ኢያሱ 3 – NASV & NUB

New Amharic Standard Version

ኢያሱ 3:1-17

እስራኤላውያን ዮርዳኖስን ተሻገሩ

1ኢያሱም ማልዶ ተነሣ። ከእስራኤላውያንም ሁሉ ጋር ከሰጢም ወደ ዮርዳኖስ መጥተው ወንዙን ከመሻገራቸው በፊት በዚያ ሰፈሩ። 2ከሦስት ቀን በኋላም የጦሩ አለቆች በሰፈር ውስጥ ዐለፉ፤ 3ሕዝቡንም እንዲህ ሲሉ አዘዙ፤ “ሌዋውያን ካህናቱ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ተሸክመው ስታዩ፣ ከሰፈራችሁ ተነሥታችሁ ታቦቱን ተከተሉ፤ 4ከአሁን በፊት በዚህ መንገድ ሄዳችሁ ስለማታውቁ፤ በየት በኩል መሄድ እንዳለባችሁ በዚህ ትረዳላችሁ፤ ሆኖም በታቦቱና በእናንተ መካከል የሁለት ሺሕ ክንድ3፥4 የዕብራይስጡ ትርጕም 900 ሜትር ይላል። ያህል ርቀት ይኑር፤ ወደ ታቦቱም አትቅረቡ።”

5ከዚያም ኢያሱ ሕዝቡን፣ “በነገው ዕለት እግዚአብሔር በመካከላችሁ አስደናቂ ነገር ስለሚያደርግ ራሳችሁን ቀድሱ” አላቸው።

6ኢያሱም ካህናቱን፣ “የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክማችሁ ሕዝቡን ቀድማችሁ ሂዱ” አላቸው፤ እነርሱም ታቦቱን ተሸክመው ሕዝቡን ቀድመው ሄዱ።

7እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ ሁሉ፣ ከአንተም ጋር መሆኔን ያውቁ ዘንድ፣ በእስራኤል ሁሉ ፊት አንተን ከፍ ከፍ ማድረጌን በዛሬዋ ዕለት እጀምራለሁ። 8የቃል ኪዳኑን ታቦት የሚሸከሙትንም ካህናት፣ ‘ከዮርዳኖስ ውሃ ዳር ስትደርሱ፣ በወንዙ ውስጥ ገብታችሁ ቁሙ’ በላቸው።”

9ኢያሱ የእስራኤልን ሕዝብ “ወደዚህ ቀርባችሁ፣ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ አላቸው፤ 10እንግዲህ ሕያው አምላክ በመካከላችሁ መሆኑንና እርሱም በርግጥ ከነዓናውያንን፣ ኬጢያውያንን፣ ኤዊያውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ጌርጌሳውያንን፣ አሞራውያንንና ኢያቡሳውያንን ከፊታችሁ እንዴት አድርጎ እንደሚያሳድዳቸው የምታውቁት በዚህ ነው። 11እነሆ፤ የምድር ሁሉ ጌታ የቃል ኪዳኑ ታቦት ቀድሟችሁ ወደ ዮርዳኖስ ይገባል። 12እንግዲህ ከእስራኤል ነገዶች ዐሥራ ሁለት ሰው ምረጡ፤ ከየነገዱም አንዳንድ ሰው ይሁን። 13የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙት ካህናት ገና እግራቸውን በዮርዳኖስ ውሃ ውስጥ እንዳስገቡ፣ ቍልቍል የሚወርደው ውሃ ወዲያውኑ ይቋረጣል፤ እንደ ክምርም ሆኖ ይቆማል።”

14ስለዚህ ሕዝቡ ዮርዳኖስን ለመሻገር ሰፈሩን ለቀው ሲወጡ፣ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ካህናት ከፊታቸው ቀድመው ሄዱ። 15ወቅቱም የመከር ጊዜ በመሆኑ፣ የዮርዳኖስ ወንዝ ሞልቶ ነበር፤ ታቦቱን የተሸከሙት ካህናት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በደረሱ ጊዜ እግራቸው ውሃውን እንደ ነካ፣ 16ከላይ የሚወርደው ውሃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ “አዳም” ተብላ እስከምትጠራው ሩቅ ከተማ ድረስ በመከማቸት እንደ ክምር ተቈለለ፤ ቍልቍል ወደ ዓረባ ጨው ባሕር3፥16 የሙት ባሕር ነው። የሚወርደውም ውሃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም ከኢያሪኮ ትይዩ ባለው አቅጣጫ ተሻገሩ። 17የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ካህናትም፣ ሕዝቡ ሁሉ፣ ማለት እስራኤል በሙሉ ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል በደረቁ ምድር ላይ ቀጥ ብለው ቆመው ነበር።

Swedish Contemporary Bible

Josua 3:1-17

Israel går över Jordan

1Tidigt följande morgon lämnade Josua och hela Israels folk Shittim och gick till Jordans strand där de slog läger innan de skulle gå över floden.

2På tredje dagen gick förmännen genom lägret 3och gav följande order: ”När ni ser de levitiska prästerna bära iväg Herrens, er Guds, förbundsark,3:3 Förbundsarken var en guldöverdragen kista där man förvarade stentavlorna med förbundsavtalet, de tio budorden. Se 2 Mos 25:10-22. ska ni bryta upp och följa dem. 4Håll er en kilometer bakom arken och se till att ni inte kommer närmare! Ni har aldrig gått den här vägen tidigare, men om ni följer arken, så vet ni vart ni ska gå.”

5Sedan sa Josua till folket: ”Rena er3:5 Jfr 2 Mos 19:10,14-15., för imorgon ska Herren göra under bland er!”

6Sedan gav Josua prästerna ordern: ”Ta arken och gå före folket!” Då lyfte de upp arken och började gå framför dem.

7”Idag ska jag börja upphöja dig”, sa Herren till Josua. ”Hela Israel ska förstå att jag är med dig precis som jag var med Mose. 8Säg till prästerna som bär arken att de ska stanna i vattenbrynet när de kommer till Jordan.”

9Sedan talade Josua till israeliterna: ”Kom och hör vad Herren, er Gud, har sagt! 10Av detta ska ni förstå att den levande Guden är mitt ibland er och att han verkligen kommer att driva undan kanaanéerna, hettiterna, hivéerna, perisséerna, girgashéerna, amoréerna och jevuséerna för er. 11Herren, hela jordens härskare, ska låta sin förbundsark leda er över floden.

12Välj nu ut tolv män, en från varje stam. 13När prästerna som bär Herrens, hela jordens härskares, ark nuddar vid vattnet med sina fötter, ska vattnet i floden sluta att rinna. Det ska stanna upp och stå som en mur.”

14Folket bröt upp från sitt läger för att gå över Jordanfloden och följde prästerna som bar förbundsarken. 15Det var skördetid och floden svämmade över sina bräddar som alltid. Men just när prästerna som bar arken skulle stiga ner i Jordan, 16stannade vattnet upp och reste sig som en mur långt borta vid Adam, en stad som låg nära Saretan. Nedströms däremot mot Aravasjön, Döda havet, rann allt vattnet undan. Folket gick då över floden mitt emot Jeriko 17och prästerna som bar Herrens förbundsark stod på torr mark mitt i Jordan och väntade tills allt folket hade kommit över.