አሞጽ 3 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

አሞጽ 3:1-15

በእስራኤል ላይ የተጠሩ ምስክሮች

1የእስራኤል ልጆች ሆይ፤ እግዚአብሔር በእናንተ ከግብፅ ባወጣሁት ሕዝብ ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤

2“ከምድር ወገን ሁሉ፣

እናንተን ብቻ መረጥሁ፤

ስለዚህ ስለ ሠራችሁት ኀጢአት ሁሉ፣

እኔ እቀጣችኋለሁ።”

3በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይስማሙ፣

አብረው መጓዝ ይችላሉን?

4አንበሳ የሚበላውን ሳያገኝ፣

በጫካ ውስጥ ይጮኻልን?

ምንም ነገርስ ሳይዝ፣

በዋሻው ውስጥ ያገሣልን?

5ወጥመድ ሳይዘረጋ፣

ወፍ በምድር ላይ ይጠመዳልን?

የሚይዘው ነገር ሳይኖርስ፣

ወጥመዱ ከምድር ይፈነጠራልን?

6የመለከት ድምፅ በከተማ ውስጥ ሲሰማ፣

ሰዎች አይደነግጡምን?

ጥፋትስ በከተማ ላይ ቢደርስ፣

ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?

7በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምስጢሩን

ለአገልጋዮቹ ለነቢያት ሳይገልጥ፣

ምንም ነገር አያደርግም።

8አንበሳ አገሣ፤

የማይፈራ ማን ነው?

ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤

ትንቢት የማይናገር ማን ነው?

9ለአዛጦን ምሽግ፣

ለግብፅም ምሽግ እንዲህ ብላችሁ ዐውጁ፤

“በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፤

በውስጧ ያለውን ታላቅ ሁከት፣

በሕዝቧም መካከል ያለውን ግፍ እዩ።”

10“ቅሚያንና ዝርፊያን በምሽጋቸው ውስጥ የሚያከማቹ፣

በጎ ነገር ማድረግን አያውቁም፤”

ይላል እግዚአብሔር

11ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“ጠላት ምድሪቱን ይወርራል፤

ምሽጎቻችሁን ያፈርሳል፤ ድንኳኖቻችሁን

ይዘርፋል።”

12እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

“እረኛ ከአንበሳ መንጋጋ፣

ሁለት የእግር ዐጥንት ወይም የጆሮ ቍራጭ እንደሚያድን፣

እንዲሁም በሰማርያ በዐልጋቸው3፥12 በዕብራይስጡ ለዚህ ዐረፍተ ነገር የተሰጠው ትርጕም አይታወቅም ጫፍ ላይ፣

በደማስቆም በምንጣፋቸው ላይ የተቀመጡ፣

እስራኤላውያን ይድናሉ።”

13“ይህን ስሙ፤ በያዕቆብም ቤት ላይ መስክሩ” ይላል ጌታ፣ ሁሉን የሚገዛ አምላክ እግዚአብሔር

14“እስራኤልን ስለ ኀጢአቷ በምቀጣበት ቀን፣

የቤቴልን መሠዊያዎች አፈርሳለሁ፤

የመሠዊያው ቀንዶች ይቈረጣሉ፤

ወደ ምድርም ይወድቃሉ።

15የክረምቱን ቤት፣

ከበጋው ቤት ጋር እመታለሁ፤

በዝኆን ጥርስ ያጌጡ ቤቶችም ይደመሰሳሉ፤

ታላላቅ አዳራሾችም ይፈርሳሉ፤”

ይላል እግዚአብሔር

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

阿摩司書 3:1-15

責備以色列人

1以色列人啊,

要聽耶和華責備你們的話,

責備我從埃及領出來的整個民族的話,

2『世上萬族之中,我只揀選了你們,

所以我要因你們的罪惡而懲罰你們。』」

3若非相約,

二人怎會同行呢?

4若非捕到獵物,

獅子怎會在林中咆哮呢?

若非獵獲食物,

猛獅怎會在洞中吼叫呢?

5若非設下誘餌,

鳥兒怎會陷入網羅呢?

若非有什麼陷進去,

網羅怎會收起來呢?

6若城中響起號角,

居民豈不恐懼顫抖?

若災禍降臨城中,

豈不是耶和華的作為?

7的確,主耶和華不向祂的僕人——眾先知顯明祂的計劃,

就不會採取任何行動。

8獅子吼叫,誰不懼怕呢?

主耶和華已發言,誰能不傳講呢?

9要向亞實突埃及的城堡宣告:

「你們要聚集到撒瑪利亞的山上,

看看城中的混亂和暴虐之事。

10他們不知正道,強取豪奪,

在他們的堡壘中積斂錢財。

這是耶和華說的。」

11所以,主耶和華說:

「敵人要圍攻此地,

攻破他們的防守,

搶掠他們的城堡。」

12耶和華說:

「牧人從獅口中救羊,

只能奪回兩條腿和一塊耳朵。

同樣,住在撒瑪利亞以色列人被救回的時候,

也僅剩一片床榻和一角臥椅。」

13主——萬軍之上帝耶和華說:

「你們要聽這話,去警告雅各家。

14我追討以色列人的罪時,

要摧毀伯特利的祭壇,

將祭壇的角砍落在地。

15我要拆毀過冬和避暑的房屋,

搗毀象牙裝飾的宮殿,

推倒許多宏偉的樓宇。

這是耶和華說的。」