ሰቈቃወ 2 – NASV & NIVUK

New Amharic Standard Version

ሰቈቃወ 2:1-22

א አሌፍ

2 ይህ ምዕራፍ ጥቅሶቹ ተከታታይ ፊደላት ባሉት የዕብራይስጥ ሆህያት የሚጀምር፣ የመጀመሪያው ወይም የመጨረሻው መሥመር ትርጕም የሚሰጥ ቃል ወይም ዐረፍተ ነገር ያለው ግጥም ነው። 1ጌታ የጽዮንን ሴት ልጅ፣

በቍጣው ደመና እንዴት ጋረዳት!2፥1 ወይም እግዚአብሔር በቍጣው የጽዮንን ሴት ልጅ እንዴት አዋረዳት!

ከሰማይ ወደ ምድር፣

የእስራኤልን ክብር ወርውሮ ጣለው፤

በቍጣው ቀን፣

የእግሩን መቀመጫ አላስታወሰም።

ב ቤት

2የያዕቆብን መኖሪያ ሁሉ፣

ጌታ ያለ ርኅራኄ ዋጣቸው፤

የይሁዳን ሴት ልጅ ምሽጎች፣

በቍጣው አፈረሳቸው፤

መንግሥቷንና መሳፍንቷን፣

በማዋረድ ወደ ምድር ጣላቸው።

ג ጊሜል

3በጽኑ ቍጣው፣

የእስራኤልን ቀንድ ሁሉ2፥3 ወይም ብርታትን ሁሉ፤ ወይም ንጉሥ ሁሉ፤ ቀንድ በዚህ ቦታ ብርታትን ያመለክታል። ሰበረ፤

ጠላት በተቃረበ ጊዜ፣

ቀኝ እጁን ወደ ኋላ መለሰ፤

በዙሪያው ያለውን ሁሉ እንደሚበላ እሳት፣

በያዕቆብ ላይ የእሳት ነበልባል ነደደ።

ד ዳሌት

4እንደ ጠላት ቀስቱን ገተረ፤

ቀኝ እጁ ተዘጋጅታለች፤

ለዐይን ደስ የሚያሰኙትን ሁሉ፤

እንደ ጠላት ዐረዳቸው፤

በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን ላይ፣

ቍጣውን እንደ እሳት አፈሰሰ።

ה ሄ

5ጌታ እንደ ጠላት ሆነ፤

እስራኤልንም ዋጠ፤

ቤተ መንግሥቶቿን ሁሉ ዋጠ፤

ምሽጎቿን አፈራረሰ፤

በይሁዳ ሴት ልጅ፣

ልቅሶንና ሰቈቃን አበዛ።

ו ዋው

6ማደሪያውን እንደ አትክልት ስፍራ ባዶ አደረገ፤

መሰብሰቢያ ስፍራውን አፈረሰ፤

እግዚአብሔር ጽዮንን፣

ዓመት በዓላቶቿንና ሰንበታቷን እንድትረሳ አደረጋት፤

በጽኑ ቍጣው፣

ንጉሡንና ካህኑን እጅግ ናቀ።

ז ዛይን

7ጌታ መሠዊያውን ናቀ፤

መቅደሱንም ተወ፤

የቤተ መንግሥቶቿን ቅጥሮች፣

ለጠላት አሳልፎ ሰጠ፤

በዓመት በዓል ቀን እንደሚደረገው

በእግዚአብሔር ቤት በኀይል ጮኹ።

ח ኼት

8በጽዮን ሴት ልጅ ዙሪያ ያለውን ቅጥር፣

እግዚአብሔር ለማፍረስ ወሰነ፤

የመለኪያ ገመድ ዘረጋ፤

ከማጥፋትም እጆቹን አልሰበሰበም፤

ምሽጎችና ቅጥሮች እንዲያለቅሱ አደረገ፤

በአንድነትም ጠፉ።

ט ቴት

9በሮቿ ወደ ምድር ሰመጡ፤

የብረት መወርወሪያዎቻቸውን ሰባበረ፤ አጠፋቸውም፤

ንጉሧና መሳፍንቷ በአሕዛብ መካከል ተማርከው ተሰድደዋል፤

ሕጉ ከእንግዲህ አይኖርም፤

ነቢያቷም ከእንግዲህ፣

ከእግዚአብሔር ራእይ አያገኙም።

י ዮድ

10የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች፣

በምድር ላይ በዝምታ ተቀምጠዋል፤

በራሳቸው ላይ ትቢያ ነሰነሱ፤

ማቅም ለበሱ፤

የኢየሩሳሌም ወጣት ሴቶች፣

ራሳቸውን ወደ ምድር ዝቅ አደረጉ።

כ ካፍ

11ዐይኔ በልቅሶ ደከመ፤

ነፍሴ በውስጤ ተሠቃየች፤

ልቤም በሐዘን ፈሰሰች፣

በከተማዪቱ መንገዶች ላይ፣

ሕዝቤ ተደምስሰዋልና፤

ልጆችና ሕፃናት ደክመዋልና።

ל ላሜድ

12በከተማዪቱ መንገዶች ላይ፣

እንደ ቈሰሉ ሰዎች ሲደክሙ፣

በእናታቸው ክንድ ላይ፣

ነፍሳቸው በመውጣት ላይ ሳለች፣

“እንጀራና የወይን ጠጅ የት አለ?”

እያሉ እናቶቻቸውን ይጠይቃሉ።

מ ሜም

13የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፤ ስላንቺ ምን ማለት እችላለሁ?

