ኤርምያስ 15 – NASV & NAV

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 15:1-21

1እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ሙሴና ሳሙኤል እንኳ በፊቴ ቢቆሙ፣ ልቤ ለዚህ ሕዝብ አይራራምና ከፊቴ አስወጣቸው፤ ይሂዱ! 2እነርሱም፣ ‘ወዴት እንሂድ?’ ቢሉህ፣ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ ‘ለሞት የተመደበ ወደ ሞት፣

ለሰይፍ የተመደበ ወደ ሰይፍ፣

ለራብ የተመደበ ወደ ራብ፣

ለምርኮ የተመደበ ወደ ምርኮ ይሄዳል።’

3እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘አራት ዐይነት አጥፊዎችን እሰድድባቸዋለሁ፤ እነዚህም፣ ለመግደል ሰይፍ፣ ለመጐተት ውሾች፣ እንዲሁም ጠራርጎ ለመብላትና ለማጥፋት የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት ናቸው። 4የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ካደረገው በደል የተነሣ፣ ለምድር ነገሥታት ሁሉ መሰቀቂያ አደርጋቸዋለሁ።’

5“ኢየሩሳሌም ሆይ፤ የሚራራልሽ ማን ነው?

ማንስ ያለቅስልሻል?

ደኅንነትሽንስ ማን ጐራ ብሎ ይጠይቃል?

6እኔን ጥለሽኛል” ይላል እግዚአብሔር

“ወደ ኋላም እያፈገፈግሽ ነው፤

ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ አነሣለሁ፤ አጠፋሻለሁም፤

ከእንግዲህም አልራራልሽም።

7በአገሪቱ የከተማ ደጆች፣

በመንሽ እበትናቸዋለሁ፤

ከመንገዳቸው አልተመለሱምና፣

ሕዝቤን በሐዘን እመታለሁ፤

ጥፋትም አመጣባቸዋለሁ፤

8የመበለቶቻቸውን ቍጥር፣

ከባሕር አሸዋ ይልቅ አበዛለሁ፤

የጐበዛዝት እናቶች በሆኑትም ላይ፣

አጥፊውን በቀትር አመጣባቸዋለሁ።

ሽብርንና ድንጋጤን፣

በድንገት አወርድባቸዋለሁ።

9የሰባቶቹ እናት ትዝለፈለፋለች፤

ትንፋሿም ይጠፋል፤

ገና ቀን ሳለ ፀሓይዋ ትጠልቃለች፤

እርሷም ታፍራለች፤ ትዋረዳለችም፤

የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት፣

ለሰይፍ እዳርጋቸዋለሁ፤”

ይላል እግዚአብሔር

10ወይኔ እናቴ! ለምድር ሁሉ፣

የጭቅጭቅና የክርክር ሰው የሆንሁትን ምነው ወለድሽ!

ለማንም አላበደርሁም፤ ከማንም አልተበደርሁም፤

ነገር ግን ሰው ሁሉ ይረግመኛል።

11እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤

“በርግጥ ለበጎ ዐላማ እታደግሃለሁ፤

በመከራና በጭንቅ ጊዜም፣

ጠላቶችህ ደጅ እንዲጠኑህ በእውነት አደርጋለሁ።

12“ሰው ብረትን፣ ከሰሜን የመጣን ብረት፣

ነሐስንስ መስበር ይችላልን?

13በመላ አገርህ፣

ስላለው ኀጢአትህ ሁሉ፣

ሀብትና ንብረትህን፣

ያለ ዋጋ አሳልፌ ለምርኮ እሰጣለሁ።

14ቍጣዬ በላያችሁ፣

የሚነድድ እሳት ትጭራለችና፣

በማታውቀው አገር፣

ለጠላቶችህ15፥14 አንዳንድ የዕብራይስጥ ጽሑፎች፣ ሰብዓ ሊቃናትና ሱርሰት ጽሑፎች ጠላቶችህ እንዲወስዱህ አደርጋለሁ ይላሉ። ባሪያ አደርግሃለሁ።”

15እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ታውቃለህ፤

እንግዲህ አስበኝ፤ ጐብኘኝም፤

አሳዳጆቼን ተበቀልልኝ።

ታጋሽ እንደ መሆንህ አታጥፋኝ፤

ባንተ ምክንያት የሚደርስብኝን ነቀፋ ዐስብ።

16ቃልህ በተገኘ ጊዜ በላሁት፤

የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤

በስምህ ተጠርቻለሁና፣

ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነልኝ።

17ፈንጠዝያ ከሚያደርጉት ጋር አልተቀመጥሁም፤

ከእነርሱም ጋር አልፈነጨሁም፤

እጅህ በላዬ ስለ ነበር፣ በቍጣህ ስለ ሞላኸኝ፣

ለብቻዬ ተቀመጥሁ።

18ሕመሜ ለምን ጸናብኝ?

