ነበር።

27ንጉሡ፣ ባሮክ ከኤርምያስ አፍ ተቀብሎ የጻፈው ቃል ያለበትን ብራና ካቃጠለ በኋላ፤ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤ 28“ሌላ ብራና ወስደህ፣ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም ባቃጠለው በመጀመሪያው ብራና ላይ የነበረውን ቃል ሁሉ ጻፍበት፤ 29ለይሁዳ ንጉሥ ለኢዮአቄም እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የባቢሎን ንጉሥ በርግጥ ይመጣል፤ ይህችን ምድር፣ በእርሷም ላይ የሚኖሩትን ሰዎችንና እንስሳትን ያጠፋል በማለት የጻፍህበት ለምንድን ነው?” ብለህ ብራናውን አቃጥለሃል። 30ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፤ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ከዘሩ አይገኝም፤ ሬሳውም ወደ ውጭ ተጥሎ ለቀን ሐሩርና ለሌሊት ቍር ይጋለጣል። 31እርሱንና ልጆቹን መኳንንቱንም ስለ ክፋታቸው እቀጣለሁ፤ አልሰሙኝምና አመጣባቸዋለሁ ያልሁትን ጥፋት ሁሉ በእነርሱና በኢየሩሳሌም በሚኖሩት፣ በይሁዳም ሕዝብ ላይ አመጣለሁ።’ ”

32ኤርምያስም ሌላ ብራና ወስዶ ለኔርያ ልጅ ለጸሓፊው ለባሮክ ሰጠው፤ ባሮክም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ባቃጠለው ብራና ላይ የነበረውን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ ተቀብሎ ጻፈበት፤ ብዙ ተመሳሳይ ቃልም ተጨመረበት።

Thai New Contemporary Bible

เยเรมีย์ 36:1-32

เยโฮยาคิมเผาม้วนหนังสือของเยเรมีย์

1ในปีที่สี่แห่งรัชกาลเยโฮยาคิมโอรสกษัตริย์โยสิยาห์แห่งยูดาห์ มีพระดำรัสขององค์พระผู้เป็นเจ้ามาถึงเยเรมีย์ว่า 2“จงเอาหนังสือม้วนมาเขียนทุกถ้อยคำของเราที่เกี่ยวกับอิสราเอล ยูดาห์ และชนชาติอื่นๆ ทั้งปวง ตั้งแต่ครั้งที่เราเริ่มพูดกับเจ้าในรัชกาลโยสิยาห์จนถึงเดี๋ยวนี้ 3เผื่อบางทีเมื่อชนยูดาห์ได้ยินเกี่ยวกับภัยพิบัติทั้งปวงที่เราคิดจะทำแก่เขานั้นแล้วจะรู้สึกตัวและหันกลับจากวิถีชั่วของตน เราก็จะให้อภัยความชั่วและบาปของเขา”

4ดังนั้นเยเรมีย์จึงเรียกบารุคบุตรเนริยาห์มา และบอกพระดำรัสขององค์พระผู้เป็นเจ้าซึ่งมีมาถึงตนให้บารุคบันทึกลงในหนังสือม้วน 5แล้วเยเรมีย์บอกบารุคว่า “เราถูกกักกัน จึงไม่สามารถไปยังพระวิหารขององค์พระผู้เป็นเจ้าได้ 6ฉะนั้นเจ้าจงไปยังพระวิหารขององค์พระผู้เป็นเจ้าในวันถืออดอาหารและอ่านพระดำรัสขององค์พระผู้เป็นเจ้าจากหนังสือม้วนที่เจ้าบันทึกตามคำบอกของเรานี้ให้ชาวยูดาห์ทั้งปวงซึ่งมาจากหัวเมืองต่างๆ ฟัง 7เผื่อบางทีพวกเขาจะมาทูลวิงวอนต่อองค์พระผู้เป็นเจ้า และหันกลับจากวิถีชั่วของตน เพราะพระพิโรธและโทสะซึ่งองค์พระผู้เป็นเจ้าได้ประกาศไว้เหนือประชาชาตินี้ใหญ่หลวงนัก”

