ኤርምያስ 21 – NASV & HTB

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 21:1-14

ለንጉሥ ሴዴቅያስ የተሰጠ ምላሽ

1የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ፣ የመልክያን ልጅ ጳስኮርን እንዲሁም የመዕሤያን ልጅ ካህኑን ሶፎንያስን ወደ እርሱ በላከ ጊዜ፣ ቃል ከእግዚአብሔር ወደ ኤርምያስ መጣ፤ የተላኩትም እንዲህ ብለውት ነበር፤ 2“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር21፥2 ናቡከደነፆር አቻ የሆነው የዕብራይስጡ ናቡከደነፆር በዚህ ክፍልና ብዙ ጊዜ በኤርምያስና ሕዝቅኤል መጽሐፍ ይገኛል። ሊወጋን ስለሆነ፣ እባክህን ፈጥነህ፣ እግዚአብሔርን ጠይቅልን፤ ምናልባት ንጉሡ ከእኛ ይመለስ ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ቀድሞው ታምራት ያደርግልን ይሆናል” ብለው ነበር።

3ኤርምያስ ግን እንዲህ አላቸው፤ “ለሴዴቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፤ 4‘የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከቅጥሩ ውጭ የከበቧችሁን የባቢሎንን ንጉሥና ባቢሎናውያንን21፥4 ወይም ከለዳውያን፤ 9 ላይ ይመ። ለመውጋት በእጃችሁ የያዛችሁትን የጦር መሣሪያ በእናንተው ላይ አዞራለሁ፤ ወደዚህችም ከተማ ሰብስቤ አስገባቸዋለሁ። 5እኔ ራሴ ለቅጣት በተዘረጋ እጅና በብርቱ ክንድ፣ በቍጣና በመዓት፣ በታላቅም መቅሠፍት እወጋችኋለሁ። 6በዚህች ከተማ የሚኖሩትን፣ ሰዎችንም ሆኑ እንስሳትን እመታለሁ፤ እነርሱም በታላቅ መቅሠፍት ይሞታሉ። 7ከዚያ በኋላ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና መኳንንቱን፣ ከመቅሠፍት፣ ከሰይፍና ከራብ የተረፈውንም ሕዝብ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆርና ሕይወታቸውን ለማጥፋት ለሚሹ ጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እርሱም በሰይፍ ይመታቸዋል፤ አያዝንላቸውም፤ አይራራላቸውም፤ አይምራቸውምም።’

8“በተጨማሪም ለዚህ ሕዝብ እንዲህ በል፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ በፊታችሁ አድርጌአለሁ፤ 9በዚህች ከተማ የሚቈይ ሁሉ በሰይፍ፣ በራብና በመቅሠፍት ይሞታል፤ ወጥቶ ለከበቧችሁ ባቢሎናውያን እጁን የሚሰጥ ግን ነፍሱን ያተርፋል፤ በሕይወትም ይኖራል። 10በዚህች ከተማ ላይ በጎ ሳይሆን ክፉ ለማድረግ ወስኛለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር፤ ለባቢሎን ንጉሥ ትሰጣለች፤ እርሱም በእሳት ያጠፋታል።’

11“ለይሁዳ ንጉሥ ቤትም እንዲህ በል፤ ‘የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ 12የዳዊት ቤት ሆይ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ ‘ካደረጋችሁት ክፋት የተነሣ፣

ቍጣዬ እንዳይቀጣጠል፣

ማንም ሊያጠፋው እስከማይችል እንዳይነድድ፣

በየማለዳው ፍትሕን አድርጉ፤

የተበዘበዘውን ሰው፣

ከጨቋኙ እጅ አድኑት።

13ከሸለቆው በላይ፣

በድንጋያማው ዐምባ ላይ የምትኖሪ ሆይ፤

እኔ በአንቺ ላይ ወጥቻለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር

“ማን በእኛ ላይ ይወጣል?

ማንስ ወደ መኖሪያችን ደፍሮ ይገባል?” የምትሉ ሆይ፤

14እንደ ሥራችሁ መጠን እቀጣችኋለሁ፤

ይላል እግዚአብሔር

በዱሯም እሳት እለኵሳለሁ፤

በዙሪያዋ ያለውንም ሁሉ ይበላል።’ ”

Het Boek

Jeremia 21:1-14

Het verzoek van de koning afgewezen

1-2 De Here sprak tegen Jeremia toen koning Zedekia Pashur, de zoon van Malkia, en de priester Zefanja, de zoon van Maäseja, naar Jeremia stuurde en smeekte: ‘Vraag de Here ons te helpen, want koning Nebukadnezar van Babel valt ons aan! Misschien wil de Here ons genadig zijn en een machtig wonder doen, zoals Hij vroeger deed, zodat Nebukadnezar zijn troepen moet terugtrekken.’

3-4 Jeremia antwoordde: ‘Ga terug naar koning Zedekia en zeg hem dat de Here God van Israël zegt: “Al uw wapens zal Ik tegen u gebruiken in de strijd tegen de koning van Babel en de Chaldeeën die u belegeren. Ik zal de vijand massaal tot in het hart van deze stad laten doordringen. 5Ik zal Zelf tegen u vechten en mijn vurige toorn op u koelen. 6Ik zal deze stad treffen met een verschrikkelijke pest waardoor mens en dier zullen sterven. 7En uiteindelijk zal Ik koning Zedekia, zijn hofhouding en alle in de stad overgebleven inwoners overgeven aan koning Nebukadnezar van Babel. Hij zal hen zonder genade afslachten.” 8Vertel deze mensen dat de Here zegt: “Maak nu uw keus tussen leven en dood! 9Wie hier in Jeruzalem blijft, zal worden gedood door uw vijanden of sterven van de honger of ziekte. Maar wie de stad uitgaat en zich overgeeft aan de Chaldeeën, blijft in leven. 10Want Ik heb Mij tegen deze stad gekeerd, Ik zal haar vijand en niet meer haar vriend zijn,” zegt de Here. “De koning van Babel zal de stad innemen en haar volledig in de as leggen.” ’

11-12 Wat het koningshuis van Juda betreft, moest Jeremia van de Here het volgende zeggen: ‘Geslacht van David, luister naar wat de Here u te zeggen heeft: “Ik sta klaar om u te veroordelen voor al het kwaad dat u hebt gedaan. Wees rechtvaardig voor degenen die u berecht! En snel, voordat mijn brandende toorn op u neerkomt als een vuur dat geen mens kan doven. 13Ik zal vechten tegen de stad Jeruzalem, die daar op een rots boven het dal ligt en nu nog bralt: ‘Wij zijn veilig, niemand kan ons hier wat doen!’ 14Maar Ik zal u straffen om uw zonden,” zegt de Here. “Ik zal een vuur aansteken in de bossen dat de hele omgeving zal verbranden.” ’