ኢያሱ 10 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ኢያሱ 10:1-43

ፀሓይ ቆመች

1የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፣ ኢያሱ ጋይን ይዞ እንደ ደመሰሳት10፥1 የዕብራይስጡ ቃል በዚህም ሆነ በቍጥር 28፡35፡37፡39 እና 40 ላይ ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ለእግዚአብሔር መስጠት ማለት ነው።፣ እንደዚሁም በኢያሪኮና በንጉሥዋ ላይ ያደረገውን ሁሉ፣ በጋይና በንጉሥዋ ላይ ማድረጉን፣ የገባዖን ሰዎችም ከእስራኤል ጋር የሰላም ውል አድርገው በአጠገባቸው መኖራቸውን ሰማ። 2በዚህም እርሱና ሕዝቡ ደነገጡ፤ ምክንያቱም ገባዖን እንደ ነገሥታቱ ከተማ ሁሉ ታላቅ ከተማ፣ በስፋቷም ከጋይ የምትበልጥ፣ ሰዎቿም ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ። 3ስለዚህ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፣ ሆሃም ወደ ተባለው የኬብሮን ንጉሥ ጲርአም ወደተባለው የየርሙት ንጉሥ፣ ያፊዓ ወደ ተባለው የለኪሶ ንጉሥና ዳቤር ወደተባለው የዔግሎን ንጉሥ በመላክ፣ 4“ወደዚህ ወጥታችሁ አግዙኝ፤ ከኢያሱና ከእስራኤላውያን ጋር ሰላምን መሥርታለችና ገባዖንን እንምታ” አላቸው።

5ከዚያም አምስቱ የአሞራውያን ነገሥታት ማለት የኢየሩሳሌም ንጉሥ፣ የኬብሮን ንጉሥ፣ የያርሙት ንጉሥ፣ የለኪሶ ንጉሥና የዔግሎን ንጉሥ ያላቸውን አስተባብረው፣ ሰራዊታቸውንም ሁሉ ይዘው በመውጣት ገባዖንን ወጓት።

6የገባዖንም ሰዎች በጌልገላ ወደ ሰፈረው ወደ ኢያሱ፣ “በተራራማው አገር የሚኖሩ የአሞራውያን ነገሥታት ኀይላቸውን አስተባብረው ተሰልፈውብናል፤ እኛን ባሮችህን አትተወን፤ ርዳን፤ ፈጥነህ በመድረስም አድነን” ሲሉ ላኩበት።

7ስለዚህ ኢያሱ ምርጥ የሆኑትን ተዋጊዎች ሁሉ ጨምሮ ሰራዊቱን በሙሉ ይዞ ከጌልገላ ወጣ። 8እግዚአብሔርም ኢያሱን፣ “አትፍራቸው፤ ሁሉንም አሳልፌ በእጅህ ሰጥቻቸዋለሁ፤ አንዳቸውም እንኳ ሊቋቋሙህ አይችሉም” አለው።

9ኢያሱ ከጌልገላ ሌሊቱን ሁሉ ሲገሠግሥ ዐድሮ ድንገት ወረራቸው። 10እግዚአብሔርም የአሞራውያንን ነገሥታት በእስራኤል ፊት አሸበራቸው፤ በገባዖን እጅግ መታቸው፤ ወደ ቤትሖሮን በሚያስወጣውም መንገድ ሽቅብ ተከተላቸው፤ እስከ ዓዜቅና እስከ መቄዳም ድረስ አሳድዶ መታቸው። 11ከቤትሖሮን ወደ ዓዜቃ ቍልቍል በሚወስደው መንገድ ላይ፣ ከእስራኤላውያን ፊት በሚሸሹበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሰማይ ትልልቅ የበረዶ ድንጋይ አወረደባቸው፤ በእስራኤላውያን ሰይፍ ካለቁት ይልቅ በወረደው የበረዶ ድንጋይ ያለቁት በልጠው ተገኙ።

12እግዚአብሔር አሞራውያንን ለእስራኤል አሳልፎ በሰጠባት ዕለት፣ ኢያሱ እግዚአብሔርን በእስራኤል ፊት እንዲህ አለው፤

“ፀሓይ ሆይ፤ በገባዖን ላይ ቁሚ፤

ጨረቃም ሆይ፤ በኤሎን ሸለቆ ላይ ቀጥ በዪ።”

