ነህምያ 9 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ነህምያ 9:1-38

እስራኤላውያን ኀጢአታቸውን ተናዘዙ

1በዚያኑ ወር ሃያ አራተኛ ቀን እስራኤላውያን ጾመው፣ ማቅ ለብሰው፣ በራሳቸው ላይ ትቢያ ነስንሰው በአንድነት ተሰበሰቡ። 2የእስራኤላውያን ዘር የሆኑትም ራሳቸውን ከባዕዳን ሁሉ ለዩ። ቆመውም ኀጢአታቸውንና የአባቶቻቸውን በደል ተናዘዙ። 3በያሉበትም ቦታ ቆመው ከአምላካቸው ከእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ሩብ ቀን አነበቡ፤ የቀረውን ሩብ ቀን ደግሞ ንስሓ በመግባትና ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር በመስገድ አሳለፉ። 4ሌዋውያኑ ኢያሱ፣ ባኒ፣ ቀድምኤል፣ ሰበንያ፣ ቡኒ፣ ሰራብያ፣ ባኒ፣ ከናኒ፣ በመውጫ ደረጃዎች ላይ ቆሙ፤ ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔርም በታላቅ ድምፅ ጮኹ። 5ሌዋውያኑ ኢያሱ፣ ቀድምኤል፣ ባኒ፣ አሰበንያ፣ ሰራብያ፣ ሆዲያ፣ ሰበንያና ፈታያ፣ “ተነሥታችሁ ቁሙ፤ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የሚኖረውን አምላካችሁን እግዚአብሔርን ወድሱ” አሉ።

“ክቡር ስምህ የተመሰገነ ይሁን፤ ከምስጋና ሁሉና ከውዳሴም በላይ ከፍ ከፍ ይበል። 6አንተ ብቻ እግዚአብሔር ነህ። ሰማያትን፣ ከሰማያት በላይ ያሉትን ሰማያትና የከዋክብታቸውን ሰራዊት ሁሉ፣ ምድርንና በላይዋ ያለውን ሁሉ፣ ባሕሮችንና በውስጣቸው ያሉትንም ሁሉ ፈጥረሃል። ለሁሉም ሕይወትን ትሰጣለህ፤ የሰማይ ሰራዊትም ይሰግዱልሃል።

7“አብራምን የመረጥኸውና ከከለዳውያን ዑር አውጥተህ አብርሃም የሚል ስም የሰጠኸው አንተ እግዚአብሔር አምላክ ነህ። 8ልቡ ለአንተ የታመነ ሆኖ ስላገኘኸውም፣ የከነዓናውያንን የኬጢያውያንን፣ የአሞራውያንን፣ የፌርዛውያንን፣ የኢያቡሳውያንንና የጌርጌሳውያንን ምድር ለዘሮቹ ለመስጠት ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገባህ፤ ጻድቅ ስለ ሆንህም የሰጠኸውን ተስፋ ጠበቅህ።

9“አንተ በግብፅ የአባቶቻችንን ሥቃይ አየህ፤ በቀይ ባሕርም9፥9 ዕብራይስጡ፣ ያም ሱፍ ይላል፤ ይኸውም የደንገል ባሕር ማለት ነው። ጩኸታቸውን ሰማህ። 10ታምራታዊ ምልክቶችንና ድንቆችን በፈርዖንና፣ በሹማምቱ ሁሉ፣ በምድሩም ሕዝብ ሁሉ ላይ ላክህ፤ ይህንም ያደረግኸው ግብፃውያን እንዴት በእብሪት እንዳስጨነቋቸው ስላወቅህ ነው። እስከ ዛሬም የሚጠራ ስም ለራስህ እንዲኖርህ አደረግህ። 11በደረቅ ምድር እንዲሻገሩ ባሕሩን በፊታቸው ከፈልህ፤ ያሳደዷቸውን ግን በኀይለኛ ውሃ ውስጥ እንደሚጣል ድንጋይ ወደ ጥልቁ ውስጥ ወረወርሃቸው። 12ቀን በደመና ዐምድ፣ በሚሄዱበት መንገድ ታበራላቸውም ዘንድ ሌሊት በእሳት ዐምድ መራሃቸው።

13“በሲና ተራራ ላይ ወረድህ፤ ከሰማይም ተናገርሃቸው። ትክክለኛ ደንቦችንና እውነተኛ ሕጎችን፣ መልካም ሥርዐቶችንና ትእዛዞችን ሰጠሃቸው። 14የተቀደሰች ሰንበትህን አስታወቅሃቸው፤ ትእዛዞችን፣ ሥርዐቶችንና ሕጎችን በባሪያህ በሙሴ አማካይነት ሰጠሃቸው። 15በተራቡ ጊዜ ከሰማይ መና ሰጠሃቸው፤ በተጠሙም ጊዜ ከዐለት ውሃ አፈለቅህላቸው፤ ልትሰጣቸው በተዘረጋች እጅ ወደ ማልህላቸውም ምድር ገብተው እንዲወርሱ አዘዝሃቸው።

