ኤርምያስ 13 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ኤርምያስ 13:1-27

ከተልባ እግር የተሠራ መቀነት

1እግዚአብሔር፣ “ሄደህ ከተልባ እግር የተሠራ መቀነት ግዛ፤ ወገብህንም ታጠቅበት፤ ነገር ግን ውሃ አታስነካው” አለኝ። 2ስለዚህ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ መቀነቱን ገዛሁ፤ ወገቤንም ታጠቅሁበት።

3ለሁለተኛም ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤ 4“ገዝተህ የታጠቅህበትን መቀነት ይዘህ ወደ ኤፍራጥስ13፥4 ወይም ፌሬጥ ሂድ፤ በዚያም በዐለት ንቃቃት ውስጥ ሸሽገው።” 5ስለዚህ እግዚአብሔር በነገረኝ መሠረት ወደ ኤፍራጥስ ሄጄ ሸሸግሁት።

6ከብዙ ቀን በኋላም እግዚአብሔር፣ “ተነሥተህ ወደ ኤፍራጥስ ሂድ፤ በዚያ እንድትሸሽገው የነገርሁህን መቀነት አምጣ” አለኝ። 7እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄጄ፣ መታጠቂያውን ከሸሸግሁበት ቦታ ቈፍሬ አወጣሁ፤ መታጠቂያውም ተበላሽቶ፣ ከጥቅም ውጭም ሆኖ ነበር።

8የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤ 9እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የይሁዳን ትዕቢትና የኢየሩሳሌምን እብሪት እንደዚሁ አጠፋለሁ። 10ቃሌን መስማት እንቢ ብለው በልባቸው እልኸኝነት በመሄድ ሊያመልኳቸውና ሊሰግዱላቸው ሌሎችን ጣዖቶች የሚከተሉ እነዚህ ክፉ ሕዝቦች ከጥቅም ውጭ እንደ ሆነው እንደዚህ መቀነት ይበላሻሉ። 11መቀነት በሰው ወገብ ላይ እንደሚታሰር፣ መላው የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ከእኔ ጋር ተጣብቆ ለስሜ ምስጋናና ክብር፣ የእኔ ሕዝብ እንዲሆንልኝ አድርጌው ነበር፤ ሕዝቤ ግን አልሰማም’ ይላል እግዚአብሔር

የወይን ጠጅ ማድጋ

12“እንዲህ በላቸው፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ማድጋ ሁሉ በወይን ጠጅ ይሞላል’፤ እነርሱም፣ ‘ማድጋ ሁሉ በወይን ጠጅ እንደሚሞላ እኛ አናውቅምን?’ ቢሉህ፣ 13እንዲህ በላቸው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታትን፣ ካህናትን፣ ነቢያትን እንዲሁም በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ሁሉ ጨምሮ በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ በስካር እሞላቸዋለሁ። 14አንዱን ሰው ከሌላው ጋር፣ አባትንና ወንድ ልጅን እርስ በእርስ አጋጫለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር፤ ያለ ሐዘኔታ፣ ያለ ምሕረትና ያለ ርኅራኄ አጠፋቸዋለሁ።’ ”

የትዕቢት ውጤት

15እግዚአብሔር ተናግሯልና፣

ስሙ፤ ልብ በሉ፤

ትዕቢተኛም አትሁኑ።

16ጨለማን ሳያመጣ፣

በሚጨልሙትም ተራሮች ላይ፣

እግሮቻችሁ ሳይሰናከሉ፣

ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ።

ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ፤

እርሱ ወደ ጨለማ ይለውጠዋል፤

ድቅድቅ ጨለማም ያደርገዋል።

17ባትሰሙ ግን፣

ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ፣

በስውር ታለቅሳለች፤

የእግዚአብሔር መንጋ ተማርኳልና፣

ዐይኔ አምርሮ ያለቅሳል፤

እንባዬም እንደ ጐርፍ ይወርዳል።

18ለንጉሡና ለእናቱ ለእቴጌዪቱ፣

“የክብር ዘውዳችሁ ከራሳችሁ ይወድቃልና፣

ከዙፋናችሁ ውረዱ” በላቸው።

19በኔጌቭ ያሉ ከተሞች ይዘጋሉ፤

የሚከፍታቸውም አይኖርም።

ይሁዳ ሁሉ ተማርኮ ይሄዳል፤

ሙሉ በሙሉም ይዘጋል።

20ዐይኖቻችሁን ከፍታችሁ፣

ከሰሜን የሚመጡትን እዩ።

ለአንቺ የተሰጠው መንጋ፣

የተመካሽባቸው በጎች የት አሉ?

21ልዩ ወዳጆች እንዲሆኑሽ ያስተማርሻቸው፣

ባለ ሥልጣን ሲሆኑብሽ ምን ትያለሽ?

እንደምትወልድ ሴት፣

ምጥ አይዝሽምን?