ቍስሌስ ለምን በረታብኝ? ለምንስ የማይፈወስ ሆነ?

እንደሚያታልል ወንዝ፣

እንደሚያሳስት ምንጭ ትሆንብኛለህን?

19ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ብትመለስ፣ መልሼ አቆምሃለሁ፤

ታገለግለኛለህም፤

የከበረውን ከማይረባው ለይተህ ብትናገር፣

አፍ ትሆነኛለህ፤

እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ እንጂ፣

አንተ ወደ እነርሱ አትመለስም፤

20ለዚህ ሕዝብ የናስ ቅጥር፣ የተመሸገ

የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፤

ልታደግህና፣ ላድንህም፣

እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፤

ቢዋጉህም እንኳ፣

ሊያሸንፉህ አይችሉም፤”

ይላል እግዚአብሔር

21“ከክፉዎች እጅ እቤዥሃለሁ፤

ከጨካኞችም ጭምደዳ እታደግሃለሁ።”

Ketab El Hayat

إرميا 15:1-21

1ثُمَّ قَالَ لِيَ الرَّبُّ: «وحَتَّى لَوْ مَثَلَ مُوسَى وَصَمُوئِيلُ أَمَامِي، مِنْ أَجْلِ الشَّعْبِ فَإِنَّ قَلْبِي لَنْ يَلْتَفِتَ إِلَى هَذَا الشَّعْبِ. اطْرَحْهُمْ مِنْ مَحْضَرِي فَيَخْرُجُوا. 2وَعِنْدَمَا يَسْأَلُونَكَ: إِلَى أَيْنَ نَذْهَبُ؟ أَجِبْهُمْ: هَذَا مَا يُعْلِنُهُ الرَّبُّ: مَنْ هُوَ لِلْوَبَأِ فَبِالْوَبَأِ يَمُوتُ، وَمَنْ هُوَ لِلسَّيْفِ فَبِالسَّيْفِ يُقْتَلُ، وَمَنْ هُوَ لِلْمَجَاعَةِ فَبِالْمَجَاعَةِ يَفْنَى، وَمَنْ هُوَ لِلسَّبْيِ فَإِلَى السَّبْيِ يَذْهَبُ. 3وَأَعْهَدُ بِهِمْ إِلَى أَرْبَعَةِ أَصْنَافٍ مِنَ الْخَرَابِ يَقُولُ الرَّبُّ: السَّيْفِ لِلذَّبْحِ، وَالْكِلابِ لِلتَّمْزِيقِ، وَطُيُورِ السَّمَاءِ وَوُحُوشِ الأَرْضِ لِلاِفْتِرَاسِ وَالإِهْلاكِ. 4وَأَجْعَلُهُمْ مَثَارَ رُعْبِ أُمَمِ الأَرْضِ نَتِيجَةً لِمَا ارْتَكَبَهُ مَنَسَّى بْنُ حَزَقِيَّا فِي أُورُشَلِيمُ. 5فَمَنْ يَعْطِفُ عَلَيْكِ يَا أُورُشَلِيمُ، وَمَنْ يَرْثِي لَكِ؟ مَنْ يَتَوَقَّفُ لِيَسْأَلَ عَنْ سَلامَتِكِ؟ 6قَدْ رَفَضْتِنِي» يَقُولُ الرَّبُّ، «وَوَاظَبْتِ عَلَى الارْتِدَادِ، لِذَلِكَ مَدَدْتُ يَدِي ضِدَّكِ وَدَمَّرْتُكِ، إِذْ سَئِمْتُ مِنْ كَثْرَةِ الصَّفْحِ عَنْكِ. 7وَأُذَرِّيهِمْ بِالْمِذْرَاةِ فِي أَبْوَابِ مُدُنِ الأَرْضِ؛ وَأُثْكِلُ وَأُهْلِكُ شَعْبِي لأَنَّهُمْ لَمْ يَرْجِعُوا عَنْ طُرُقِهِمِ الأَثِيمَةِ. 8وَأَجْعَلُ عَدَدَ أَرَامِلِهِمْ أَكْثَرَ مِنْ عَدَدِ رَمْلِ الْبَحْرِ، وَأَجْلِبُ فِي الظَّهِيرَةِ مُهْلِكاً عَلَى أُمَّهَاتِ الشُّبَّانِ، وَأُوْقِعُ عَلَيْهِمِ الرُّعْبَ وَالْهَوْلَ بَغْتَةً. 9ذَبُلَتْ وَالِدَةُ السَّبْعَةِ الأَبْنَاءِ. أَسْلَمَتْ رُوحَهَا وَغَرَبَتْ شَمْسُ حَيَاتِهَا وَالنَّهَارُ لَمْ يَغِبْ بَعْدُ. لَحِقَ بِها الْخِزْيُ وَالْعَارُ. أَمَّا بَقِيَّتُهُمْ فَأَدْفَعُهُمْ إِلَى حَدِّ السَّيْفِ أَمَامَ أَعْدَائِهِمْ»، يَقُولُ الرَّبُّ.

