ራእይ 1 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ራእይ 1:1-20

1ቶሎ መሆን የሚገባውን ነገር ለአገልጋዮቹ እንዲያሳይ፣ እግዚአብሔር ለእርሱ የሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ ይህ ነው፤ ኢየሱስም መልአኩን ልኮ ለአገልጋዩ ለዮሐንስ ገለጠለት፤ 2እርሱም ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ያየውን ሁሉ መሰከረ። 3ዘመኑ ቀርቧል፤ እንግዲህ ይህን የትንቢት ቃል የሚያነብብ ብፁዕ ነው፤ የሚሰሙትና የተጻፈውንም የሚጠብቁ ብፁዓን ናቸው።

ሰላምታና ውዳሴ

4ከዮሐንስ፤

በእስያ አውራጃ ለሚገኙ ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤

ካለው፣ ከነበረውና ከሚመጣው፣ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት፣1፥4 ወይም ሰባት ዕጥፍ መንፈስ 5እንዲሁም ታማኝ ምስክር፣ ከሙታን በኵርና የምድር ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

ለወደደንና ከኀጢአታችንም በደሙ ነጻ ላወጣን፣ 6አምላኩንና አባቱን እንድናገለግልም መንግሥትና ካህናት ላደረገን፣ ለእርሱ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን! አሜን።

7እነሆ፤ በደመና ይመጣል፤

የወጉት እንኳ ሳይቀሩ፣

ዐይን ሁሉ ያየዋል፤

የምድርም ሕዝቦች ሁሉ ከእርሱ የተነሣ ዋይ ዋይ ይላሉ።

አዎ! ይህ ሁሉ ይሆናል፤ አሜን።

8“ያለውና የነበረው፣ የሚመጣውም፣ ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ፣ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ” ይላል።

የሰውን ልጅ የሚመስለው

9እኔ ወንድማችሁ ዮሐንስ፣ ከእናንተ ጋር አብሬ በኢየሱስ መከራውንና መንግሥቱን፣ ትዕግሥቱንም ተካፋይ የሆንሁ፣ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክርነት ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ። 10በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤ የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ከበስተ ኋላዬ ሰማሁ፤ 11ድምፁም፣ “የምታየውን በጥቅልል መጽሐፍ ጽፈህ በኤፌሶን፣ በሰምርኔስ፣ በጴርጋሞን፣ በትያጥሮን፣ በሰርዴስ፣ በፊላድልፍያና በሎዶቅያ ወደሚገኙት ወደ ሰባቱ የእስያ አብያተ ክርስቲያናት ላክ” አለ።

12እኔም የሚናገረኝን ድምፅ ለማየት ዞር አልሁ፤ ዞር ባልሁም ጊዜ ሰባት የወርቅ መቅረዞችን አየሁ፤ 13በመቅረዞቹም መካከል “የሰው ልጅ የሚመስል” አየሁ፤ እርሱም እስከ እግሩ የሚደርስ መጐናጸፊያ የለበሰ፣ ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር። 14ራሱና ጠጕሩም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር፣ እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፤ ዐይኖቹም የእሳት ነበልባል ይመስሉ ነበር። 15እግሮቹ በእቶን እሳት የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፤ ድምፁም እንደ ብዙ ወራጅ ውሃ ድምፅ ነበረ። 16በቀኝ እጁ ሰባት ከዋክብት ይዞ ነበር፤ ከአፉም በሁለት በኩል የተሳለ ሰይፍ ይወጣ ነበር፤ ፊቱም በሙሉ ድምቀቱ እንደሚያበራ ፀሓይ ነበረ።

17ባየሁት ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ በእግሩ ሥር ወደቅሁ። እርሱም ቀኝ እጁን በላዬ ጭኖ እንዲህ አለኝ፤ “አትፍራ፤ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም እኔ ነኝ፤ 18እኔ ሕያው ነኝ፤ ሞቼ ነበር፤ እነሆ፤ አሁን ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፤ የሞትና የሲኦል መክፈቻም በእጄ ነው።

19“ስለዚህ ያየኸውን፣ አሁን ያለውንና በኋላም የሚሆነውን ጻፍ። 20በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምስጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት1፥20 ወይም መልእክተኞች ናቸው፤ ሰባቱ መቅረዞች ደግሞ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

启示录 1:1-20

1以下是上帝赐给耶稣基督的启示,让祂把将来要发生的事指示祂的众奴仆。因此,祂差遣天使告诉祂的奴仆约翰2约翰便为自己所看见的一切——上帝的道和耶稣基督做见证。 3那位宣读这预言的人和那些听见并遵守其中内容的人有福了,因为日期近了。

问候七教会

4-5约翰写信给你们亚细亚的七间教会。愿昔在、今在、以后永在的上帝,祂宝座前的七灵1:4-5 七灵”指的就是圣灵,数字七代表完全,不是说有七个灵。和耶稣基督赐给你们恩典和平安。耶稣基督是忠心的见证人,是首先从死里复活的,是世上君王的首领。祂爱我们,用自己的血救我们脱离罪恶, 6使我们成为祭司的国度1:6 成为祭司的国度”或译“成为国度,做祭司”。来事奉祂的父上帝。愿祂得到一切荣耀和权柄,一直到永永远远。阿们!

7看啊!祂要驾云降临,世人都要看见祂,包括曾经刺祂的人。地上的万族都必因祂而哀哭。这事必定实现。阿们!

8主上帝说:“我是阿拉法,我是俄梅加1:8 阿拉法”和“俄梅加”分别是希腊文第一个和最后一个字母,故此句意即“我是始,我是终”。,我是昔在、今在、以后永在的全能者。”

基督的显现

9约翰是你们的弟兄,在耶稣里和你们患难与共、同享国度、一起忍耐。我因传扬上帝的道、为主耶稣做见证而到了拔摩海岛上。 10主日,我被圣灵感动,听见身后有号角般响亮的声音说: 11“把你所看见的写在书上,然后送给以弗所士每拿别迦摩推雅推喇撒狄非拉铁非老底嘉七间教会。”

12我转身看究竟是谁在对我说话,我看见七个金灯台, 13有一位好像人子耶稣的站在这些灯台中间。祂长袍垂脚,金带围胸, 14头与发白如羊毛、洁白如雪,眼睛像火焰, 15双脚像炉中冶炼过的铜一样光亮,声音如同洪涛之声。 16祂右手拿着七颗星,口中吐出一把两刃的利剑,面貌如烈日放光。

17我一看见祂,便扑倒在祂脚前,像死了一样。祂把右手按在我身上,说:“不要害怕!我是首先的,我是末后的, 18我是永活者。我曾经死过,但看啊,我永永远远活着。我掌握死亡和阴间的钥匙。 19所以,你要将所看见的一切——现在和将来要发生的事都记录下来。 20你所看见在我右手中的七颗星和七个金灯台的奥秘是,七颗星代表七间教会的天使1:20 天使”或译“信使”或“使者”,下同,可能指教会的守护天使,或者是教会的领袖。,七个灯台代表七间教会。