ምሳሌ 20 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ምሳሌ 20:1-30

1የወይን ጠጅ ፌዘኛ፣ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል፤

በእነዚህ የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም።

2የንጉሥ ቍጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፤

የሚያስቈጣውም ሰው ሕይወቱን ለመከራ ይዳርጋል።

3ከጠብ መራቅ ለሰው ክብሩ ነው፤

ተላላ ሁሉ ግን ለጥል ይቸኵላል።

4ሰነፍ ሰው በወቅቱ አያርስም፤

ስለዚህ በመከር ወራት ይፈልጋል፤

አንዳችም አያገኝም።

5የሰው ልብ ሐሳብ እንደ ጥልቅ ውሃ ነው፤

አስተዋይ ሰው ግን ከዚያ ቀድቶ ያወጣዋል።

6ብዙ ሰው ጽኑ ፍቅር እንዳለው ይናገራል፤

ታማኝን ሰው ግን ማን ሊያገኘው ይችላል?

7ጻድቅ ነቀፋ የሌለበት ሕይወት ይመራል፤

ከእርሱም በኋላ የሚከተሉት ልጆቹ ቡሩካን ናቸው።

8ንጉሥ ለፍርድ ዙፋኑ ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ፣

ክፉውን ሁሉ በዐይኖቹ አበጥሮ ይለያል።

9ለመሆኑ፣ “ልቤን በንጽሕና ጠብቄአለሁ፤

ንጹሕ ነኝ፤ ኀጢአት የለብኝም” የሚል ማን ነው?

10ሁለት ዐይነት ሚዛን፣ ሁለት ዐይነት መስፈሪያ፣

ሁለቱንም እግዚአብሔር ይጸየፋቸዋል።

11ሕፃን እንኳ ጠባዩ ንጹሕና ቅን መሆኑ፣

ከአድራጎቱ ይታወቃል።

12የሚሰሙ ጆሮዎች፣ የሚያዩ ዐይኖች፣

ሁለቱንም እግዚአብሔር ሠርቷቸዋል።

13እንቅልፍ አትውደድ፤ አለዚያ ድኻ ትሆናለህ፤

ዐይንህን ክፈት፤ የተትረፈረፈ ምግብ ይኖርሃል።

14ዕቃ የሚገዛ፣ “የማይረባ ነው፤ የማይረባ ነው” ብሎ ያራክሳል፤

ሲመለስ ግን በግዥው ይኵራራል።

15ወርቁም አለ፤ ቀዩም ዕንተትረፍርፏል፤

ዕውቀት የሚናገሩ ከንፈሮች ግን ብርቅ ጌጦች ናቸው።

16ለማይታወቅ ሰው ዋስ የሆነውን ልብሱን ግፈፈው፤

ለዘልዛላ ሴት የተዋሰውን በቃሉ ያዘው።

17ሰው በማጭበርበር ያገኘው ምግብ ይጣፍጠዋል፤

በመጨረሻ ግን አፉን ኰረት ሞልቶት ያገኘዋል።

18ምክር ጠይቀህ ዕቅድ አውጣ፤

ጦርነት የምትገጥም ከሆነ መመሪያ ተቀበል።

19ሐሜተኛ ምስጢር ያባክናል፤

ስለዚህ ለፍላፊን ሰው አርቀው።

20አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ፣

መብራቱ በድቅድቅ ጨለማ ይጠፋል።

21ከጅምሩ ወዲያው የተገኘ ርስት፣

በመጨረሻ በረከት አይኖረውም።

22“ለደረሰብኝ በደል ብድሬን ባልመልስ!” አትበል፤

እግዚአብሔርን ጠብቅ፤ እርሱ ይታደግሃል።

23ሁለት ዐይነት ሚዛን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤

አባይ ሚዛን አይወደድም።

24የሰው አካሄዱ በእግዚአብሔር ይመራል፤

ሰውስ የገዛ መንገዱን እንዴት ማስተዋል ይችላል?

25በችኰላ ስእለት መሳል፣

ከተሳሉም በኋላ ማቅማማት ለሰው ወጥመድ ነው።

26ጠቢብ ንጉሥ ክፉዎችን አበጥሮ ይለያል፤

የመውቂያ መንኰራኵርንም በላያቸው ላይ ይነዳል።

27የሰው መንፈስ ለእግዚአብሔር መብራት ነው፤20፥27 ወይም የእግዚአብሔር መብራት የሰውን መንፈስ ይመረምራል

ውስጣዊ ማንነቱንም ይፈትሻል።

28ፍቅርና ታማኝነት ንጉሥን ይጠብቁታል፤

በፍቅርም ዙፋኑ ይጸናል።

29የጎልማሶች ክብር ብርታታቸው፣

የሽማግሌዎችም ሞገስ ሽበታቸው ነው።

30የሚያቈስል በትር ክፋትን ያስወግዳል፤

ግርፋትም የውስጥ ሰውነትን ያጠራል።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

箴言 20:1-30

1酒使人放肆,烈酒叫人吵闹。

因酒误事,实为不智。

2君王震怒如狮子咆哮,

触怒他的人自寻死路。

3避免纷争是光荣,

愚人个个爱争吵。

4懒惰人不按时耕种,

收获时必一无所得。

5人心的谋略如深水,

唯有哲士才能汲取。

6人都声称自己忠诚,

但谁能找到忠信者?

7义人行为正直,

他的后代也蒙福。

8王坐在宝座上审判,

他的眼目明察罪恶。

9谁敢说:“我心灵洁净,纯洁无罪?”

10缺斤少两、尺寸不足,

都为耶和华所憎恶。

11孩童的举动是否纯良,

都显明他的本性。

12能听的耳,能看的眼,

两者都为耶和华所造。

13不要贪睡,免得贫穷;

勤劳工作,粮食丰足。

14买主总说货物不好,

买走后又连连自夸。

15智慧之言胜过黄金和许多珠宝。

16谁为陌生人作保,就拿去谁的外衣;

谁为外族人作保,就要承担责任。

17骗来的饼觉得香甜,

最后却是满口泥沙。

18集思出良策,

征战靠智谋。

19嚼舌的人泄露秘密,

不可结交多嘴的人。

20咒骂父母的人,

他的生命20:20 生命”希伯来文是“灯”。必消逝在黑暗中。

21早年轻易得来之财,

最终不会成为祝福。

22不要说:“我要以恶报恶”,

要等候耶和华替你申冤。

23耶和华憎恶缺斤少两,

祂厌恶骗人的天平。

24人的脚步由耶和华所定,

人怎能知道自己的道路?

25人向主许愿要三思,

免得事后作茧自缚。

26明君必筛出恶人,

用石磙碾轧他们。

27心灵是耶和华的灯,

鉴察人的肺腑心肠。

28君王靠慈爱和忠信护佑,

他的王位因慈爱而稳固。

29力量是青年的荣耀,

白发是老人的尊荣。

30鞭伤能驱除罪恶,

责打能洁净人心。