13ስለዚህ ሕዝቡ ጠላቶቹን እስኪበቀል

ድረስ10፥13 ወይም ሕዝቡ እስኪያሸንፍ ድረስ፣ ፀሓይ ባለችበት ቆመች፤

ጨረቃም አልተንቀሳቀሰችም።

ይህም በያሻር መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል።

ፀሓይ በሰማዩ መካከል ቆመች፤ ለመጥለቅም ሙሉ ቀን ፈጀባት። 14እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ዕለት ከዚያ በፊትም ሆነ ከዚያ በኋላ አልነበረም፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ተዋግቶ ነበርና።

15ከዚያም ኢያሱ ከመላው እስራኤል ጋር ጌልገላ ወዳለው ሰፈር ተመለሰ።

አምስቱ የአሞራውያን ነገሥታት ተገደሉ

16በዚህ ጊዜ አምስቱ የአሞራውያን ነገሥታት ሸሽተው በመቄዳ ዋሻ ተደብቀው ነበር። 17ኢያሱም አምስቱ ነገሥታት በመቄዳ ዋሻ ውስጥ ተደብቀው መገኘታቸውን ሰማ፤ 18እንዲህም አለ፤ “ትልልቅ ድንጋዮች ወደ ዋሻው አፍ አንከባሉ፤ ጠባቂ ሰዎችንም በዚያ አቁሙ፤ 19ጠላቶቻችሁን አሳድዷቸው እንጂ ችላ አትበሉ፤ ከበስተ ኋላ ሆናችሁም አደጋ ጣሉባቸው፤ ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ ከልክሏቸው፤ እነሆ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቷቸዋልና።”

20ስለዚህ ኢያሱና እስራኤላውያን እስከ መጨረሻው ደመሰሷቸው፤ የተረፉት ጥቂቶቹ ግን ወደ ተመሸጉት ከተሞቻቸው ለመድረስ ቻሉ። 21ከዚያም ሰራዊቱ ሁሉ በደኅና ተመልሶ፣ ኢያሱ ወደ ሰፈረበት ወደ መቄዳ መጣ፤ በእስራኤላውያንም ላይ አንዲት ቃል የተናገረ ሰው አልነበረም።

22ኢያሱም፤ “ዋሻውን ከፍታችሁ እነዚያን አምስቱን ነገሥታት አውጥታችሁ አምጡልኝ” አላቸው። 23እነርሱም አምስቱን ነገሥታት ማለትም የኢየሩሳሌምን ንጉሥ፣ የኬብሮንን ንጉሥ፣ የያርሙትን ንጉሥ፣ የለኪሶን ንጉሥ የዔግሎንን ንጉሥ አውጥተው አመጡለት። 24እነዚህን ነገሥታት ባመጡለትም ጊዜ፣ ኢያሱ መላውን የእስራኤልን ወንዶች ከጠራ በኋላ አብረውት የመጡትን የጦር አዛዦች፣ “ወደዚህ ቅረቡና እግሮቻችሁን በእነዚህ ነገሥታት ዐንገት ላይ አድርጉ” አላቸው፤ እነርሱም ወደ ፊት ቀርበው እግራቸውን በነገሥታቱ ዐንገት ላይ አሳረፉ።

25ኢያሱም፣ “አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ በርቱ፤ ጽኑ፤ እንግዲህ በምትወጓቸው ጠላቶች ሁሉ ላይ እግዚአብሔር እንደዚሁ ያደርጋልና” አላቸው። 26ከዚያም ኢያሱ ነገሥታቱን መትቶ ገደላቸው፤ በአምስትም ዛፎች ላይ ሰቀላቸው፤ ሬሳቸውም እስኪመሽ ድረስ አልወረደም ነበር።

27ፀሓይ ለመጥለቅ በማዘቅዘቅ ላይ ሳለች ኢያሱ ትእዛዝ ሰጠ፤ ከዚያም የነገሥታቱን ሬሳ ከዛፎቹ ላይ አውርደው ቀድሞ ተደብቀው ወደ ነበሩበት ዋሻ ውስጥ ጣሏቸው። በዋሻውም አፍ ትልልቅ ድንጋዮች አኖሩ፤ ድንጋዮቹም እስከ ዛሬ ድረስ በዚያ ይገኛሉ።

28በዚያች ዕለት ኢያሱ መቄዳን ያዘ፤ ከተማዪቱንና ንጉሥዋንም በሰይፍ ስለት መታ፤ አንድም ሰው ሳያስቀር በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽሞ ደመሰሰ፤ በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም ሁሉ፣ በመቄዳ ንጉሥ ላይ አደረገ።

