ኢሳይያስ 34 – NASV & NIVUK

New Amharic Standard Version

ኢሳይያስ 34:1-17

ፍርድ በአሕዛብ ላይ

1እናንት አሕዛብ ሆይ፤ ኑ አድምጡም፤

እናንተ ሰዎች ሆይ፤ አስተውሉ።

ምድርና በውስጧ ያለ ሁሉ፣

ዓለምና ከእርሷ የሚበቅል ሁሉ ይስማ።

2እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ ተቈጥቷል፤

ቍጣውም በሰራዊታቸው ሁሉ ላይ ነው፤

ፈጽሞ ያጠፋቸዋል34፥2 በዚህና በቍጥር 5 ላይ የዕብራይስጡ ቃል አንድን ሰው ወይም ነገር ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ለእግዚአብሔር መስጠትን የሚያመለክት ነው።

ለዕርድም አሳልፎ ይሰጣቸዋል።

3ከእነርሱም የተገደሉት ወደ ውጭ ይጣላሉ፤

ሬሳቸው ይከረፋል፤

ተራሮችም ደም በደም ይሆናሉ።

4የሰማይ ከዋክብት ሁሉ ይሟሽሻሉ፤

ሰማይ እንደ ብራና ይጠቀለላል፤

የከዋክብት ሰራዊት ሁሉ፣

ጠውልጎ እንደ ረገፈ የወይን ቅጠል፣

ደርቆም እንደ ወደቀ የበለስ ቅጠል ይሆናሉ።

5ሰይፌ በሰማያት እስኪበቃት ጠጥታለች፤

እነሆ፤ ወደ ኤዶም፣

ፈጽሞ ወዳጠፋሁት ሕዝብ ለፍርድ ወርዳለች።

6የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተነክራለች፤

ሥብ ጠግባለች፤

በበግ ጠቦትና በፍየል ደም፣

በአውራም በግ ኵላሊት ሥብ ተሸፍናለች።

እግዚአብሔር በባሶራ ከተማ መሥዋዕት፣

በኤዶምም ታላቅ ዕርድ አዘጋጅቷልና።

7ጐሽ አብሯቸው፣

ኮርማም ከወይፈን ጋር ይወድቃል፤

ምድራቸው በደም ትርሳለች፤

ዐፈራቸውም ሥብ በሥብ ይሆናል።

8እግዚአብሔር የበቀል ቀን፣

ስለ ጽዮንም የሚሟገትበት ዓመት አለውና።

9የኤዶም ምንጮች ሬንጅ፣

ዐፈሯ የሚቃጠል ድኝ፣

ምድሯም የሚንበለበል ዝፍት ይሆናል።

10እሳቷ ሌሊትና ቀን አይጠፋም፤

ጢሷም ለዘላለም ይትጐለጐላል፤

ከትውልድ እስከ ትውልድ ባድማ ትሆናለች፤

ማንም በዚያ ዳግም አያልፍም።

11ጭልፊትና34፥11 የእነዚህ አዕዋፍ ትክክለኛ ማንነታቸው በትክክል አይታወቅም። ጃርት ይወርሷታል፤

ጕጕትና ቍራም ጐጆ ይሠሩባታል።

እግዚአብሔር በኤዶም ላይ፣

የመፈራረሷን ገመድ፣

የመጥፊያዋንም ቱንቢ ይዘረጋል።

12መሳፍንቷም መንግሥት ተብለው ለመጠራት የሚያስችላቸው ነገር አይኖራቸውም፤

አለቆቿም በሙሉ ጥርግ ብለው ይጠፋሉ።

13በቅጥር የተመሸጉ ከተሞቿን እሾኽ፣

ምሽጎቹንም ሳማና አሜከላ ይወርሷቸዋል፤

የቀበሮዎች ጕድጓድ፣

የጕጕቶችም መኖሪያ ትሆናለች።

14የምድረ በዳ አራዊት ከጅቦች ጋር አብረው ይሆናሉ፤

በበረሓ ፍየል የሚመሰሉ አጋንንትም እርስ በእርስ ይጠራራሉ፤

የሌሊት ፍጥረታት ማረፊያቸውን በዚያ ያደርጋሉ፤

ለራሳቸውም የማረፊያ ቦታ ያገኛሉ።

15ጕጕት በዚያ ጐጆ ሠርታ ዕንቍላል ትጥላለች፤

ትቀፈቅፋለች፤ ጫጩቶቿን በክንፎቿ

ትታቀፋቸዋለች፤

ጭላቶችም ጥንድ ጥንድ ሆነው፣

ለርቢ በዚያ ይሰበሰባሉ።

16በእግዚአብሔር መጽሐፍ እንዲህ የሚለውን ተመልከቱ፤ አንብቡም፤

ከእነዚህ አንዱ አይጐድልም፤

እያንዳንዷም አጣማጇን አታጣም፤

ይህ ትእዛዝ ከአፉ ወጥቷል፤

መንፈሱ በአንድ ላይ ይሰበስባቸዋልና።

17ድርሻ ድርሻቸውን ይመድብላቸዋል፤

እጁም ለክታ ታካፍላቸዋለች።

ለዘላለም የእነርሱ ትሆናለች፤

ከትውልድ እስከ ትውልድም ይኖሩባታል።

New International Version – UK

Isaiah 34:1-17

Judgment against the nations

1Come near, you nations, and listen;

pay attention, you peoples!

Let the earth hear, and all that is in it,

the world, and all that comes out of it!

2The Lord is angry with all nations;

his wrath is on all their armies.

He will totally destroy34:2 The Hebrew term refers to the irrevocable giving over of things or persons to the Lord, often by totally destroying them; also in verse 5. them,

he will give them over to slaughter.

3Their slain will be thrown out,

their dead bodies will stink;