8บารุคบุตรเนริยาห์ก็ทำตามที่ผู้เผยพระวจนะเยเรมีย์สั่งไว้ทุกประการ และอ่านข้อความขององค์พระผู้เป็นเจ้าทั้งหมดนี้จากหนังสือม้วนให้ประชาชนที่พระวิหารขององค์พระผู้เป็นเจ้าฟัง 9ในเดือนที่เก้า ปีที่ห้าแห่งรัชกาลเยโฮยาคิมโอรสกษัตริย์โยสิยาห์แห่งยูดาห์ มีประกาศให้ประชาชนทั้งปวงในเยรูซาเล็มและหัวเมืองต่างๆ ของยูดาห์มาถืออดอาหารต่อหน้าองค์พระผู้เป็นเจ้า 10จากห้องของเกมาริยาห์บุตรราชเลขาชาฟานซึ่งอยู่ในลานด้านบนตรงทางเข้าประตูใหม่ของพระวิหาร บารุคก็อ่านถ้อยคำของเยเรมีย์จากหนังสือม้วนนั้นให้ประชากรทั้งหมดซึ่งอยู่ที่พระวิหารขององค์พระผู้เป็นเจ้าฟัง

11เมื่อมีคายาห์บุตรเกมาริยาห์บุตรของชาฟานได้ยินพระดำรัสทั้งปวงขององค์พระผู้เป็นเจ้าจากม้วนหนังสือนั้น 12ก็ลงมายังห้องของราชเลขาในพระราชวัง ซึ่งบรรดาข้าราชบริพารทั้งปวงนั่งอยู่ ได้แก่ราชเลขาเอลิชามา เดไลยาห์บุตรเชไมอาห์ เอลนาธันบุตรอัคโบร์ เกมาริยาห์บุตรชาฟาน เศเดคียาห์บุตรฮานันยาห์ และข้าราชบริพารอื่นๆ ทุกคน 13เมื่อมีคายาห์เล่าทุกอย่างตามที่ได้ยินบารุคอ่านจากหนังสือม้วนให้ประชาชนฟังแล้ว 14พวกเขาก็ส่งเยฮูดีบุตรเนธานิยาห์ซึ่งเป็นบุตรเชเลมิยาห์บุตรคูชีมาบอกบารุคว่า “จงนำหนังสือม้วนที่ท่านอ่านให้ประชาชนฟังนั้นมาเถิด” บารุคบุตรเนริยาห์จึงมาพบพวกเขาพร้อมกับหนังสือม้วน 15พวกเขากล่าวกับบารุคว่า “จงนั่งลงอ่านให้เราฟังเถิด”

บารุคจึงอ่านให้ฟัง 16เมื่อพวกเขาได้ยินเนื้อความทั้งหมดแล้ว ก็มองหน้ากันด้วยความหวาดกลัวและกล่าวกับบารุคว่า “เราต้องทูลรายงานเนื้อความเหล่านี้ให้กษัตริย์ทรงทราบ” 17แล้วพวกเขาจึงถามบารุคว่า “บอกเราสิว่า เหตุใดเจ้าจึงเขียนเรื่องราวทั้งหมดนี้? เยเรมีย์บอกให้เจ้าเขียนหรือ?”

18บารุคตอบว่า “ถูกแล้ว ท่านเยเรมีย์เป็นผู้บอกข้อความทั้งหมดนี้ให้ข้าพเจ้าเขียนด้วยหมึกลงในหนังสือม้วน”

19ข้าราชบริพารเหล่านั้นจึงกล่าวกับบารุคว่า “ทั้งเจ้าและเยเรมีย์ จงไปซ่อนตัว อย่าให้ใครรู้ว่าเจ้าอยู่ที่ไหน”