16“እነርሱና አባቶቻችን ግን ትምክሕተኞችና ዐንገተ ደንዳኖች ሆኑ፤ ትእዛዞችህንም አልፈጸሙም። 17ለመስማት አልፈለጉም፤ በመካከላቸውም ያደረግሃቸውን ታምራት ማስታወስ አልቻሉም። ዐንገታቸውን አደነደኑ፤ በዐመፃቸውም ወደ ባርነታቸው ለመመለስ መሪ ሾሙ። አንተ ግን ይቅር ባይ አምላክ፣ ቸርና ርኅሩኅ፣ ለቍጣም የዘገየህና ምሕረትህ የበዛ ነህ። ስለዚህ አልተውሃቸውም፤ 18የጥጃ ምስል ለራሳቸው አቅልጠው፣ ‘ከግብፅ ያወጣህ አምላክ ይህ ነው’ ባሉና አስጸያፊ የስድብ ቃል በተናገሩ ጊዜ እንኳ አልተለየሃቸውም።

19“ከርኅራኄህ ብዛት የተነሣ በምድረ በዳ አልተውሃቸውም፤ ቀን የደመናው ዐምድ በመንገዳቸው ላይ መምራቱን፣ ሌሊትም የእሳቱ ዐምድ በሚሄዱበት ላይ ማብራቱን አላቆመም። 20ያስተምራቸው ዘንድ ቸር መንፈስህን ሰጠሃቸው፤ መናውን ከአፋቸው አልከለከልህም፤ በተጠሙ ጊዜ ውሃ ሰጠሃቸው። 21በምድረ በዳ አርባ ዓመት መገብሃቸው፤ ምንም ያጡት አልነበረም፤ ልብሳቸው አላለቀም፤ እግራቸውም አላበጠም።

22“በሩቅ የሚገኙትን ድንበሮች እንኳ ሳይቀር፣ መንግሥታትንና አሕዛብን ሰጠሃቸው። የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፣ የባሳን ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ። 23ወንዶች ልጆቻቸውን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛሃቸው፤ አባቶቻቸው ገብተው እንዲወርሱ ወዳዘዝሃቸውም ምድር አገባሃቸው። 24በምድሪቱ ወንዶች ልጆቻቸው ገቡባት፤ ወረሷትም። በምድሪቱ ላይ ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያን በፊታቸው አንበረከክህ፤ ያሻቸውን ያደርጉባቸው ዘንድ ከነዓናውያንን ከንጉሦቻቸውና ከምድሪቱ ሕዝቦች ጋር በእጃቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው። 25የተመሸጉ ከተሞቻቸውንና የሠባውን ምድር ያዙ፤ በመልካም ነገር ሁሉ የተሞሉ ቤቶቻቸውን፣ የተቈፈሩ የውሃ ጕድጓዶቻቸውን፣ የወይን ተክላቸውን፣ የወይራ ዛፎቻቸውንና ስፍር ቍጥር የሌላቸውን የፍሬ ዛፎች ያዙ። እስኪጠግቡ በሉ፤ ወፈሩም፤ በታላቅ በጎነትህም ደስ ተሰኙ።

26“ነገር ግን እንቢተኞች ሆኑ፤ ዐመፁብህም፤ ሕግህንም አሽቀንጥረው ጣሉ፤ ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩት ነቢያትህን ገደሉ፤ አስጸያፊ የስድብ ቃልም ተናገሩ። 27ስለዚህ ላስጨነቋቸው ጠላቶቻቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው። በተጨነቁ ጊዜ ግን ወደ አንተ ጮኹ፤ አንተም ከሰማይ ሰማሃቸው፤ ከርኅራኄህም ብዛት የተነሣ ከጠላቶቻቸው እጅ የሚያድኗቸውን ታዳጊዎች ሰጠሃቸው።

28“ነገር ግን ዕረፍት ባገኙ ጊዜ፣ በፊትህ ክፉውን ነገር እንደ ገና ፈጸሙ፤ ከዚያም ይገዟቸው ዘንድ በጠላቶቻቸው እጅ ጣልሃቸው፤ እንደ ገና ወደ አንተ በጮኹ ጊዜ፣ ከሰማይ ሰማህ፤ በርኅራኄህም በየጊዜው ታደግሃቸው።

