ኢሳይያስ 11 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ኢሳይያስ 11:1-16

ከእሴይ ግንድ የወጣ ቍጥቋጥ

1ከእሴይ ግንድ ቍጥቋጥ ይወጣል፤

ከሥሮቹም አንዱ ቅርንጫፍ ፍሬ ያፈራል።

2የእግዚአብሔር መንፈስ፣

የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣

የምክርና የኀይል መንፈስ፣

የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።

3እግዚአብሔርን በመፍራት ደስ ይለዋል፤

ዐይኑ እንዳየ አይፈርድም፤

ጆሮውም እንደ ሰማ አይበይንም።

4ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤

ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤

በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤

በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።

5ጽድቅ የወገቡ መታጠቂያ፣

ታማኝነትም የጐኑ መቀነት ይሆናል።

6ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይኖራል፤

ነብርም ከፍየል ግልገል ጋር ይተኛል፤

ጥጃ፣ የአንበሳ ደቦልና የሠባ ከብት11፥6 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ግን፣ የሠባ አንበሳ ይበላል ይላል። በአንድነት ይሰማራሉ፤

ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል።

7ላምና ድብ በአንድነት ይሰማራሉ፤

ልጆቻቸውም አብረው ይተኛሉ፤

አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል።

8ጡት የሚጠባ ሕፃን በአደገኛ እባብ ጕድጓድ ላይ ይጫወታል፤

ጡት የጣለም ሕፃን እጁን በእፉኝት ጕድጓድ ይከትታል።

9በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ

ጕዳት ወይም ጥፋት አያደርሱም፤

ውሃ ባሕርን እንደሚሸፍን፣

ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።

10በዚያን ቀን፣ የእሴይ ሥር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ መንግሥታት ወደ እርሱ ይመጣሉ፤ ማረፊያውም የከበረ ይሆናል። 11በዚያን ቀን፣ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደ ገና የተረፈውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦር፣ ከታችኛው ግብፅ፣ ከላይኛው ግብፅ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኤላም፣ ከባቢሎን፣ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።

12ለመንግሥታት ምልክትን ያቆማል፤

ከእስራኤልም የተሰደዱትን መልሶ ያመጣቸዋል፤

የተበተኑትን የይሁዳ ሕዝብ፣

ከአራቱ የምድር ማእዘን ይሰበስባል።

13የኤፍሬም ምቀኝነት ያከትማል፤

የይሁዳ ጠላቶችም11፥13 ወይም፣ ባላንጣዎቹ ይቈረጣሉ፤

ኤፍሬም በይሁዳ አይቀናም፤

ይሁዳም ኤፍሬምን አይጠላም።

14በምዕራብ በኩል በፍልስጥኤም ተረተር ላይ ይወርዳሉ፤

ሁለቱም ተባብረው በምሥራቅ ያለውን ሕዝብ ይዘርፋሉ፤

በኤዶምና በሞዓብ ላይ እጃቸውን ያነሣሉ፤

አሞናውያንም ይገዙላቸዋል።

15እግዚአብሔር በሚጋረፍም ነፋስ፣

የግብፅን ባሕረ ሰላጤ ያደርቃል፤

እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ11፥15 ዕብራይስጡ ወንዙ ይላል። ላይ ይዘረጋል፤

ሰባት ታናናሽ ጅረትም አድርጎ

ይለያየዋል፤

ስለዚህ ሰዎች ከነጫማቸው መሻገር ይችላሉ።

16እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ

እንደ ሆነው ሁሉ፣

ከአሦር ለተረፈው ቅሬታ ሕዝብ፣

እንዲሁ ጐዳና ይዘጋጅለታል።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

以賽亞書 11:1-16

大衛的後裔做王

1就像樹墩上長出新的枝條,

大衛的後裔中必有一人做王。

2耶和華的靈必住在他身上,

使他有聰明和智慧、謀略和能力,

能認識並敬畏耶和華。

3他必以敬畏耶和華為樂。

他不憑眼見施行審判,

不憑耳聞斷定是非,

4而是按公義審判貧窮人,

以公正為受苦者斷案。

他必用口中的杖擊打世界,

以嘴裡的氣殺戮惡人。

5公義必作他的腰帶,

信實必作他肋下的帶子。

6那時,豺狼和綿羊羔同住,

豹子和山羊羔同臥,

牛犢和獅子同群,

小孩子可以照看牠們。

7牛與熊一起吃喝,

小牛和小熊一起躺臥,

獅子像牛一樣吃草。

8吃奶的嬰孩在毒蛇的洞口玩耍,

斷奶的孩子把手伸進蛇洞。

9在我的整個聖山上,

牠們都不傷人、不害物。

認識耶和華的人必充滿天下,

就像水充滿海洋一樣。

10到那日,耶西的根必成為引導萬民的旗幟,外族人都來尋求他,他的住處充滿榮耀。 11到那日,主必再次伸手從亞述埃及巴特羅古實以攔示拿哈馬和眾海島救回祂剩餘的子民。

12祂必向各國豎立旗幟,

召集被擄的以色列人,

把分散在世界各地的猶大人聚集起來。

13以色列必不再嫉妒猶大

猶大必不再與以色列為敵,

以色列的嫉妒和猶大的敵意必煙消雲散。

14他們必聯合起來,

向西征討非利士

向東征服以東摩押亞捫

15耶和華必使埃及的海乾涸,

揮手用焦熱的風使幼發拉底河分成七條溪流,

使人可以涉水而過。

16祂剩餘的子民必沿著大路從亞述歸回,

就像昔日以色列人離開埃及一樣。