ምሳሌ 27 – NASV & JCB

New Amharic Standard Version

ምሳሌ 27:1-27

1ነገ በሚሆነው አትመካ፤

ቀን የሚያመጣውን አታውቅምና።

2ሌላው ያመስግንህ እንጂ የገዛ አፍህ አይደለም፤

ሌላ ሰው ያወድስህ እንጂ የገዛ ከንፈርህ አይሁን።

3ድንጋይ ይከብዳል፤ አሸዋም ሸክም ነው፤

የተላላ ሰው ጕነጣ ግን ከሁለቱም ይከብዳል።

4ንዴት ጨካኝ፣ ቍጣም ጐርፍ ነው፤

በቅናት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል?

5የተገለጠ ዘለፋ፣

ከተደበቀ ፍቅር ይሻላል።

6ከጠላት ደጋግሞ መሳም ይልቅ፣

የወዳጅ ማቍሰል ይታመናል።

7ለጠገበ ማር አይጥመውም፤

ለተራበ ግን እሬት እንኳ ይጣፍጠዋል።

8ከቤቱ ወጥቶ የሚባዝን ሰው፣

ጎጆዋን ለቅቃ እንደምትባዝን ወፍ ነው።

9ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤

የወዳጅ ማስደሰትም ከቅን ምክሩ ይመነጫል።

10የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ አትተው፤

መከራ በሚያጋጥምህ ጊዜ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፤

ሩቅ ካለ ወንድም ቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል።

11ልጄ ሆይ፤ ጠቢብ ሁን፤ ልቤን ደስ አሰኘው፤

ለሚንቁኝ ሁሉ መልስ መስጠት እችል ዘንድ።

12ጥንቁቅ አደጋን አይቶ ይሸሸጋል፤

ማስተዋል የጐደለው ግን ወደዚያው ይሄዳል፤ ይጐዳልም።

13ለማይታወቅ ሰው የተዋሰን ልብሱን ግፈፈው፤

ለዘልዛላ ሴት ከተዋሰማ ዐግተው።

14ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ ባልንጀራውን በማለዳ ቢመርቅ፣

እንደ ርግማን ይቈጠራል።

15ጨቅጫቃ ሚስት፣

በዝናብ ቀን እንደሚወርድ የማያቋርጥ ጠፈጠፍ ናት፤

16እርሷን ለመግታት መሞከር፣ ነፋስን እንደ መግታት ወይም ዘይትን

በእጅ እንደ መጨበጥ ነው።

17ብረት ብረትን እንደሚስል፣

ሰውም ሌላውን ሰው እንደዚሁ ይስለዋል።

18በለስን የሚንከባከብ ፍሬዋን ይበላል፤

ጌታውን የሚያገለግልም ክብርን ይጐናጸፋል።

19ውሃ ፊትን እንደሚያሳይ፣

የሰውም ልብ ማንነቱን ገልጦ ያሳያል።

20ሲኦልና የሙታን ዓለም27፥20 ወይም ሞትና ጥፋት እንደማይጠግቡ ሁሉ፣

የሰውም ዐይን አይረካም።

21ብር በማቅለጫ፣ ወርቅ በከውር እንደሚፈተን፣

ሰውም በሚቀበለው ምስጋና ይፈተናል።

22ጅልን በሙቀጫ ብትወቅጠው፣

እንደ እህልም በዘነዘና ብታደቅቀው፣

ጅልነቱን ልታስወግድለት አትችልም።

23በጎችህ በምን ሁኔታ እንዳሉ ደኅና አድርገህ ዕወቅ፤

መንጋህንም ተንከባከብ፤

24ሀብት ለዘላለም አይኖርምና፤

ዘውድም ከትውልድ ወደ ትውልድ ጸንቶ አይኖርም።

25ደረቁ ሣር ተወግዶ፣ አዲሱ ብቅ ሲል፣

በየኰረብታው ላይ ያለው ሣር ተሰብስቦ ሲገባ፣

26ከበግ ጠቦቶች ልብስ ታገኛለህ፤

ፍየሎችም የዕርሻ መሬት መግዣ ይሆኑሃል።

27አንተንና ቤተ ሰብህን፣

ገረዶችህንም ጭምር ለመመገብ፣

የተትረፈረፈ የፍየል ወተት ይኖርሃል።

Japanese Contemporary Bible

箴言 知恵の泉 27:1-27

27

1今日一日、何が起こるかわからないのに、

明日の予定を得意になって話してはいけません。

2自分で自分をほめるより、

人からほめられるようにしなさい。

3神に背く者は、思いどおりにならないと

腹を立て、手のつけようがありません。

4怒られるよりも、嫉妬されるほうが怖いものです。

5愛するあまり、

悪いことをしても何も注意しないより、

しかるときははっきりしかるほうがよいのです。

6敵にうわべだけ親切にされるより、

友に傷つけられるほうがましです。

7腹がいっぱいだと、

どんなごちそうもまずく感じますが、

腹がすいていると何でもおいしく食べられます。

8家を離れてあちこち渡り歩く人は、

巣を離れてさまよう鳥のようです。

9友に励まされるのは、

香水をつけたように気持ちのよいものです。

10自分の友でも父の友人でも、

彼らを大事にしなさい。

いざというとき、

遠くの親類よりあてになります。

11わが子よ。知恵のある人間になりなさい。

そうすれば、

私もどんなに鼻が高いことでしょう。

12何かを始めるとき、

思慮深い人はきちんと見通しを立てますが、

考えの足りない人は

向こう見ずに手をつけて失敗します。

13見ず知らずの人の借金を立て替える以上に

危ない賭けはありません。

14朝まだ暗いうちに大声であいさつすると、

いやがられます。

15気むずかしい女は、

いつまでもしたたり続ける雨もりのようです。

16風を止めることも、油でぬるぬるした手で

物をつかむこともできないように、

彼女のぐちを止めることはできません。

17鉄が鉄によって研がれるように、

友との熱のこもった議論は、

互いを研ぎ合います。

18果樹園の番人がそこの果物を頂けるように、

主人のために働く者が報酬を受けるのは当然です。

19顔を映すのは鏡ですが、

人のほんとうの心は、

その人がどんな友を選ぶかでわかります。

20野心と死には終わりがありません。

21銀と金の純度はるつぼで試され、

人は、称賛を浴びるときに試されます。

22神の教えに背く愚か者につける薬はありません。

23-24財産はすぐになくなり、

王位はいつまでも続きません。

だから自分の収入や、家畜の状態を知っておきなさい。

25-27牧草を刈り取り、二番草も刈り取ったあと、

山の草を集めなさい。

そうすれば、子羊の毛もやぎの乳も十分に取れ、

家族の生活に困りません。