29“ወደ ሕግህ እንዲመለሱ አስጠነቀቅሃቸው፤ እነርሱ ግን እብሪተኞች ሆኑ። ትእዛዞችህንም አልፈጸሙም፤ አንድ ሰው ቢፈጽማቸው በሕይወት የሚኖርባቸውን ሥርዐቶችህን ተላለፉ። እንቢተኞች ሆነው ጀርባቸውን አዞሩብህ፤ ዐንገታቸውን አደነደኑ፤ መስማትም አልፈለጉም። 30ብዙ ዘመን ታገሥሃቸው፤ በነቢያትህ አማካይነት በመንፈስህ አስጠነቀቅሃቸው። ነገር ግን አላደመጡህም፤ ከዚህም የተነሣ ጎረቤቶቻቸው ለሆኑ አሕዛብ አሳልፈህ ሰጠሃቸው። 31አንተ ግን ቸርና መሓሪ አምላክ ነህና ከምሕረትህ ብዛት የተነሣ፣ ፈጽመህ አላጠፋሃቸውም፤ አልተውሃቸውምም።

32“አሁንም አምላካችን ሆይ፤ ቃል ኪዳንህንና ዘላለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ ታላቅ፣ ኀያልና የተፈራህ አምላክ ሆይ፤ ከአሦር ነገሥታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ፣ በነገሥታታችንና በመሪዎቻችን፣ በካህናታችንና በነቢያታችን፣ በአባቶቻችንና በመላው ሕዝብህ ላይ የደረሰው ይህ ሁሉ መከራ በፊትህ እንደ ቀላል ነገር አይታይ። 33በደረሰብን ሁሉ አንተ ጻድቅ ነህ፤ እኛ በደለኞች ነን፤ አንተ ግን ትክክለኛውን አደረግህ። 34ነገሥታታችን፣ መሪዎቻችን፣ ካህናታችንና አባቶቻችን ሕግህን አልጠበቁም፤ ትእዛዞችህን ወይም የሰጠሃቸውን ማስጠንቀቂያዎች አልሰሙም። 35በገዛ መንግሥታቸው፣ በሰጠሃቸው ታላቅ በጎነትህና በፊታቸውም ባዘጋጀህላቸው ሰፊና ለም ምድር እንኳ፣ አንተን አላገለገሉም፤ ከክፉ መንገዳቸውም አልተመለሱም።

36“እነሆ፤ ዛሬም ባሮች ነን፤ አባቶቻችን ፍሬዋንና በረከቷን እንዲበሉ በሰጠሃቸው ምድር ባሮች ነን። 37ከኀጢአታችን የተነሣ የተትረፈረፈው መከር ሲሳይ የሆነው በላያችን ላስቀመጥሃቸው ነገሥታት ነው፤ እነርሱም ደስ እንዳሰኛቸው በሰውነታችንና በቀንድ ከብቶቻችን ላይ ያዝዛሉ። እኛም በታላቅ ጭንቀት ውስጥ እንገኛለን።”

የሕዝቡ መስማማት

38“ከዚህ ሁሉ የተነሣም ጽሑፍ ላይ በማስፈር ግዴታ የምንገባበትን የውል ስምምነት እናደርጋለን፤ መሪዎቻችን፣ ሌዋውያኖቻችንና ካህናታችንም ማኅተሞቻቸውን ያኖሩበታል።”

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

尼希米記 9:1-38

以色列人認罪禱告

1這月二十四日,以色列人聚集禁食。他們身披麻衣,頭撒塵土。 2以色列人與其他外族人隔離,站著承認自己的罪惡和祖先的過犯。 3他們站在自己的地方,宣讀他們上帝耶和華的律法書,長達三個小時9·3 三個小時」希伯來文是「一天的四分之一」。。他們又用了三個小時認罪,敬拜他們的上帝耶和華。 4利未耶書亞巴尼甲篾示巴尼布尼示利比巴尼基拿尼站在臺上,大聲呼求他們的上帝耶和華。 5利未耶書亞甲篾巴尼哈沙尼示利比荷第雅示巴尼毗他希雅說:「起來稱頌你們的上帝耶和華,直到永永遠遠。耶和華啊,你榮耀的聖名當受稱頌!願你的名被尊崇,超過一切稱頌和讚美!