ከምንስ ጋር አወዳድርሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፤

አጽናናሽ ዘንድ፣

በምን ልመስልሽ እችላለሁ?

ቍስልሽ እንደ ባሕር ጥልቅ ነው፤

ማንስ ሊፈውስሽ ይችላል?

נ ኑን

14የነቢያቶችሽ ራእይ፣

ሐሰትና ከንቱ ነው፤

ምርኮኛነትሽን ለማስቀረት፣

ኀጢአትሽን አይገልጡም።

የሚሰጡሽም የትንቢት ቃል፣

የሚያሳስትና ከመንገድ የሚያወጣ ነው።

ס ሳሜክ

15በአጠገብሽ የሚያልፉ ሁሉ፣

እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል፤

“የውበት መደምደሚያ፣ የምድር ሁሉ ደስታ፣

የተባለች ከተማ ይህች ናትን?”

እያሉ ራሳቸውን በመነቅነቅ፣

በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያሾፋሉ።

ע ዐዪን

16ጠላቶችሽ ሁሉ በአንድ ላይ፣

አፋቸውን በኀይል ከፈቱ፤

ጥርሳቸውን እያፏጩ አሾፉ፤

እንዲህም አሉ፤ “ውጠናታል፤

የናፈቅነው ጊዜ ይህ ነበር፤

ኖረንም ልናየው በቃን።”

פ ፌ

17እግዚአብሔር ያሰበውን አደረገ፤

ከረዥም ጊዜ በፊት የተናገረውን፣

ቃሉን ፈጸመ፤

ያለ ርኅራኄ አፈረሰሽ፤

ጠላት በሥቃይሽ ላይ እንዲደሰት፣

የጠላትሽንም ቀንድ2፥17 ቀንድ በዚህ ቦታ ብርታትን ያመለክታል ከፍ ከፍ አደረገ።

צ ጻዲ

18የሕዝቡ ልብ፣ ወደ ጌታ ጮኸ።

የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፤

ቀንና ሌሊት፣

እንባሽ እንደ ወንዝ ይፍሰስ፤

ለራስሽ ዕረፍትን አትስጪ፣

ዐይኖችሽ ከማንባት አያቋርጡ።

ק ቆፍ

19የሌሊቱ ሰዓት ሲጀምር፣

ተነሺ በሌሊት ጩኺ፤

በጌታ ፊት፣

ልብሽን እንደ ውሃ አፍስሺ፤

በየመንገዱ ዳር ላይ፣ በራብ ስለወደቁት፣

ስለ ልጆችሽ ሕይወት፣ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።

ר ሬሽ

20አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ እይ፤ ተመልከትም፤

በማን ላይ እንዲህ አድርገህ ታውቃለህ?

በውኑ እናቶች ሕፃኖቻቸውን፣

ተንከባክበው ያሳደጓቸውን ልጆች ይብሉን?

ካህኑና ነቢዩስ፣

በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ይገደሉን?

ש ሲን እና ሺን

21በየመንገዱ ዐቧራ ላይ፣

ወጣትና ሽማግሌ በአንድነት ወደቁ፤

ወይዛዝርቴና ጐበዛዝቴ፣

በሰይፍ ተገደሉ፤

በቍጣህ ቀን ገደልሃቸው፤

ያለ ርኅራኄም ዐረድሃቸው።

ת ታው

22“በበዓል ቀን ለግብዣ እንደምትጠራ፣

ሽብርን ከየአቅጣጫው በእኔ ላይ ጠራህ፤

በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን፣

ማንም አላመለጠም ወይም አልተረፈም፤

የተንከባከብኋቸውንና ያሳደግኋቸውን፣

ጠላቴ አጠፋብኝ።”

New International Version – UK

Lamentations 2:1-22

This chapter is an acrostic poem, the verses of which begin with the successive letters of the Hebrew alphabet. 1How the Lord has covered Daughter Zion

with the cloud of his anger2:1 Or How the Lord in his anger / has treated Daughter Zion with contempt!