22“ይህ ለምን ደረሰብኝ?” ብለሽ

ራስሽን ብትጠይቂ፣

ልብስሽን ተገልበሽ የተገፈተርሽው፣

በሰውም እጅ የተንገላታሽው፣

ከኀጢአትሽ ብዛት የተነሣ ነው።

23ኢትዮጵያዊ13፥23 ዕብራይስጡ ኩሻዊ ይላል (ምናልባት በላይኛው አባይ አካባቢ የሚኖር ሰው ሊሆን ይችላል)። መልኩን፣

ነብርስ ዝንጕርጕርነቱን መለወጥ ይችላልን?

እናንት ክፉ ማድረግ የለመዳችሁትም፣

መልካም ማድረግ አትችሉም።

24“የበረሓ ነፋስ ብትንትኑን እንደሚያወጣው ገለባ፣

እንዲሁ እበታትናችኋለሁ።

25እኔን ረስተሽ፣

በከንቱ አማልክት ስለ ታመንሽ፣

ያወጅሁልሽ ድርሻሽ፣

ዕጣ ፈንታሽ ይህ ነው፤”

ይላል እግዚአብሔር

26“ኀፍረትሽ እንዲገለጥ፣

ልብስሽን ፊትሽ ድረስ እገልባለሁ፤

27በኰረብቶችና በሜዳዎች ላይ፣

አስጸያፊ ተግባርሽን፣

ምንዝርናሽንና ማሽካካትሽን፣

ኀፍረተ ቢስ ግልሙትናሽን አይቻለሁ።

ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ወዮልሽ፤

ከርኩሰትሽ የማትጸጂው እስከ መቼ ነው?”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

耶利米书 13:1-27

腰带的比喻

1耶和华对我说:“你去买一条麻布腰带束在腰间,不可让它沾水。” 2我照耶和华的话买了腰带,束在腰间。 3耶和华又对我说: 4“拿着你买来的腰带去幼发拉底河边,把它藏在那里的石缝中。” 5于是,我照耶和华的吩咐把腰带藏在那里。 6多日后,耶和华对我说:“去幼发拉底河边取回我吩咐你藏的腰带。” 7我就去幼发拉底河边把所藏的腰带挖出来,但腰带已经腐烂,不能用了。

8耶和华对我说: 9“这是耶和华说的,‘我也要这样消灭犹大的骄傲和耶路撒冷的狂妄。 10这邪恶的百姓拒绝听我的话,一意孤行,跟随、供奉、祭拜别的神明,他们将像这腰带一样毫无用处。 11我本想使以色列人和犹大人紧靠着我,就像腰带紧贴在人的腰间,让他们做我的子民,使我声名远扬、得到赞美和尊崇,他们却不肯听从。这是耶和华说的。’

12“因此,你告诉他们,以色列的上帝耶和华说,‘每个瓶子都要盛满酒。’若他们说,‘难道我们不知道每个瓶子都要盛满酒吗?’ 13你就告诉他们,‘耶和华说,我要使坐在大卫宝座上的君王以及祭司、先知、耶路撒冷人和这片土地上所有的居民都酩酊大醉; 14我要使他们彼此撞得粉碎,就算父子也要彼此相撞;我要毁灭他们,决不心慈手软。’”

15耶和华说话了,你们要留心听,

不可傲慢。

16趁着你们的上帝耶和华还未使黑暗来临,

你们还未在漆黑的山上绊倒,

要把荣耀归给祂。

否则,祂必使你们期望的光明变为幽冥和黑暗。

17如果你们因为骄傲而不肯听,

我会暗自哭泣、泪流满面,

因为耶和华的子民将要被掳。

18耶和华让我对君王和太后说:

“从宝座上下来吧,

因为你们头上华美的王冠将要掉落。”

19南部的城邑将被围困,

无人能解围,

犹大人都要被掳,无一幸免。

20耶路撒冷啊,

举目看看那些从北方来的敌人吧,

从前赐给你的佳美羊群——你的百姓如今在哪里呢?

21耶和华让你结交的盟友来统治你,

你还有什么话可说?

难怪你痛苦不堪,

就像分娩的妇人。

22也许你在想:“为什么这些事发生在我身上?”

你的裙子被撕破,你遭受蹂躏,

是因为你罪大恶极。

23古实人能改变他们的肤色吗?

豹子能脱去它们的斑点吗?

你这作恶成性的人怎能行善呢?

24因此,耶和华说:

“我要把你分散到四方,

像旷野的风吹散碎秸一样。

25这是你应得的报应,

是我量给你的,

因为你把我抛诸脑后,

信靠假神。

这是耶和华说的。

26因此,我要把你的裙子掀到你的脸上,

使人见到你的羞耻。

27你在山上和田野间拜偶像,

像无耻的妇人与情郎苟合,

发出淫语浪声。

这些可憎之事,我都看见了。

耶路撒冷啊,你有祸了!

你什么时候才肯自洁呢?”