10وَيْلٌ لِي يَا أُمِّي لأَنَّكِ أَنْجَبْتِنِي لأَكُونَ إِنْسَانَ خِصَامٍ وَرَجُلَ نِزَاعٍ لِكُلِّ الأَرْضِ. لَمْ أَقْرِضْ وَلَمْ أَقْتَرِضْ. وَمَعَ ذَلِكَ كُلُّ وَاحِدٍ يَلْعَنُنِي. 11دَعْهُمْ يَشْتِمُونَ يَا رَبُّ. أَلَمْ أَتَضَرَّعْ إِلَيْكَ مِنْ أَجْلِ خَيْرِهِمْ؟ إِنِّي أَبْتَهِلُ إِلَيْكَ الآنَ مِنْ أَجْلِ أَعْدَائِي فِي وَقْتِ الضِّيقِ وَالْمِحْنَةِ.

12«أَيُمْكِنُ لِلْمَرْءِ أَنْ يَكْسِرَ حَدِيداً وَنُحَاساً مِنَ الشِّمَالِ؟ 13سَأَجْعَلُ ثَرْوَتَكَ وَكُنُوزَكَ نَهْباً بِلا ثَمَنٍ بِسَبَبِ كُلِّ خَطَايَاكَ فِي جَمِيعِ أَرْضِكَ. 14وَأُصَيِّرُكَ عَبْداً لأَعْدَائِكَ فِي أَرْضٍ لَا تَعْرِفُهَا، لأَنَّ نَاراً قَدِ اضْطَرَمَتْ فِي احْتِدَامِ غَضَبِي، سَوْفَ تُحْرِقُكُمْ».

15يَا رَبُّ، أَنْتَ عَرَفْتَ. اذْكُرْنِي وَارْعَنِي وَانْتَقِمْ لِي مِنْ مُضْطَهِدِيَّ. لَا تَتَمَهَّلْ طَوِيلاً فِي الانْتِقَامِ لِي، فَأَنْتَ تَعْلَمُ أَنِّي مِنْ أَجْلِكَ احْتَمَلْتُ التَّعْيِيرَ. 16حَالَمَا بَلَغَتْنِي كَلِمَاتُكَ أَكَلْتُهَا فَأَصْبَحَتْ لِي بَهْجَةً وَمَسَرَّةً لِقَلْبِي، لأَنِّي دُعِيتُ بِاسْمِكَ أَيُّهَا الرَّبُّ الإِلَهُ الْقَدِيرُ. 17لَمْ أَجْلِسْ فِي مَجَالِسِ الْعَابِثِينَ، وَلَمْ أَشْتَرِكْ فِي لَهْوِهِمْ. اعْتَزَلْتُ وَحْدِي لأَنَّ يَدَكَ كَانَتْ عَلَيَّ، وَقَدْ مَلأْتَنِي سُخْطاً. 18لِمَاذَا لَا يَنْقَطِعُ أَلَمِي، وَجُرْحِي لَا يُشْفَى، وَيَأْبَى الالْتِئَامَ؟ أَتَكُونُ لِي كَجَدْوَلٍ كَاذِبٍ أَوْ مِيَاهٍ سَرِيعَةِ النُّضُوبِ؟

19لِذَلِكَ، هَكَذَا قَالَ الرَّبُّ: «إِنْ رَجَعْتَ أَسْتَرِدَّكَ فَتَمْثُلَ أَمَامِي. إِنْ نَطَقْتَ بِالْقَوْلِ السَّدِيدِ وَنَبَذْتَ الْكَلامَ الْغَثَّ، أَجْعَلْكَ الْمُتَحَدِّثَ بِفَمِي، فَيُقْبِلُونَ إِلَيْكَ مُسْتَرْشِدِينَ، وَأَنْتَ لَا تَلْجَأُ إِلَيْهِمْ طَالِباً نَصِيحَةً. 20وَأَجْعَلُكَ سُوراً نُحَاسِيًّا مَنِيعاً لِهَذَا الشَّعْبِ، فَيُحَارِبُونَكَ وَلَكِنَّهُمْ يُخْفِقُونَ، لأَنِّي أَنَا مَعَكَ لأُنْقِذَكَ وَأُخَلِّصَكَ. 21أُنْقِذُكَ مِنْ قَبْضَةِ الأَشْرَارِ، وَأَفْدِيكَ مِنْ أَكُفِّ الْعُتَاةِ».