6「你,唯有你是耶和華!你造了天、天上的天和天上的萬象、地和地上的一切、海和海中的一切,你賜給他們生命。眾天軍都敬拜你。 7你是耶和華上帝,你揀選了亞伯蘭,帶他離開迦勒底吾珥,又給他改名為亞伯拉罕8你知道他對你忠心,就與他立約,把迦南人、人、亞摩利人、比利洗人、耶布斯人及革迦撒人的土地賜給他的後代。你實現了你的應許,因為你是公義的。

9「你看見我們祖先在埃及所受的苦,又聽見他們在紅海邊的呼求, 10就行神蹟奇事對付法老及其所有的臣僕和國民,因為你知道他們對以色列人行事狂傲。你使自己威名遠揚直到今日。 11你在我們祖先面前把海水分開,使他們在海中走乾地過去;你把追趕他們的人扔進深海,好像把石頭扔進大水中。 12白天,你用雲柱帶領他們;夜間,你用火柱照亮他們當走的路。 13你降臨在西奈山,從天上與他們說話,賜給他們公正的典章、信實的律法、美好的律例和誡命。 14你使他們知道你的神聖安息日,藉你僕人摩西賜給他們誡命、律例和法度。 15他們餓了,你賜下天糧給他們吃;他們渴了,你使磐石流出水給他們喝。你吩咐他們去佔領你起誓賜給他們的土地。 16但我們的祖先行事狂傲,頑固不化,不肯聽從你的誡命。 17他們拒絕聽從,忘記了你為他們所行的奇事,頑固不化,自立首領要回埃及做奴隸。但你是樂意饒恕,有恩典,有憐憫,不輕易發怒,充滿慈愛的上帝,你沒有離棄他們。 18縱使他們為自己鑄造了一頭牛犢,聲稱那是把他們帶出埃及的上帝,大大褻瀆了你, 19你還是對他們大施憐憫,沒有在曠野離棄他們。白天,雲柱沒有離開他們,仍然引導他們前行;夜間,火柱仍然照亮他們當走的路。 20你差遣你良善的靈去教導他們,沒有停止賜他們嗎哪吃,也沒有停止賜他們水喝。 21在曠野的四十年間,你供養他們,使他們一無所缺,他們的衣服沒有穿破,腳也沒有走腫。

22「你將列國和萬民賜給他們,為他們劃分疆界,他們佔領了希實本西宏巴珊的土地。 23你使他們的子孫多如天上的星星,你帶領他們進入你應許他們祖先的土地。 24他們的子孫進去佔領了那地方,你在他們面前制伏了那裡的迦南人,把迦南諸王和那地方的人交在他們手裡,任由他們處置。 25他們奪取堅固的城池、肥沃的土地、裝滿美物的房屋、挖好的水井、葡萄園、橄欖園以及各樣的果樹。他們吃得飽足,身體發胖,享受你的厚恩。

26「然而,他們不順從你,背叛你,把你的律法拋在背後,又殺掉勸誡他們歸向你的眾先知,大大褻瀆了你。 27於是你把他們交在欺壓他們的仇敵手中。他們在患難中向你呼求,你就從天上垂聽,懷著豐盛的憐憫賜給他們拯救者,把他們從仇敵手中拯救出來。 28可是,他們得享平安後,又在你面前作惡,於是你離棄他們,把他們交在敵人手中,使敵人統治他們。他們回轉向你呼求,你就從天上垂聽,你一次次地懷著憐憫拯救他們。 29你警告他們,要使他們遵守你的律法,但他們行事狂傲,不聽從你的誡命,干犯你的典章。人若遵行這典章就必存活,但他們背棄你,頑固不化,不肯聽從。 30你多年來容忍他們,差遣你的靈藉著你的眾先知警告他們,但他們依然不肯聽從,於是你把他們交在列邦手中。 31然而,你大施憐憫,沒有完全毀滅他們,也沒有離棄他們,因為你是有恩典和憐憫的上帝。

32「因此,我們的上帝啊,你是偉大、全能、可畏、守約、施慈愛的上帝,求你不要輕看我們的王、首領、祭司、先知、祖先和你的子民從亞述諸王時代直到今天所受的苦難。 33在這臨到我們的一切事上,你都是公義的,因為你行事信實,我們行事邪惡。 34我們的王、首領、祭司和祖先沒有遵行你的律法,也沒有留心聽從你的誡命和你給他們的警告。 35他們即使在本國,在你賜給他們廣闊肥沃的土地上得享你的厚恩,也不事奉你,不離開惡道。 36今天,我們淪為奴隸,在你賜給我們祖先的土地上,在你讓我們祖先享用其出產和各樣美物的土地上,我們淪為奴隸。 37因為我們的罪過,這地方的豐富出產都歸給了那些你派來統管我們的王。他們隨意統管我們和我們的牲畜。我們生活在極大的苦難中。

38「鑒於這一切,我們鄭重立約,記載下來。我們的首領、利未人和祭司都在上面蓋了印。」