20หลังจากที่พวกเขาเก็บหนังสือม้วนไว้ในห้องของราชเลขาเอลิชามาแล้ว ก็ไปเข้าเฝ้ากษัตริย์เยโฮยาคิมที่ท้องพระโรง ทูลรายงานทุกสิ่งให้ทรงทราบ 21กษัตริย์ทรงใช้เยฮูดีมาเอาหนังสือม้วนไป เยฮูดีนำหนังสือม้วนจากห้องของราชเลขาเอลิชามาไปอ่านถวายกษัตริย์ ขณะที่ข้าราชบริพารทั้งปวงยืนเฝ้าอยู่ใกล้ๆ 22ขณะนั้นเป็นเดือนที่เก้าและกษัตริย์ประทับอยู่ที่ตำหนักฤดูหนาว มีเตาไฟลุกโชนตั้งอยู่ต่อหน้า 23ทุกครั้งที่เยฮูดีอ่านหนังสือม้วนไปได้สามสี่ตอน กษัตริย์จะทรงใช้มีดของอาลักษณ์ตัดส่วนนั้นออกและเหวี่ยงทิ้งลงไปในไฟ จนกระทั่งหนังสือม้วนทั้งหมดถูกเผา 24กษัตริย์และข้าราชบริพารทั้งปวงที่ได้ฟังเนื้อความทั้งหมดนี้ไม่ได้แสดงท่าทีหวาดหวั่นแต่อย่างใด ทั้งไม่ได้ฉีกเสื้อผ้าของตน 25ทั้งๆ ที่เอลนาธันและเดไลยาห์กับเกมาริยาห์ทูลวิงวอนกษัตริย์ไม่ให้เผาหนังสือม้วน พระองค์ก็ไม่ทรงฟัง 26กลับตรัสสั่งให้เยราเมเอลโอรสองค์หนึ่ง และเสไรอาห์บุตรอัสรีเอลกับเชเลมิยาห์บุตรอับเดเอลไปจับกุมตัวบารุคผู้เป็นอาลักษณ์และจับผู้เผยพระวจนะเยเรมีย์มา แต่องค์พระผู้เป็นเจ้าทรงซ่อนทั้งสองไว้

27หลังจากที่กษัตริย์ทรงเผาหนังสือม้วนซึ่งบารุคบันทึกถ้อยคำตามคำบอกของเยเรมีย์ไปแล้ว มีพระดำรัสขององค์พระผู้เป็นเจ้ามาถึงเยเรมีย์ว่า 28“จงเอาหนังสือม้วนใหม่มาบันทึกถ้อยคำทั้งหมดที่ได้เขียนไว้ในหนังสือม้วนแรกซึ่งกษัตริย์เยโฮยาคิมแห่งยูดาห์ได้เผาไปแล้ว 29และจงบอกกษัตริย์เยโฮยาคิมแห่งยูดาห์ด้วยว่า ‘องค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสดังนี้ว่า เจ้าเผาหนังสือม้วนนั้นไปและกล่าวว่า “ทำไมจึงเขียนลงไปว่ากษัตริย์บาบิโลนจะมาทำลายล้างดินแดนนี้และจะกำจัดทั้งคนและสัตว์ไปจากแผ่นดิน?” 30ดังนั้นองค์พระผู้เป็นเจ้าตรัสเกี่ยวกับกษัตริย์เยโฮยาคิมแห่งยูดาห์ดังนี้ว่า เขาจะไม่มีทายาทนั่งบนบัลลังก์ดาวิด ร่างของเขาจะถูกเหวี่ยงทิ้งให้ตากแดดตอนกลางวัน และตากน้ำค้างแข็งตอนกลางคืน 31เราจะลงโทษเขา ลูกหลาน และเหล่าข้าราชบริพารของเขา เพราะความชั่วร้ายของพวกเขา เราจะนำภัยพิบัติทั้งปวงซึ่งเราได้ประกาศไว้แล้วนั้นมายังเขาและบรรดาผู้ที่อาศัยอยู่ในเยรูซาเล็มกับยูดาห์ เพราะพวกเขาไม่ยอมฟัง’”

32เยเรมีย์จึงนำหนังสือม้วนใหม่มาให้อาลักษณ์บารุคบุตรเนริยาห์เขียนตามคำบอกของตน มีข้อความครบถ้วนเหมือนในม้วนที่กษัตริย์เยโฮยาคิมแห่งยูดาห์เผาทิ้งไปแล้ว และมีข้อความคล้ายคลึงกันอีกมากมายเพิ่มเข้ามา