He has hurled down the splendour of Israel

from heaven to earth;

he has not remembered his footstool

in the day of his anger.

2Without pity the Lord has swallowed up

all the dwellings of Jacob;

in his wrath he has torn down

the strongholds of Daughter Judah.

He has brought her kingdom and its princes

down to the ground in dishonour.

3In fierce anger he has cut off

every horn2:3 Or off / all the strength; or every king2:3 Horn here symbolises strength. of Israel.

He has withdrawn his right hand

at the approach of the enemy.

He has burned in Jacob like a flaming fire

that consumes everything around it.

4Like an enemy he has strung his bow;

his right hand is ready.

Like a foe he has slain

all who were pleasing to the eye;

he has poured out his wrath like fire

on the tent of Daughter Zion.

5The Lord is like an enemy;

he has swallowed up Israel.

He has swallowed up all her palaces

and destroyed her strongholds.

He has multiplied mourning and lamentation

for Daughter Judah.

6He has laid waste his dwelling like a garden;

he has destroyed his place of meeting.

The Lord has made Zion forget

her appointed festivals and her Sabbaths;

in his fierce anger he has spurned

both king and priest.

7The Lord has rejected his altar

and abandoned his sanctuary.

He has given the walls of her palaces

into the hands of the enemy;

they have raised a shout in the house of the Lord

as on the day of an appointed festival.

8The Lord determined to tear down

the wall around Daughter Zion.

He stretched out a measuring line

and did not withhold his hand from destroying.

He made ramparts and walls lament;

together they wasted away.

9Her gates have sunk into the ground;

their bars he has broken and destroyed.

Her king and her princes are exiled among the nations,

the law is no more,

and her prophets no longer find

visions from the Lord.

10The elders of Daughter Zion

sit on the ground in silence;

they have sprinkled dust on their heads

and put on sackcloth.

The young women of Jerusalem

have bowed their heads to the ground.

11My eyes fail from weeping,

I am in torment within;

my heart is poured out on the ground

because my people are destroyed,

because children and infants faint

in the streets of the city.

12They say to their mothers,

‘Where is bread and wine?’

as they faint like the wounded

in the streets of the city,

as their lives ebb away

in their mothers’ arms.

13What can I say for you?

With what can I compare you,

Daughter Jerusalem?

To what can I liken you,

that I may comfort you,

Virgin Daughter Zion?

Your wound is as deep as the sea.

Who can heal you?

14The visions of your prophets

were false and worthless;

they did not expose your sin

to ward off your captivity.

The prophecies they gave you

were false and misleading.

15All who pass your way

clap their hands at you;

they scoff and shake their heads

at Daughter Jerusalem:

‘Is this the city that was called

the perfection of beauty,

the joy of the whole earth?’

16All your enemies open their mouths

wide against you;

they scoff and gnash their teeth

and say, ‘We have swallowed her up.

This is the day we have waited for;

we have lived to see it.’

17The Lord has done what he planned;

he has fulfilled his word,

which he decreed long ago.

He has overthrown you without pity,

he has let the enemy gloat over you,

he has exalted the horn2:17 Horn here symbolises strength. of your foes.

18The hearts of the people

cry out to the Lord.

You walls of Daughter Zion,

let your tears flow like a river

day and night;

give yourself no relief,

your eyes no rest.

19Arise, cry out in the night,

as the watches of the night begin;

pour out your heart like water

in the presence of the Lord.

Lift up your hands to him

for the lives of your children,

who faint from hunger

at every street corner.

20‘Look, Lord, and consider:

whom have you ever treated like this?

Should women eat their offspring,

the children they have cared for?

Should priest and prophet be killed

in the sanctuary of the Lord?

21‘Young and old lie together

in the dust of the streets;

my young men and young women

have fallen by the sword.

You have slain them in the day of your anger;

you have slaughtered them without pity.

22‘As you summon to a feast day,

so you summoned against me terrors on every side.

In the day of the Lord’s anger

no-one escaped or survived;

those I cared for and reared

my enemy has destroyed.’