የደቡብ ከተሞች መያዝ

29ከዚያም ኢያሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከመቄዳ ወደ ልብና ዐለፉ፤ ወጓትም። 30እንዲሁም እግዚአብሔር ከተማዪቱንና ንጉሥዋን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። ኢያሱ ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ በሰይፍ ስለት አጠፋ፤ አንድም ሰው አላስተረፈም። በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም በልብና ንጉሥ ላይ ደገመው።

31ከዚያም ኢያሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከልብና ወደ ለኪሶ ዐለፉ፤ ወጓትም። 32እግዚአብሔር ለኪሶን አሳልፎ ለእስራኤል ሰጠ፤ ኢያሱም በሁለተኛው ቀን ያዛት፤ በልብና እንዳደረገው ሁሉ እዚህም ከተማዪቱንና በውስጧ ያሉትን ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጃቸው። 33በዚህ ጊዜ የጌዝር ንጉሥ ሆራም ለኪሶን ለመርዳት መጣ፤ ኢያሱ ግን አንድ እንኳ ሳያስተርፍ ንጉሡንና ሕዝቡን መታቸው።

34ከዚያም ኢያሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከለኪሶ ወደ ዔግሎን ዐለፉ፤ ወጓትም። 35በዚያኑ ዕለት ያዟት፤ በሰይፍም ስለት አጠፏት፤ በለኪሶ እንዳደረጉት ሁሉ እዚህም በውስጧ የሚገኙትን ፈጽመው ደመሰሷቸው።

36ከዚያም ኢያሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከዔግሎን ወደ ኬብሮን ወጡ፤ ወጓትም። 37ከተማዪቱንም ከንጉሧ፣ ከመንደሮቿና በውስጧ ካሉት ጋር ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት ፈጇቸው፤ በዔግሎን እንዳደረጉት ሁሉ እዚህም ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽመው ደመሰሱ።

38ከዚያም ኢያሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ወደ ኋላ ተመልሰው ዳቤርን ወጓት። 39ከተማዪቱን፣ ንጉሥዋንና መንደሮቿን ይዘው በሰይፍ ስለት ፈጇቸው፤ በውስጧ ያለውንም ሁሉ አንድም ሳያስቀሩ ደመሰሱ፤ በልብናና በንጉሥዋ እንዲሁም በኬብሮን ያደረጉትን ሁሉ እዚህም በዳቤርና በንጉሥዋ ላይ ደገሙት።

40በዚህ ሁኔታም ኢያሱ ተራራማውን አገር ኔጌቭን፣ የምዕራቡን ቈላና የተራራውን ሸንተረሮች ጨምሮ ምድሪቱን በሙሉ ከነገሥታቷ ጋር ያዘ። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት፣ እስትንፋስ ያላቸውን ሁሉ ፈጽሞ ደመሰሰ፤ ማንንም በሕይወት አላስቀረም። 41ኢያሱም ከቃዴስ በርኔ እስከ ጋዛ እንዲሁም የጎሶምን ምድር ሁሉ እስከ ገባዖን ድረስ በሙሉ ያዘ። 42ኢያሱ እነዚህን ሁሉ ነገሥታትና ምድራቸውን ያሸነፈው በአንድ ዘመቻ ብቻ ነበር፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ተዋግቶላቸዋልና።

43ከዚህ በኋላ ኢያሱ ከመላው እስራኤላውያን ጋር ጌልገላ ወዳለው ሰፈር ተመለሰ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

約書亞記 10:1-43

太陽停止

1耶路撒冷亞多尼·洗德聽說約書亞奪取並毀滅了城,像對付耶利哥耶利哥王一樣對付城和城的王,又聽說基遍人已經跟以色列人立了盟約,住在他們中間, 2便大為恐懼。因為基遍是一座大城,宏偉得像座都城,比城更大,城中的人都驍勇善戰。 3耶路撒冷亞多尼·洗德便派遣使者去見希伯崙何咸耶末毗蘭拉吉雅非亞伊磯倫底璧,說: 4「求你們上來幫助我攻打基遍,因為這城已經與約書亞以色列人立了和約。」 5這五位亞摩利王便聯合起來,率領他們所有的軍隊在基遍附近紮營,攻打基遍