the mountains will be soaked with their blood.

4All the stars in the sky will be dissolved

and the heavens rolled up like a scroll;

all the starry host will fall

like withered leaves from the vine,

like shrivelled figs from the fig-tree.

5My sword has drunk its fill in the heavens;

see, it descends in judgment on Edom,

the people I have totally destroyed.

6The sword of the Lord is bathed in blood,

it is covered with fat –

the blood of lambs and goats,

fat from the kidneys of rams.

For the Lord has a sacrifice in Bozrah

and a great slaughter in the land of Edom.

7And the wild oxen will fall with them,

the bull calves and the great bulls.

Their land will be drenched with blood,

and the dust will be soaked with fat.

8For the Lord has a day of vengeance,

a year of retribution, to uphold Zion’s cause.

9Edom’s streams will be turned into pitch,

her dust into burning sulphur;

her land will become blazing pitch!

10It will not be quenched night or day;

its smoke will rise for ever.

From generation to generation it will lie desolate;

no-one will ever pass through it again.

11The desert owl34:11 The precise identification of these birds is uncertain. and screech owl34:11 The precise identification of these birds is uncertain. will possess it;

the great owl34:11 The precise identification of these birds is uncertain. and the raven will nest there.

God will stretch out over Edom

the measuring line of chaos

and the plumb-line of desolation.

12Her nobles will have nothing there to be called a kingdom,

all her princes will vanish away.

13Thorns will overrun her citadels,

nettles and brambles her strongholds.

She will become a haunt for jackals,

a home for owls.

14Desert creatures will meet with hyenas,

and wild goats will bleat to each other;

there the night creatures will also lie down

and find for themselves places of rest.

15The owl will nest there and lay eggs,

she will hatch them, and care for her young

under the shadow of her wings;

there also the falcons will gather,

each with its mate.

16Look in the scroll of the Lord and read:

None of these will be missing,

not one will lack her mate.

For it is his mouth that has given the order,

and his Spirit will gather them together.

17He allots their portions;

his hand distributes them by measure.

They will possess it for ever

and dwell there from generation to generation.