ኢያሱ 5 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ኢያሱ 5:1-15

በጌልገላ የተደረገ ግዝረት

1በዚህ ጊዜ ከዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል ያሉት የአሞራውያን ነገሥታት ሁሉ፣ በባሕሩም ዳርቻ ያሉ የከነዓናውያን ነገሥታት በሙሉ እግዚአብሔር ዮርዳኖስን እስክንሻገር ወንዙን በእስራኤላውያን ፊት እንዴት እንዳደረቀው በሰሙ ጊዜ፣ ልባቸው በፍርሀት ቀለጠ፤ እስራኤላውያንንም ለመቋቋም ድፍረት ዐጡ።

2በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን፣ “የባልጩት መቍረጫ አዘጋጅተህ፣ ያልተገረዙትን እስራኤላውያንን ለሁለተኛ ጊዜ ግረዛቸው” አለው። 3ስለዚህ ኢያሱ የባልጩት መቍረጫ አዘጋጅቶ በጊብዓዝ ዓረሎት5፥3 ትርጓሜውም የሸለፈት ኰረብታ ማለት ነው። በተባለ ስፍራ እስራኤላውያንን ገረዛቸው።

4እንግዲህ ኢያሱ እስራኤላውያንን የገረዘበት ምክንያት ይህ ነው፤ ዕድሜያቸው መሣሪያ ለመያዝ የደረሱ ወንዶች ሁሉ ከግብፅ ከወጡ በኋላ በመንገድ ላይ ሳሉ በምድረ በዳ ሞቱ። 5ከዚያ የወጡት ሰዎች ሁሉ ተገርዘው ነበር፤ ከግብፅ ከወጡ በኋላ በምድረ በዳ በጕዞ ላይ ሳሉ የተወለዱት ግን በሙሉ አልተገረዙም ነበር። 6ግብፅን ለቀው በወጡ ጊዜ መሣሪያ ለመያዝ የደረሱ ወንዶች ሁሉ ለእግዚአብሔር ስላልታዘዙ፣ እነርሱ ሞተው እስኪያልቁ ድረስ፣ እስራኤላውያን በምድረ በዳ አርባ ዓመት ይንከራተቱ ነበር። እግዚአብሔር ለእኛ ይሰጠን ዘንድ ለአባቶቻቸው ቃል የገባላቸውን ያችን ማርና ወተት የምታፈስስ ምድር እንደማያዩአት ምሏልና። 7ስለዚህ በእነርሱ ምትክ ወንዶች ልጆቻቸውን አስነሣ። እንግዲህ ኢያሱ የገረዛቸው እነዚህን ነበር፤ በጕዞ ላይ ሳሉ ባለመገረዛቸው ከነሸለፈታቸው ነበሩና። 8ሕዝቡ ሁሉ ከተገረዙ በኋላ ቍስሉ እስኪሽር ድረስ እዚያው በሰፈሩበት ቦታ ቈዩ።

9ከዚያም እግዚአብሔር ኢያሱን፣ “እነሆ፤ ዛሬ የግብፅን ነውር ከእናንተ ላይ አንከባልያለሁ” አለው፤ ከዚህም የተነሣ የዚያ ቦታ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ5፥9 በዕብራይስጡ ጌልገላ የሚለው ቃል ድምፅ መንከባለል ከሚለው ቃል ጋር አንድ ዐይነት ነው። ተባለ።

10እስራኤላውያን በኢያሪኮ ሜዳ በጌልገላ ሰፍረው ሳሉ፣ ወሩ በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት የፋሲካን በዓል አከበሩ። 11ከፋሲካም በኋላ በዚያኑ ዕለት የምድሪቱን ፍሬ ማለት ያልቦካ ቂጣና የተጠበሰ እሸት በሉ። 12የምድሪቱን ፍሬ በበሉበት ቀን5፥12 ወይም በበሉበት ጊዜ ተብሎ መተርጐም ይችላል። መናው መውረዱ ቀረ፤ ከዚያ በኋላ ለእስራኤላውያን መና አልወረደላቸውም፤ ነገር ግን በዚያኑ ዓመት የከነዓንን ምድር ፍሬ በሉ።

የኢያሪኮ መውደቅ

13ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ፣ ቀና ብሎ ሲመለከት የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ አንድ ሰው ከፊቱ ቆሞ አየ። ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፤ “ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው።

14እርሱም፣ “አይደለሁም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ በመሆኔ እነሆ፤ መጥቻለሁ” ሲል መለሰለት፤ ኢያሱም በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደና፣ “ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድን ነው?” አለው።

15የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃም ኢያሱን፣ “ጫማህን ከእግርህ አውልቅ፤ የቆምህባት ምድር የተቀደሰች ናትና” አለው፤ ኢያሱም እንደ ታዘዘው አደረገ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

約書亞記 5:1-15

在吉甲行割禮

1約旦河西岸一帶的亞摩利眾王和沿海一帶的迦南眾王,聽說耶和華為了讓以色列人過河而使約旦河成為乾地,都嚇得膽戰心驚,勇氣盡失。

2那時,耶和華對約書亞說:「你用火石做成刀子,再次給以色列人行割禮。」 3約書亞便用火石做成刀子,在割禮山給以色列人行了割禮。 4約書亞給他們舉行割禮,是因為所有從埃及出來、能夠作戰的男子都死在曠野的路上。 5埃及出來的男子都受過割禮,而後來在曠野出生的以色列人都沒有受過割禮。 6以色列人在曠野飄泊了四十年,直到從埃及出來可以作戰的男子都死了為止,因為他們不聽從耶和華的話。耶和華向他們起誓,不讓他們看見那奶蜜之鄉,衪曾應許他們祖先要把那個地方賜給他們。 7耶和華立他們的子孫代替他們。這新一代的以色列人沒有受過割禮,因為在路上沒有為他們行過割禮。於是,約書亞為他們行了割禮。

8全體民眾受了割禮後,都留在自己的營內,直到康復為止。 9耶和華對約書亞說:「今天我除去了你們在埃及受的羞辱。」因此,那地方叫吉甲5·9 吉甲」意思是「除去」。,沿用至今。

在迦南守逾越節

10以色列人都在耶利哥平原上的吉甲紮營,並於一月十四日傍晚在那裡守逾越節。 11第二天他們就吃當地的穀物,吃無酵餅和烤麥穗。 12他們吃了當地出產後的第二天,嗎哪便不再降下,以色列人再沒有嗎哪吃了。那一年他們開始吃迦南的出產。

耶和華軍隊的元帥

13約書亞走近耶利哥,舉目看見一個人手裡拿著拔出來的劍站在他面前。約書亞上前去問道:「你是來幫助我們的,還是來幫助我們敵人的?」 14那人答道:「都不是,我來是做耶和華軍隊的統帥。」約書亞就俯伏下拜說:「我主,有什麼話要吩咐僕人?」 15耶和華軍隊的統帥對約書亞說:「把你腳上的鞋脫下!因為你站的地方是聖潔的。」約書亞便把鞋脫下來。