6基遍人派人去吉甲告訴約書亞說:「住在山區的亞摩利眾王正聯合起來攻打我們,求你趕快來救我們!不要不顧你的僕人。」 7於是,約書亞便率領他的全軍,包括所有的精兵,從吉甲上去。 8耶和華對約書亞說:「不要害怕,我已經把他們交在你手中,他們沒有一人能抵擋你。」 9約書亞吉甲出發,連夜趕路,突襲敵人。 10耶和華使亞摩利聯軍陣腳大亂,以色列人就在基遍大敗敵軍,在去伯·和崙的上坡路上追殺他們,一直追到亞西加瑪基大11敵人在從伯·和崙亞西加的下坡路上逃竄的時候,耶和華降下大冰雹,被冰雹砸死的人比以色列人用刀殺死的還要多。

12耶和華將亞摩利人交在以色列人手中,那天約書亞當眾向耶和華禱告:

「太陽啊,停在基遍

月亮啊,停在亞雅崙谷!」

13果然太陽停住了,

月亮也不動了,

直到以色列人殺敗敵人。

《雅煞珥書》記載了這事。約有一天的時間,太陽停留在天空,沒有西沉。 14耶和華這樣垂聽一個人的祈求是空前絕後的,這是因為耶和華要為以色列爭戰。

15後來,約書亞率領以色列軍返回了吉甲的營地。

亞摩利五王被殺

16那五王逃進瑪基大的山洞裡,躲藏起來。 17有人告訴約書亞那五個王藏在瑪基大的山洞裡, 18約書亞便下令說:「滾幾塊大石頭堵住洞口,派人看守。 19你們不可停下來,要繼續追殺敵人,不要讓他們逃回城,你們的上帝耶和華已經把他們交在你們手中了。」 20約書亞以色列人把敵人殺得大敗,幾乎全軍覆沒,一些殘餘都逃進了堅固的城壘。 21以色列人都安然無恙地回到約書亞駐紮的瑪基大營。再也沒有人敢威脅以色列人了。

22約書亞說:「打開洞口,把裡面的五個王押出來見我。」 23眾人便把耶路撒冷王、希伯崙王、耶末王、拉吉王、伊磯倫王從洞裡押出來,帶到約書亞面前。 24約書亞召來全體以色列人,然後對那些跟他一起出征的將領說:「你們上前來,用腳踏在這些王的頸上。」各將領便照著約書亞的吩咐做了。 25約書亞對他們說:「你們不要害怕,也不要驚慌,應該剛強勇敢,因為耶和華要使你們所有的仇敵都落此下場。」 26隨後約書亞將這五個王殺死,把屍體分別掛在五棵樹上,直到傍晚。 27日落時,約書亞才下令把屍體放下,丟在他們先前躲藏的山洞裡,用大石頭堵住洞口,石頭至今還在那裡。

28約書亞在當天佔領了瑪基大,把瑪基大王和所有的居民都殺了,一個沒留。他對待瑪基大王跟以前對待耶利哥王一樣。

29約書亞以色列軍又從瑪基大出發,去攻打立拿30耶和華將立拿城和立拿王交在以色列人手中,他們殺了全城的人,一個沒留。他們對待立拿王跟以前對待耶利哥王一樣。

31約書亞以色列軍從立拿前往拉吉,他們在城外紮營,攻打拉吉32耶和華將拉吉交在以色列人手中,第二天約書亞便攻佔了拉吉,殺了全城的人,就像在立拿所行的一樣。 33基色何蘭前來支持拉吉,結果也被約書亞殺得一個不剩。

34約書亞又率領以色列全軍從拉吉前往伊磯倫,在城外紮營,攻打伊磯倫35他們當天就攻陷該城,殺了城內所有的人,就像在拉吉所行的一樣。

36約書亞和全體以色列人又從伊磯倫去攻打希伯崙37他們攻陷該城及其附屬城邑,殺了希伯崙王和城邑中的居民,一個沒留,就像在伊磯倫所行的一樣。

38然後,約書亞和全體以色列人再回兵攻打底璧39攻取了該城及其附屬城邑,擒獲底璧王,殺了城中所有的人,一個沒留,就像對待希伯崙立拿立拿王一樣。

40這樣,約書亞征服了整個地區,包括山區、南地、丘陵和山坡,按照以色列的上帝耶和華的吩咐殺了當地的諸王和所有的居民,一個沒留。 41約書亞征服了各地,從加低斯·巴尼亞加薩歌珊全境,直到基遍42約書亞能一鼓作氣殺敗諸王,征服他們的土地,都是因為有以色列的上帝耶和華為以色列人爭戰。 43之後,約書亞率領以色列人回到吉甲的營地。